Ethio-Cinema
11/12/2022
አርቲስት ታሪኩ ብርሃኑ (ባባ) ከዚህ ዓለም በሞት ተለየ
በፊልም ሥራዎቹ ብዙዎች ዘንድ ተወዳጅነትን እና ዝናን ያተረፈው አርቲስት ታሪኩ ብርሃኑ (ባባ) ከዚህ ዓለም በሞት ተለየ።
ወጣቱ የፊልም ባለሙያ ባደረበት ሕመም ለሳምንታት በሕክምና ሲረዳ ቢቆይም ሕይወቱ ሊያልፍ ችሏል።
አርባ ያህል ፊልሞች ላይ የተወነው አርቲስት ታሪኩ በሕመም ምክንያት ሕይወቱ ማለፉን ኢፕድ ከአርቲስቱ የቅርብ ሰዎች ማረጋገጡን ዘግቧል።
አርቲስቱ ወጣት በ97፣ ወንድሜ ያዕቆብ፣ ላውንድሪ ቦይ፣ ማርትሬዛ፣ ይመችሽ-የአራዳ ልጅ 2፣ ሞኙ የአራዳ ልጅ 4፣ አንድ ሁለት፣ ብር ርርር፣ ወደው አይሰርቁ፣ ወፌ ቆመች፣ እንደ ቀልድ፣ ወቶ አደር፣ አባት ሀገር እና ሌሎችም ፊልሞች ላይ ተውኗል።
አርቲስት ታሪኩ ብርሃኑ የአንድ ልጅ አባት ነበረ።
15/11/2022
Summary!
በባለፊት ሳምንታት የተማርናቸውን ትምህርቶች ከምስል ጋር አስደግፈን በአጫጭር ገለፃዎች እንደሚከተለው ቀርበዋል።
የፊልም ስራ ዑደት
LIFECYCLE OF A FILM
የፊልም ስራ በመደበኛነት በሶስት ክፍለ ጊዜ ውስጥ ያልፋል ቅድመ ማምረት /Pre production/ ማምረት / Production/ እና ድህረ ማምረትን / Post production/
ቅድመ ማምረት የፊልም ቀረፃውን ለማድረግ ዝግጅቶች የሚደረጉበት ክፍለ ጊዜ ነው፡፡ በማምረት ክፍለ ጊዜ ደግሞ ፊልሙ በተመረጠለት መቼት ላይ ከምድብ ተዋንያኖቹ/cast/ እና ከባለሙያዎቹ/crew/ ጋር በመሆን ቀረፃ የሚከናወንበት ክፍለ ጊዜ ነው፤ እንዲሁም የድህረ ማምረት ክፍለ ጊዜ ደግሞ የተቀረጸው ፊልም /Footage/ የሚቀናበርበት እና ወደ አለቀለት ፊልም የሚለወጥበት ክፍለጊዜ ነው፡፡
የተለያዩ የፊልም ስራ አባላቶች በእያንዳንዱ ክፍለ ጊዜ ውስጥ በተለያየ የስራ መጠን የሚወሰን ተሳትፎ ይኖራቸዋል፤ አንዳንድ ባለሙያዎች እንደ ፕሮዲውሰር እና ዳይሬክተር የመሰሉት ባጠቃላይ የፊልም ስራው ዑደት ተሳታፊ ናቸው፤ ሌሎች እንደ ቪዥዋል ኢፌክት አርቲስት የመሰሉት ማለትም ባለቀለት የፊልም ፎቴጅ (ተቀርጾ የተቀናበረ ፊልም) ላይ የሚሰሩ ዓይነት ሙያተኞች አነስተኛ ተሳትፎ ያላቸው እና በአንደኛው ክፍለ ጊዜ ላይ ብቻ ስራቸውን የሚሰሩ ዓይነት ሊሆኑ ይችላሉ፡፡
የፊልም ሰሪዎች ተግባራት ከታች ባለው ግራፍ ላይ አልተጠቀሱም ነገር ግን በተከታታይ በተፃፉት ፅሁፎች/articles/ ውስጥ በሚገባ ተብራርተዋለል፡፡
ከታች የምትመለከቱት ግራፍ የፊልም ስራ ዑደትን ከፊልም ድርሰት /Script/ ሀሳብ ጀምሮ እስከመጨረሻ ያለቀለት ፊልም ማረጋገጫ ድረስ ያለውን ያሳያል፡፡ ሁሉም ዋና ዋና የስራ እርከን ደረጃ በእያንዳንዱ ክፍለ ጊዜ ላይ እንዲታዩ ሆነው ቀርበዋል፡፡
ሆኖም ግን መታወቅ ያለበት በተግባር የፊልም ስራው ዑደት ከወራት እስከ ዓመታት ሊጠናቀቅ የሚችል መሆኑን ሲሆን በግራፉ ላይ የቀረበው እርከን/steps/ የሚያሳየው በፊልም አመራረት ወቅት በየጊዜው የሚኖረውንና መኖር ያለበትን የአሰራር ድግግሞሽ ነው፡፡ በተጨማሪም የተወሰኑ ጥቂት ዕርከኖች /steps/ በተመሳሳይ በእንዳንዱ ክፍለ ጊዜ ውስጥ በተመሳሰለ መልኩ ሊከሰቱ ይችላሉ።
Click here to claim your Sponsored Listing.
Category
Contact the business
Telephone
Website
Address
Mexico
Addis Ababa