HaqCheck

HaqCheck

Share

09/01/2025

የባንክ ቁጥሩ የአቶ ክርስትያን ታደለ ንግድ ባንክ አካውንት ኣይደለም!

ከሰሞኑ ከ15ሺህ በላይ ተከታይ ያለው የX ወይም በቀድሞ ስሙ ትዊተር አካውንት የቀድሞ የአማራ ብሄራዊ ንቅናቄ (አብን) የህዝብ ግንኙነት ሀላፊና የኢፌዲሪ ህዝብ ተወካዮች ም/ቤት አባል የሆኑትን እና በአሁን ሰዓት በእስር ላይ የሚገኙት አቶ ክርስትያን ታደለ በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ላይ ባለው አካውንታቸው ወደ 74 ሚልዮን የሚጠጋ ብር እንዳላቸው በመግለፅ የአንድ ንግድ ባንክ አካውንት ቁጥርን ከኮምፕዩተር ላይ በማንሳት አጋርቶ ነበር።

ከዚህም ባለፈ ይህ አካውንት አንድ የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አባል እንዴት ይህን ያህል ገንዘብ ሊኖረው እንደቻለ ሲጠይቅ እና ከህዝብ ትወካዮች ምክር ቤት አባላት ደሞዝ ጋር ሲያወዳድረው ተመልክተናል።

ይህ በX ላይ የተጋራው ከ46ሺህ በላይ እይታዎች ሲኖሩት ከ139 በላይ ግብረ መልሶች አሉት። በX ላይ በተጋራው ፖስቱ ላይ ያለው ምስል የተለወጠ መሆኑን ከሚያሳዩ ነገሮች አንዱ Currency በሚለው የመግለጫ ቦታ ላይ “ETB Kristian Tadele” የሚል ፅሁፍ ይታያል።

የአቶ ክርስትያን ታደለ ነው ተብሎ የተቀመጠው የንግድ ባንክ ቁጥር “1000335830378” ሲሆን ሀቅቼክ በቀላል መንገድ የአካውንት ቁጥሩን ለማጣራት ባደረገው ጥረት አካውንቱ “The Memory of Artist Hachalu Hundesa” በሚል ስም የተከፈተ እንደሆነ ማረጋገጥ ተችሏል።

ሀቅቼክ ከዚህ በፊት ይህን መረጃ በተለያዩ ጊዜያት ሲጋራ አግኝቶት የነበረ ሲሆን በወቅቱም ከ136 ሺህ በላይ ተከታዮች ባሉት የፌስቡክ ገፅ በመጋቢት 22 ቀን 2015 ዓ.ም ላይ አገኝቶት ነበር።

ይህ መረጃ በድጋሚ ከአንድ አመት እና ጥቂት ወራቶች በኋላ በድጋሚ እየተጋራ እንደሆነ ማስተዋል ችለናል። ሀሰተኛ መረጃዎች ጊዜና ሁኔታዎችን እየጠበቁ በድጋሚ ሊጋሩ ይችላሉ። ሁልጊዜም ቢሆን መረጃዎችን ከማጋራታችን በፊት እናጣራ።

03/01/2025

የበዓል ወቅቶች በቀረቡ ቁጥር በኦንላይንም ከኦንላይን ውጪም የተለያዩ ሰዎችን የማጭበርበሪያ እና የማጥመጃ መንገዶች ጥቅም ላይ ይውላሉ። በአሁኑ ጊዜ እነዚህ አጭበርባሪዎች ከሚጠቀሟቸው መንገዶች አንዱ የሰዉን ደካማ ጎን እና ስሜቱን ሊይዝ የሚችሉ ነገሮችን በመጠቀም ሲሆን ሰዎች ሽልማቶችን እና ገንዘቦችን ማግኘት ከፈለጉ በፍጥነት እንዲያደርጉ በመገፋፋት ሰዎች ውሳኔን እንዲወስኑ ሲያደርጉ እንመለከታለን።

ይህንንም ሲያደርጉ የተለያዩ ታዋቂ ፤ ሀብታም እና ተፅዕኖ ፈጣሪ ግለሰቦችን ስም እና ማንነት ከዚህም ባለፈ የታዋቂ ድርጅቶች ምልክቶችን እና ድረ-ገፆችን አስመስሎ በመስራት ታማኝ ለመምሰል ሲሞክሩ ይስተዋላል።

ከሰሞኑ በተለያዩ የፌስቡክ ገፆች ላይ ሼክ መሀመድ ሁሴን አሊ አል አሙዲን ለመጪው የገና በዓል ለኢትዮጵያውያን የ75ሺ ብር ስጦታ እየሰጡ እንደሆነ እና ሽልማቱንም ለማግኘት የተቀመጠውን ሊንክ በመጫን በድረ-ገፁ ውስጥ ያለውን ፎርም እንዲሞሉ ያስገድዳል።

ሀቅቼክ ከነዚህ መረጃዎች በመነሳት በእነዚህ የፌስቡክ ገፆች የተጋራውን ሊንክ ትክክለኛነት ያጣራ ሲሆን ኦንላይን የሚገኙ የማጣሪያ መሳርያዎችን ተጠቅመን ስንመለከት ሊንኩ የሚወስደን ድረ-ገፅ አደገኛ እና ሰዎችን ለማጥመድ የተዘጋጀ እንደሆነ ማረጋገጥ ችለናል። ከዚህ በተጨማሪም የማስፈንጠርያ ሊንኩን ሳንጫን ሊንኩ ሊወስደን የሚችለውን ድረ-ገፅ መመልከት ችለናል።

ሼክ መሀመድ ሁሴን አሊ አል አሙዲን እና ቤተሰቦቻቸው በተለያዩ ጊዜያቶች በድርቅ ለተጎዱ ወገኖች እና በበዓላት ጌዜያቶች አቅም ለሌላቸው ወገኖች እርዳታን እንደሚሰጡ ይታወቃል።

ይሁን እንጂ ሀቅቼክ በፌስቡክ ገፆቹ የተጋራውን ፖስት እና የተያያዘውን ሊንክ በማጣራት ሰዎችን የማጥመጃ እና የማጭበርበር ይዘት እንዳለው ማረጋገጥ ችሏል።

ሙሉውን ያንብቡ https://bitl.to/3Yrn

13/12/2024

ከሰሞኑን በተለያዩ ማህበራዊ ሚድያዎች በዋናነት በዩትዩብ እና ቲክቶክ ላይ በተለያዩ የሃገራችን አርቲስቶች ስም በርከት ያሉ ሙዚቃዎች በመሰራጨት ላይ ይገኛሉ። እነዚህ ሙዚቃዎች በዋናነት ፖለቲካዊ ይዘት ያላቸው ሲሆን በአጭር ጊዜ ውስጥ በርካታ ተመልካቾችን እንዲሁም ግብረ መልሶችን ማግኘት ችለዋል። ይሁንና እነዚህ ሙዚቃዎችን ጠለቅ ብለን ስንመለከታቸው በArtificial Intelligence (ሰው ሰራሽ አስተውህሎት) የተዘጋጁ ሆነው እናገኛቸዋለን። በአሁኑ ሰዓት ከቴክኖሎጂ መዘመን ጋር ተያይዞ በሰውሰራሽ አስተውልሆት የሚሰሩ ነገሮችን መለየት አስቸጋሪ እየሆነ ቢመጣም በኦንላይን የሚገኙ እና በሰውሰራሽ አስተውህሎት የተሰሩ ድምፆችን እና ቪድዮዎችን የመለያ መሳሪያዎችን ተጠቅመን ስናጣራ እነዚህ ከሰሞኑ እየተለቀቁ ያሉት ሙዚቃዎች አብዛኛዎቹ በአርቲስቶቹ የተዘፈኑ እንዳልሆኑ እና በሰውሰራሽ አስተውልሆት የተሰሩ እንደሆኑ ማረጋገጥ ችለናል።

ይህ ድርጊት ምናልባትም ገንዘብ ለማግኘት አልያም ደግሞ ፖለቲካዊ ጥቅም ለማግኘት ታዋቂ ሙዚቀኞችን ስም በመጥቀስ እና የነሱ ስራ በማስመሰል ተከታዮቻቸውን ለማንቀሳቀስ የተከናወነ ሊሆን ይችላል።

ነገርግን እንዲህ አይነቱ ሃሰተኛ ስያሜዎች በአርቲስቶቹ ስም ፣ ስራ እና ፖለቲካዊ አቋም ላይ ከሚያመጣው ተጽዕኖ ባለፈ በተከታዮቻቸው ዘንድ እምነት ማጣትን፣ የሚወዷቸውን ሙዚቀኞች ያላስተላለፉትን አቋም መያዝ እና ማንጸባረቅን ያስከትላል።

Want your organization to be the top-listed Non Profit Organization in Addis Ababa?
Click here to claim your Sponsored Listing.

Telephone

Address


Jambo Office Apartment, 8th Floor Gabon Street, Kirkos Sub-City, Woreda 03 Addis Ababa
Addis Ababa