Murad malik
27/06/2025
እስራኤል የተኩስ አቁም ስምምነቱ መጣሷ ተነገረ !
የእስራኤል ጦር በደቡባዊ ሊባኖስ ላይ ባደረሰው የአየር ጥቃት ቢያንስ አንድ ሰው ሲገደል ከአስር በላይ ቆስለዋል ሲል የሊባኖስ መንግስት አስታወቀ ።
የሊባኖስ መንግስት ብሄራዊ የዜና አገልግሎት የሀገሪቱን የጤና ጥበቃ ሚኒስቴር ጠቅሶ እንደዘገበው በናባቲህ የመኖሪያ አፓርትመንት ህንጻ ላይ በደረሰ የአየር ጥቃት አንዲት ሴት ህይወት ሲያልፍ 13 ሌሎች ሰዎች ቆስለዋል ። በተመሳሳይም በከተማው ዳርቻ ላይ በደረሰ የአየር ጥቃት ሌሎች ሰባት ሰዎች ቆስለዋል ሲል ዘግቧል።
የሊባኖሱ ፕሬዝዳንት ጆሴፍ አውን አርብ ዕለት እስራኤል በሊባኖስ ላይ ጥቃቱን በመቀጠሏ አሜሪካ ያደረሰውን የተኩስ አቁም ስምምነትን ያለማቋረጥ እየጣሰች ነው ሲሉ ከሰዋል።
የእስራኤል መንግስት በበኩሉ ጦር ቃል አቀባይ በኩል ባወጣዉ መግለጫ በሲቪል ላይ ጉዳት አደረሰ የሚለዉ ዘገባ “ትክክል አይደለም” ያሉ ሲሆን ጥቃቱ የተፈፀመው
በናባቲህ ግዛት ውስጥ በሚገኘው ቤልፎርት ውስጥ ሂዝቦላ እስራኤል ከዚህ ቀደም ከጥቅም ውጪ ያደረገችው የመከላከያ ስርአትና የመሳርያ ማከማቻ ዳግም መጠቀም በመጀመሩ ይህን ለወታደራዊ አገልግሎት የሚዉል ስፍራ ኢላማ ያደረገ ነዉ ብሏል ።
ሄዝቦላህን "በመኖሪያ ህንጻዎች እና በሊባኖስ ሲቪሎች አቅራቢያ ያሉ ኃይለኛ ሮኬቶችን ማከማቸቱን በመቀጠል አደጋ ላይ ጥሏል" ሲሉ ሄዝቦላን ከሰዋል።
የእስራኤል ጥቃት እንደገና መጀመር ከአንድ አመት በላይ የተኩስ ልውውጦችን ያስቆመውን በህዳር ወር የተፈፀመውን በሁለቱ ወገኖች ስምምነት የሚጥስ እንደሆነ ከአልጀዚራ የዜና ወኪል ያገኘነው መረጃ ያሳያለ
27/06/2025
ጥቂት ፖለቲከኞች ሙሉ ህዝቡን በተደጋጋሚ ለጦርነት የሚዳርጉበት ሁኔታ ማክተም አለበት - አቶ ጌታቸው ረዳ
**************************************
ጥቂት ፖለቲከኞች ሙሉ ህዝቡን በተደጋጋሚ ለጦርነት የሚዳርጉበት ሁኔታ ማክተም እንዳለበት የጠቅላይ ሚኒስትሩ የምስራቅ አፍሪካ ጉዳዮች አማካሪ ሚኒስትር ጌታቸው ረዳ ተናገሩ።
አቶ ጌታቸው ይህን ያሉት “ሰላም፣ዲሞክራሲ እና ልማት በትግራይ እድሎች እና ፈተናዎች” በሚል ሀሳብ ውይይት በተካሄደበት ወቅት ነው።
በመድረኩ ንግግር ያደረጉት የሰላም ሚኒስትር መሐመድ እድሪስ በበኩላቸው፥ በሰላም፣ ልማትና ዲሞክራሲ ጉዳዮች ወጣቱ መምከሩ ብዙ እንዲያተርፍ ያደርገዋል ብለው፤ የጎደለን ነገርን በውይይት መፍታት እንደሚያስፈልግ ነው የገለጹት።
ዘላቂ ሰላምን በክልሉ ለማረጋገጥ የሚያስችሉ ጉዳዮች ላይ ከትግራይ ተወላጆች ጋር ነው ምክክሩ የተደረገው።
መድረኩ በሴንተር ፎር ሪስፖንሲብል ኤንድ ፒስፉል ፖለቲክስ ከአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ ጋር በመተባበር የተዘጋጀ ሲሆን፤ በትግራይ ዘላቂ ሰላምን ለማረጋገጥ በሚያስችሉ ጉዳዮች ትኩረት አደርጓል።
በትግራይ የገጠመውን የሰላም እጦት በሰላማዊ መንገድ መፍትሄ መስጠት ዓላማ ባደረገው መድረክ፤ ሁሉም በርብርብ በመስራት በክልሉ ሰላም፣ዲሞክራሲ እና ልማት ማረጋገጥ ይገባል ነው የተባለው።
የጠቅላይ ሚኒስትሩ የምስራቅ አፍሪካ ጉዳዮች አማካሪ ሚኒስትር ጌታቸው ረዳ ጥቂት ፖለቲከኞች ሙሉ ህዝቡን በተደጋጋሚ ለጦርነት የሚዳርጉበት ሀኔታ ሊያከትም እንደሚገባ ገልጸዋል።
የውይይቱ ተሳታፊዎችም ክልሉ ሰላሙን ማረጋገጥ ባለመቻሉ ችግሮች መኖራቸውን በመጠቆም፤ የውይይት መድረኮች ተደርገው የሚመለከታቸው ባለድርሻ አካላት ኃላፊነታቸውን ሊወጡ ይገባል ሲሉ ሀሳባቸውን ሰጥተዋል።
#አናስ ኢብኑ ኑር #ሰላም
24/06/2025
22/06/2025
ኢራን የሆርሙዝ የባህር ሰርጥን እንዳትዘጋ ቻይና እንድታግባባ አሜሪካ ጠየቀች
***********************
ኢራን የሆርሙዝ የባህር ሰርጥን እንዳትዘጋ ቻይና የማግባባት ስራ እንድትሰራ የአሜሪካ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ማርኮ ሩቢዮ ጠየቁ፡፡
ማርኮ ሩቢዮ በዚህ የባህር ሰርጥ ነዳጅ ጭነው ከሚያልፉት መርከቦች መሀል የቻይና መርከቦች ስለሚገኙበት የባህር ሰርጡ ቢዘጋ ቻይናም ተጎጂ በመሆኗ ይህ እንዳይሆን ማገዝ አለባት ብለዋል።
ኢራን ይህንን የባህር ሰርጥ ብትዘጋው አሜሪካን ጨምሮ ብዙ ሀገራት ኢኮኖሚ እንደሚጎዳ የገለፁት ማርኮ ሩቢዮ፤ ይህ ሳይሆን ቀርቶ ኢራን ይህን ውሳኔ ከወሰነች አሜሪካና ሌሎች ሀገራት ምላሽ ሊሰጡ ይችላሉ ሲሉ ማስጠንቀቃቸውን ሮይተርስ ዘግቧል፡፡
የኢራን ፓርላማ የአለማችን 20 በመቶ የሚሆነው ድፍድፍ ነዳጅ የሚተላለፍበት የባህር ሰርጥን ለመዝጋት የቀረበውን የውሳኔ ሀሳብ ማፅደቁ የተገለፀ ሲሆን፤ ውሳኔ ተፈጻሚ የሚሆነው የኢራኑ መሪ አያቶላህ አሊ ኻሚኒ በሚያሳልፉት የመጨረሻ ትእዛዝ መሆኑ ተነግሯል፡፡
40 ኪሎ ሜትር ብቻ ስፋት ያለው የሆርሙዝ የባህር ሰርጥ የመዘጋት አደጋ ካጋጠመው በአለም የነዳጅ ዋጋ ላይ ትልቅ ተፅእኖ ሊፈጥር እንደሚችልም ተገልጿል፡፡
15/06/2025
ይድረስ ለ Ethio telecom
ጉዳዩ:-የ2G-3G ጥያቄ ሰለመጠየቅ ይመለከታል::
ከላይ በርዕሱ ለመግለፅ እንደተሞከረው በአፋር ክልል ኪብላቲ ረሱ ዳሉል ወረዳ መሃል ከተማ
የሚትገኝ አዱኩዋ በሚባል የሚትታወቅ ከተማ እስካሁን በ2G ኒትወርክ አገልግሎት ውስጥ ትገኛለች
ይቺ ውብ ከተማይቷ ብዙ የማህበረሰብ ከፍሎች አክፋ የሚትገኝ ከተማ ሲትሆን በራሷ እና በህዝብ ብዛት ልክ በቂ የኢንተርኔት አገልግሎት ያላገኘች የአገልግሎት ለውጥ በተሰፋ የሚትጠብቅ ከተማ ናት
አሁንም የከተማው ማህበረሰብ በእናንተ ላይ ሙሉ እምነት ሰለሚኖራቸው ህልማቸወ እውን እንዲታደርጉ ዘንድ የድርሻቹህ እንድትወጡ በአክብሮት ለመጠየቅ እወዳለሁ::
Sher & following &like & copy link
29/03/2025
ኢድ ሙባረክ!
የሸዋል ወር ጨረቃ በሳኡዲ አረበያ በመታየቷ የኢድ አል ፊጥር በዓል በነገው ዕለት እሁድ ማርች 30 በደማቅ ሁኔታ የሚከበር ይሆናል::
አላህ መልካም ስራችንን ይቀበለን!
05/12/2024
በትግራይ ክልል ባለው ወቅታዊ የፖለቲካ፣ የአስተዳደርና የፀጥታ ሁኔታ ላይ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በተገኙበት ውይይት ተካሄደ
****************
በዛሬው ዕለት በትግራይ ክልል ባለው አጠቃላይ የፖለቲካ፣ የአስተዳደር እና የፀጥታ ሁኔታ እንዲሁም ሌሎች ተያያዥ ጉዳዮች ላይ የፌደራል መንግሥት ከፍተኛ አመራሮች በክልሉ ካሉ የፖለቲካ እና የፀጥታ አመራሮች ጋር ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በተገኙበት ሰፊ ውይይት አድርገዋል።
በውይይቱ ወቅት፥ በክልሉ የሚታዩ ችግሮችን በጋራ መፍታት በሚቻልበት ሁኔታ ላይ ምክክር ተደርጓል።
ይህን ተከትሎም በተለዩ አንኳር ጉዳዮች ላይ በተቀመጡ የጋራ አቅጣጫዎች መሠረት በትብብር በመስራት የክልሉን ህዝብ የፀጥታ፣ የመልካም አስተዳደር እና የልማት ፍላጎት ለማሟላት አስቻይ ሁኔታ ለመፍጠር መግባባት ላይ ተደርሷል።
በተለይም ከመኖሪያቸው የተፈናቀሉ ዜጎችን ወደቀዬአቸው እና የቀድሞ ታጣቂዎችን ደግሞ ወደ መደበኛ ሕይወት የመመለስ ሥራ በሚሳለጥበት እና በበለጠ ትኩረት በሚሰራበት ሁኔታ ላይ መግባባት ተፈጥሯል።
በተጨማሪም በክልሉ ያሉ የተፈጥሮ ሀብቶች አጠቃቀም የህዝብን እና የሀገርን ጥቅም በሚያስጠብቅ ሕጋዊ አግባብ እንዲከናወን፣ ለህዝብ የሚቀርቡ የመንግሥት አገልግሎቶችም የህዝብን ፍላጎት በሚመጥን አግባብ እንዲሻሻሉ ቀጣይነት ያለው ጠንካራ ስራ እንዲሰራ በውይይቱ አቅጣጫ ተቀምጧል።
በመጨረሻም የክልሉ ጊዜያዊ አስተዳደር ክልላዊ ምርጫ እስኪያካሂድ ድረስ ያለበትን ኃላፊነት ለመወጣት በሚያስችለው አግባብ ላይም አቅጣጫ በማስቀመጥ ውይይቱ ተጠናቅቋል።
Etv News Amharic ኢቲቪ ዜና አማሪክ
https://t.me/etvnewsamharic
Shout out to my newest followers! Excited to have you onboard! Iman Zaelani, Mohamed Omer, Ali Nesru, Nazrul Islam
16/11/2024
Jabal Al Noor, Makkah 🕋🌴🥰✨️
Cave Hira
Innaa-lillaahi wa-inna ileyhi raajiquun 😭😭😭
-abeena_Muusa Laahadda Acarra Amanok rabah nek baxsimem naabbe.😭
Yalli kaah racmatay addunyak tayse akeera kaah yacaay Kay buxah marah imaan Kee Sabri yacaay
Click here to claim your Sponsored Listing.
Category
Website
Address
Meklle
Addis Ababa