Agape
10/02/2020
ነፍሴ ለመለመች || ኤፍሬም አለሙ
ነፍሴ ለመለመች ለመለመች ለመለመች
ጌታን ስላገኘች ለመለመች ለመለመች(x2)
የደረቁ አጥንቴን አለምልሞልኛል
ፅዋዬንም ደግሞ ጌታ ሞልቶልኛል
በሞት ጥላ ብሄድ የቱ ያስፈራኛል
ልኡል እረኛዬ መኖሪያዬ ሆኗል
ነፍሴ ለመለመች ለመለመች ለመለመች
ጌታን ስላገኘች ለመለመች ለመለመች(x2)
ከአመት እስከ አመት እንዳፈራ በወንዙ ዳር ተተክያለው
ፍሬዋንም ደግሞ ሁሌ እንደምትሰጥ እንደማይረግፈው ዛፍ ሆኛለው
ሙቀት እና ብርዱ ቢነሳ አልሰጋም እደርቃለው ብዬ
ህይወቴ ከምንጩ ተጣብቋል እለመልማለው ዝምብዬ
የደረቁ አጥንቴን አለምልሞልኛል
ፅዋዬንም ደግሞ ጌታ ሞልቶልኛል
በሞት ጥላ ብሄድ የቱ ያስፈራኛል
ልዑል እረኛዬ ከለላዬ ሆኗል
ነፍሴ ለመለመች ለመለመች ለመለመች
ጌታን ስላገኘች ለመለመች ለመለመች(x2)
ይኀው.... አምልኮ
ይኀው.....ዝማሬ
ይኀው....ጌታ
ተቀበለኝ አሽትተው ላንተ ክብር ሲያንስ ነው
ሲያንስ ነው(x4)
ኦሆሆሆ....በደረቅ ምድር
ኦሆሆሆ....ውሃ በሌለው
ኦሆሆሆ....አንተን አግኝቼ ኦሆሆሆ....ተደስቻለው
ኦሆሆሆ....እረካው በቃ
ኦሆሆሆ....ቆረጠ ጥሜ
ኦሆሆሆ....ዘመኔ ያልቃል ኦሆሆሆ....በልምላሜ
ነፍሴ ለመለመች ለመለመች ለመለመች
ጌታን ስላገኘች ለመለመች ለመለመች(x2)
🎼
Click here to claim your Sponsored Listing.
Category
Telephone
Website
Address
Addis Ababa