Amir Ali
"አንዳንዴ መፍትሄ ከሚሰነዝሩልን አፎች በላይየሚያዳምጡን ጆሮዎች ያስፈልጉናል። በጥልቀት በመፍትሔ ሳይሆን በመደመጥ ብቻ የሚድኑ ህመሞች ብዙ ናቸው። ማቀፍ ደረጃ ያልደረሱ በመዳበስ ላይ የሚገኙ መነካካቶች ብቻ የብቸኝነትን ቆፈን ይገፋሉ።"📖
"...የሰው ልጅ አቅምና የማጥፋት ኃይሉ የተመጠነ መሆኑ በጀ እንጂ በትንሽ መከፋት ስንቱን ሲገለባብጥና ከስልፍ ውጭ ሲያተረማምስ በኖረ ነበር። የስሜት አፀፋችን ለከት አልባ መሆኑ 'ተደፈርን፤ ተዋረድን ባልን ቁጥር የአርማጌዶን ጦርነት እያስነሳንም የማንረካበት እራስ ወዳድነት ውስጣችን አለ፡፡ ምንድነን?"
"… እውነት በስሎ እስኪደርስ ከራባችሁ፣ እስኪነጋ ካላስቻላችሁ፣ የሐሰትን እሸት አስተውላችሁ ጠርጥሩ፤ ከመጠራታችሁ በፊት በልብ ጥሩ፤ የሰው ላብ ካለባችሁ ታጠቡ፤ ጫንቃህን የተጫነ ካለ ውረድ በለው፣ ከሰው ጫንቃ ላይም ከሆንክ በቶሎ ውረድ፤ ጫንቃዬን ያሳክከኛል የምትል ሁላ ጠርጥር፣ ወይ ወርዶ ያልወረደ ሸክም አለ፣ አልያም ተዘርፎ ያልተወራረደ ሐቅ ሊኖርብህ ይችላል። 📖
07/03/2025
"...ሰው ጊዜን በደቂቃና በሰዓት : በወራትና በዓመታት ሸንሽኖ : ከግድግዳው ላይ ሰቅሎ በዕጁ ላይ ጠፍሮ ሊገዛው ሊቆጣጠረው ይሞክራል ። ጊዜ ደግሞ ሰውን ከልጅነት ወደ ወጣትነት : ከጉልምስና ወደ እርጅና እያክለፈለፈ ከሞት ደጃፍ ያደርስና መቃብር ይጨምረዋል ። በክረምትና በበጋ : በፀደይና በመጸው እየተመሠለ መልኩን እየቀያየረ ሲመጣና ሲሄድ : ሲዞርና ሲፈራረቅ ... የጊዜ ጉዞ ያዙሪት'ንጅ የወደፊት አይመስልም ።"📖
Click here to claim your Sponsored Listing.
Category
Website
Address
Addis Ababa