LELA News
08/06/2026
ኢትዮጵያ ሆይ ...
የንጉሱ መዝሙር በዛሬ አይን | ኃ/ስላሴ | ደርግ | ኢህአዴግ | The Anthem of the King Through Today's Eyes ''ኢትዮጵያ ሆይ ደስ ይበልሽ" ለ45 ዓመታት የተዘመረ እና በኢትዮጵያ ለረጅም ጊዜ ያገለገለ ብሄራዊ የህዝ...
06/06/2026
"በመጀመርያ አርሲ በወገኖቻችን ላይ በደረሰው የሞት አደጋ የተሰማኝን ሀዘን እየገለፅኩ ሀዘኑ የደረሰባቹ የአካባቢው ነዋሪዎች እንዲሁም ለመላው የኢትዮጵያ ህዝብ ፈጣሪ መፅናናቱን እንዲስጠን እየፀለይኩ በዛሬው ዕለት በአዲስ አበባ እስታድዮም ላቀርበው የነበረው የሙዚቃ ዝግጅት መሰረዜን እና ኮንሰርቱንም እማልሳተፍ መሆኔን በትህትና እገልፃለሁ ። በስተመጨረሻም ለኤቨንቱ አዘጋጆች ለተፈጠረው ነገር እጅግ ይቅርታ እጠይቃለሁ። እግዝያብሔር ይብቃቹ ይበለን!"
ድምጻዊ
02/06/2026
ሐውለት አህመድ (ፒኤችዲ) እንደፃፉት!...
***
ይቺም ሻማ ሰልችታለች!
===============
በአገራችን ለሚቀጥሉት ብዙ አሥርት ዓመታት ምናልባትም አሁን በሕይወት የምንገኝ ሰዎች በአጠቃላይ ሳናይ የምንሞተው ነገር የመንግሥት ከፍተኛ ባለሥልጣናት ''ኃላፊነቴን በአግባቡ ስላልተወጣሁ ሥራዬን በፈቃዴ ለቅቄያለሁ፤ ከ'ኔ የተሻለ ሰው ይምራው'' የሚለው ነው።
በአርሲ ዞን በኦርቶዶክስ ክርስትና አማኞች እና አብያተ-ክርስትያናት ላይ በተደጋጋሚ ጥቃቶች እየተሰነዘሩ ብዙ ሰው በአሰቃቂ ሁኔታ ሞተ፤ አብያተ-ክርስትያናት እና ቅርሶችም ወደሙ፤ በነዋሪዎቹ ዘንድ ሥጋትና ጥርጣሬ ሰፈነ።
ይሄን ተደጋጋሚ ጥቃት ለማስቀረት የተሠራ ሥራ አለ? ሰላም ማስከበር 100% የክልሉ መንግሥት ሥራ አይደለም እንዴ? ምን አድርጓል? ሰላም ማስከበር ካቃታቸው በኢትዮጵያ ሕግ መሠረት ''አልቻልንም፤ የፌዴራል መንግሥት ጣልቃ ይግባልን'' ይባላል እኮ! መቼም ''እኔ ለዚህ ኃላፊነት ብቁ ሆኜ አልተገኘሁም፤ የተሻለ ብስለትና ልምድ ያለው ሰው ይተካኝ'' የሚሉ ኃላፊዎችን በሕይወት እያለን እንደማናይ ዕሙን ነው።
ሰው ባለቀ ቁጥር ይቺን ሻማ ብልጭ ማድረግ ምን ፋይዳ አለው? ይሰለቻል። የክልሉ መንግሥት ለዚህ ዞን ልዩ ትኩረት ሰጥቶ ሕዝቡን ይጠብቅ። በጊዜ መፍትሔ ካልተሰጠው የዚህ ዳፋ የማይተርፈው ሰው የለም።
እንደ አንድ ተርታ ዜጋ በደረሰው ጉዳት ሐዘኔን ለመግለጽ እወዳለሁ። 😥
31/05/2026
https://www.youtube.com/watch?v=M9892uIAE4Y
ከምኒልክ ቤተመንግስት እስከ ዘመናዊው ሙዚቃ፡ ያልተነገረው ሚስጥር | From Menelik's Palace to Modern Music: The Untold Secret ከምኒልክ ቤተመንግስት እስከ ዘመናዊው ሙዚቃ፡ ያልተነገረው ሚስጥር | From Menelik's Palace t...
Click here to claim your Sponsored Listing.
Category
Contact the business
Website
Address
Addis Ababa