ENAT BANK S.C.
23/03/2023
ትርታ 97.6 ኤፍኤም እና እናት ባንክ በጋራ አብሮ ለመሥራት የአጋርነት ስምምነት ተፈራረሙ።
መጋቢት 13 ቀን 2015 ዓ.ም. በትርታ 97.6 ኤፍኤም በተካሄደው ሥነ ሥርዓት የእናት ባንክ የኦፕሬሽንስ ዘርፍ ምክትል ፕሬዚዳንት ወ/ሮ ትዕግስት አባተ እና የትርታ ትሬዲንግ ኃላፊነቱ የተወሰነ የግል ማኅበር ዋና ሥራ አስፈጻሚ አቶ ዘካሪያስ ስንታየሁ አብሮ ለመሥራት የሚያስችላቸውን የስምምነት ፊርማ ተፈራርመዋል::
በዕለቱም የጣቢያው እና የባንኩ ከፍተኛ የሥራ ኃላፊዎች በሥነ ሥርዓቱ ላይ ተገኝተዋል::
ትርታ 97.6 ኤፍኤም በሕትመት ሚዲያ ብሎም በብሮድካስት ሚዲያው የረጅም ዓመት ልምድ ባላቸው ሰባት ጋዜጠኞች ዘካሪያስ ስንታየሁ፣ ደረጄ ጠገናው፣ ብሩህይሁን በላይ፣ ግርማቸው እንየው፣ ሶፎንያስ እንየው፣ ውብሸት አሰፋ እና የኋላሸት ዘሪሁን እንዲሁም በታዋቂዋ ሥራ ፈጣሪ እና የሃይብሪድ ዲዛይን ኃላፊነቱ የተወሰነ የግል ማኅበር (ራይድ) መሥራች እና ዋና ሥራ አስፈጻሚ ወ/ሮ ሳምራዊት ፍቅሩ አማካኝት ሐምሌ 3 ቀን 2012 ዓ.ም. ከመገናኛ ብዙኃን ባለሥልጣን የሥርጭት ፍቃድ አግኝቶ ሐምሌ 2 ቀን 2014 ዓ.ም. የሙከራ ሥርጭቱን እንደ ጀመረ ይታወቃል።
ከዚህ ቀደም ትርታ 97.6 ኤፍኤም ለሥርጭት እንዲበቃ እና እውን እንዲሆን የእናት ባንክ ከፍተኛ የገንዘብ እገዛ ማድረጉን የገለጹት አቶ ዘካሪያስ፣ የተፈጸመው ስምምነት የሁለቱን ተቋማት ትብብር የበለጠ እንደሚያጠናክረው ተናግረዋል። በሌላ በኩል ሚዲያውን መደገፍ ራሳችንን መደገፍ ነው ያሉት ወ/ሮ ትዕግስት፣ ትርታ 97.6 ኤፍኤም ብቁ ዜጎችን በማፍራትና አገርን በበጎ መልኩ በመገንባት ረገድ የበኩሉን አስተዋጽኦ ያበረክታል ብለው እንደሚያምኑ ተናግረዋል።
02/02/2023
ሁላችሁም ተጋብዛችኋል !!!
እናት ባንክ ከኢትዮ ሰርከስ ኢንተርቴይመንት ቡድን ጋር በጋራ በመሆን የስላንቺን ልዩ የቁጠባ ሂሳብ (ከፍተኛ የወለድ ምጣኔና ልዩ የብድር አገልግሎት የሚያስገኝ ) በስፋት ለማስተዋወቅ በልዩ ልዩ የሰርከስ ትርዒት የታጀበ ፕሮግራም በዚህ ሳምንት በእቴጌ ጣይቱ አብይ ቅርንጫፍ፣ የትነበርሽ ንጉሴ ጃክሮስ ፣ አርበኛ ከበደች ስዩም ገርጂ ቅርንጫፎች እያካሄደ ይገኛል ፡፡
ስላንቺን በልዩ መልኩ የማስተዋወቅ ዘመቻ በቀጣይ በዘሚ የኑስ ፊጋ ፣ሎሬት ሲስተር ጥበበ ማኮ ሰሚት፣ሀና ማሪያም እና ፀሀይ ይትባረክ ለቡ ቅርጫፎቻችን እንደሚካሄድ ልናሳውቃችሁ እንወዳለን፡፡
ማን እንደ እናት !
Click here to claim your Sponsored Listing.
Category
Contact the business
Website
Address
Kazanchis
Addis Ababa
18401
Opening Hours
| Monday | 08:00 - 18:00 |
| Tuesday | 08:00 - 18:00 |
| Wednesday | 08:00 - 18:00 |
| Thursday | 08:00 - 18:00 |
| Friday | 08:00 - 18:00 |
| Saturday | 08:00 - 18:00 |