Federal Civil Service Commission

Federal Civil Service Commission

Share

Photos from Federal Civil Service Commission's post 28/05/2026

የመንግስት አገልግሎትና አስተዳደር ሪፎርም የዝግጅት ምዕራፍ ትግበራ ላይ የተካሄደው ድጋፋዊ የክትትል ሪፖርት ተገመገመ፡፡
*********************
አዲስ አበባ ግንቦት 20/2018 ዓ.ም ፣ሲቪል ሰርቪስ ኮሚሽን፤
የፌዴራል ሲቪል ሰርቪስ ኮሚሽን ያደራጀው የሱፕርቪዥን ቡድን በክልሎችና በከተማ አስተዳደሮች ሲያካሄድ የነበረውን የመንግስት አገልግሎትና አስተዳደር ሪፎርም የዝግጅት ምዕራፍ ክትትልና ድጋፍ ስራ ሪፖርት በማጠናቀቅ አፈጻፀሙ የሚገመገምበትን መድረክ አዘጋጅቷል።

በየክልሉ ተሰማርተው የነበሩ የሱፐርቪዥን ቡድኑ አባላት አሁን ባለቡበት ቦታ ሆነው በቀላሉ መሳተፍ እንዲችሉ መድረኩ በበይነ-መረብ (ኦንላይን) የተከናወነ ሲሆን፣ በመድረኩ የተገኙትና ውይይቱን የመሩት የሲቪል ሰርቪስ ኮሚሽን ኮሚሽነር ክቡር ዶ/ር መኩሪያ ኃይሌ ሲሆኑ የኮሚሽኑ ም/ኮሚሽነር ክብርት ወ/ሮ አልማዝ መሰለም በውይይቱ ላይ ተገኝተው ከክትትልና ሱፐርቪዥን ቡድኑ የተጠናቀረውን ጥቅልና ጭምቅ ሪፖርት አቅርበዋል።

ይህ ሰፊ የድጋፋዊ ሱፐርቪዥን ሥራ የተከናወነው በመጀመሪያው ዙር (Wave 1) የዝግጅት ምዕራፍ ሥራቸውን በስኬት አጠናቀው ወደ ትግበራ የተሸጋገሩ አራት የፌዴራል ተቋማት ሪፎርሙን ወደ ክልልና ከተማ አስተዳደር ቢሮዎች የማውረድ ሥራ መጀመራቸውን ተከትሎ ነው።

በዚህም መሠረት ከፌዴራልና ከክልል የተውጣጡ አመራሮችና ከፍተኛ ባለሙያዎችን ያቀፉ 12 የክትትል ቡድኖች በ11 ክልሎችና በሁለቱ ከተማ አስተዳደሮች ስር በሚገኙ አራት ቁልፍ ቢሮዎች ማለትም በፐብሊክ ሰርቪስና የሰው ሀብት ልማት፣ በሥራና ክህሎት፣ በጤና እንዲሁም በፋይናንስ ቢሮዎች ላይ የተዘጋጀውን የመገምገሚያ መስፈርት መሠረት በማድረግ ድጋፋዊ ምልከታና ክትትል ያደረጉ ሲሆን የክትትሉ ዋና ዓላማ የሪፎርም ሥራው ወደ ክልል ሴክተር ቢሮዎች የወረደበትን ደረጃ መፈተሽ፣ ጠንካራና ደካማ አፈጻጸሞችን መለየት፣ እንዲሁም የታዩ ክፍተቶችን በቦታው ላይ በሚደረግ ድጋፍ መሙላትና መልካም ተሞክሮዎችን መቅሰም እንደነበር ተገልጿል።

በመድረኩ ላይ በቀረበው ዝርዝር ሪፖርት መሠረት በእያንዳንዱ ተቋም የታዩ የሪፎርም አፈጻጸሞች፣ የተደረጉ የተሞክሮ ልውውጦች፣ ያጋጠሙ ተግዳሮቶችና የተወሰዱ የመፍትሔ እርምጃዎች ላይ ከክልል ም/ቢሮ ኃላፊዎችና ከጠቅላላው የቡድኑ አባላት ጋር ሰፊ ውይይት ተደርጓል።

ከተሳታፊዎች የተነሱ አንዳንድ ጠቃሚ የማስተካከያ ሐሳቦችን በማካተት የተጠናቀረው ይህ የሪፎርም አፈጻጸም ሪፖርት፣ በቀጣይ በምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ክቡር አቶ ተመስገን ጥሩነህ ለሚመራው ሀገራዊ የሪፎርም ኮሚቴ ቀርቦ ውሳኔና አቅጣጫ የሚሰጥበት እንደሚሆን ተገልጿል።
# የውጭ ግንኙነትና ኮሚኒኬሽን ስራ አስፈጻሚ

Photos from Federal Civil Service Commission's post 04/05/2026

በመንግስት መሥሪያ ቤቶች እየተካሄደ ባለው የሪፎርም እና የብቃት ምዘና ሂደት መሠረት፣ ከደረጃ 1 (Level 1) በታች ያሉ የመንግስት ሰራተኞችን አቅም ለመገንባት የሚያስችል የቴክኒክና ሙያ ስልጠና እየተሰጠ መሆኑ ተገለፀ።
+++++++++++++++++++++++++++++++++
አዲስ አበባ፣ ሚያዚያ 26 ቀን 2018 ዓ.ም፣ የፌዴራል ሲቪል ሰርቪስ ኮሚሽን፡
በመንግስት መሥሪያ ቤቶች እየተካሄደ ባለው የመንግስት አገልግሎትና አስተዳደር ሪፎርም የብቃት ምዘና ሂደት መሠረት ወደ ምዘና ከመግባታቸው በፊት ቅድመ ስልጠና፣ በዌቭ አንድ ወደ ሪፎርሙ ለገቡ ተቋማት ከደረጃ 1 በታች ያሉ የመንግስት ሰራተኞችን አቅም ለመገንባት የሚያስችል የቴክኒክና ሙያ ማሻሻያ ስልጠና አዲስ አበባ በሚገኙ 10 የቴክኒክና ሙያ ማሰልጠኛ ተቋማት ገብተው የብቃት ስልጠና የሚያገኙበት መንገድ መመቻቸቱ ተገለጸ፡፡

ይህ ስልጠና የሚሰጠው በአራት ዙር ሲሆን በመጀመሪያው ዙር የፌዴራል ቴክኒከና ሙያ ማሰልጠኛ ኢንስቲትዩት፣ ጄኔራል ዊንጌት ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ፣ ተግባረ እድ ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ፣ ተፈሪ መኮንን ፖሊ ቴክኒከ ኮሌጅ፣ አቃቂ ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ፣ ጎፋ ኢንዱስትሪያል ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ፣ ምስራቅ ፖሊ ቴኪኒክ ኮሌጅና ልደታ ማኑፋክቸሪንግ ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጆች ለሰራተኞቹ ስልጠናውን እየሰጡ ይገኛሉ፡፡

በዚህ ከሁለት እስከ ሶስት ወር በሚቆየው የመጀመሪያ ዙር ስልጠና በፌዴራል ተቋማት የሚገኙ ከ30 በላይ ከሚሆኑ የመንግስት ተቋማት የተውጣጡ በተለያዩ ሙያዎች ላይ እያገለገሉ የሚገኙና ከደረጃ አንድ በታች የሆኑ ሰራተኞች ተለይተው እየተሳተፉ መሆኑ ተገልጾዋል፡፡

ስልጠናውም በተለያዩ ብቃቶች ዙሪያ የተዘጋጀ ሲሆን ከስልጠናው በኋላ በሚደረገው ምዘና ባስመዘገቡት ውጤት መሰረት ለሰልጣኞች ሰርተፍኬት ይበረከትላቸዋል፡፡

ይህ መሰል ስልጠና መዘጋጀቱ መንግስት የሰራተኛውን አቅም ከማጎልበትና ለብቃት ምዘናው ዝግጁ ከማድረግ አንጻር የተሰራና ከፍተኛ ድጋፍ የሚሰጥ መሆኑም ተመላክቷል፡፡
#የውጭ ግንኙነትና ኮሚኒኬሽን ስራ አስፈጻሚ ቢሮ

Want your organization to be the top-listed Government Service in Addis Ababa?
Click here to claim your Sponsored Listing.

Address


Bole Road, Kirkos S. City Woreda 09 Around Flamingo Restaurant
Addis Ababa
1082

Opening Hours

Monday 08:30 - 17:30
Tuesday 02:30 - 17:30
Wednesday 02:30 - 17:30
Thursday 02:30 - 17:30
Friday 02:30 - 17:30