Bole Woreda 14 Communication
25/05/2026
24/05/2026
"ለምርጫው ሰላማዊነት የበኩላችን እንወጣለን"
7ኛው አገራዊና ከተማ አቀፍ ምርጫ ፍፁም ሰላማዊና ዲሞክራሲያዊ ሆኖ እንዲጠናቀቅ የበኩላቸውን እንደሚወጡ የሰላም ሰራዊት አባላት ገልፀዋል።
በቦሌ ክ/ከተማ የወረዳ 14 አስተዳደር ለሰላም ሰራዊት አባላት ምርጫው ሰላማዊና ዴሞክራሲያዊ ሆኖ እንዲጠናቀቅ የሚያስችል የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠና ሰጥቷል።
ግንቦት 16/18ዓ.ም
24/05/2026
ከዛሬ የተሻገረ ለመጪው ትውልድ የሚሆን አሻራ !!
የአዲስአበባ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ አዳነች አቤቤ መርቀው ለአገልግሎት ክፍት ያደረጉት የለሚ ኮሙኒቲ ስታዲየም ከዛሬ የተሻገረ ለመጪው ትውልድ የሚተላለፍ የብልፅግና አሻራ ነው።
በቦሌ ክ/ከተማ ወረዳ 14 አስተዳደር በካፒቴን አበራ ለሚ የተሰራው የለሚ ኮሙኒቲ ስታዲየም እውነተኛ የሀገር እና የወገን ፍቅር የሚለካው ለራስ በሚኖር ሕይወት ሳይሆን፣ ለሌሎች በሚተርፍ በጎነትና ለሀገር በሚተው ዘላቂ አሻራ መሆኑን ያሳየ ህያው ምስክር ነው።
የለሚ ኮሙኒቲ ስታዲየም ከ300 ሚሊዮን ብር በላይ በሆነ ወጪ በ4,900 ካሬ ሜትር ቦታ ላይ የተገነባ ሲሆን የእግር ኳስ መጫወቻ ሜዳ፣ የመሮጫ ትራክ፣ ጥላ ያለው የተመልካች መቀመጫ፣ ለወጣቶች የስራ እድል የሚውሉ ሱቆች፣ መታጠቢያና መጸዳጃ ቤቶች፣ ጂምናዚየም እና የእቃ ማከማቻ መጋዘንን ያካተተ ነው።
ይህ ዘመናዊ ስታዲየም መለስተኛ አለምአቀፍ ውድድሮችን ለማስተናገድ የሚያስችል አቅም ያለው ነው።
ክብርት ከንቲባ አዳነች አቤቤ ስታዲየሙን መርቀው አገልግሎት ሲያስጀምሩ የለሚ ኮሚኒቲ ስታዲየምን ገንብተው ያስረከቡትን ካፒቴን አበራ ለሚን በራሴና በከተማ አስተዳደሩ ስም እያመሰገንኩ የአካባቢው ነዋሪዎችም እንኳን ደስ አላችሁ በማለት ስታዲየሙን በእንክብካቤ እንዲጠቀሙ መልዕክት አስተላልፈዋል።
ግንቦት 16/18ዓ.ም
Click here to claim your Sponsored Listing.
Category
Contact the organization
Telephone
Address
Gerji Police Station
Addis Ababa