Nehemiah Autism Center
12/06/2026
የቁሳቁሰ እና የአልባሳት ድጋፍ
🌟 ዛሬ የሴቶች እና ማህበራዊ ጉዳዮች አካቶ ትግበራ ጽ/ቤት አመራር አካላት በማዕከላችን በመገኘት ጉብኝት አድርገዋል ፤ ከጉብኝታቸውም ጎን ለጎን ማዕከላችን ከኦቲዝም ጋር ተያይዞ እየሰራ ስላለው ስራ በሰፊው ግንዛቤን ማግኘት እና ስለ ማዕከላችን የተብራራ ገለፃን ማግኘት ችለዋል ፤ ይህም ጠቃሚ ጉብኝት እየሰራን ያለውን ስራ ወደ ተሻለ ደረጃ የሚያደርስ እና ነህምያ ኦቲዝም ማዕከል ከየውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ጋር እና ከሌሎች የመንግስት ቢሮዎች እና አካላት ጋር የበለጠ አብሮ የመስራት እድልን የሚፈጥር ሆኗል።
በሴቶች እና ማህበራዊ ጉዳዮች አካቶ ትግበራ ጽ/ቤት ለማዕከላችን ድጋፍ ካደረጉት መካከል የመማሪያ ቁሳቁስ ፤ የንፅህና መጠበቂያ እቃዎች ፣ የህፃናት አልባሳት ጨምሮ ብዙዎች ተጠቃሽ ናቸው ፤ እነዚህም ቁሳቁሶች ልጆቻችንን ለማስተማር እና እነሱን ለማሰልጠን በእጅጉ የሚረዳን ሆኖ አግኝተነዋል፡፡
✨ የሴቶች እና ማህበራዊ ጉዳዮች አካቶ ትግበራ ጽ/ቤት አመራሮች እኛን በማክበር ካላችሁ ጊዜ ላይ አመቻችታቹ ማዕከላችንን በአካል ተገኝታችሁ ስለጉበኙ እና እጅግ ጠቃሚ የሚባል ጊዜን በማዕከላችን ስላሳለፋቹ የተሰማንን ደስታ እየገለፅን ላሳዩን ቀና መተባበር እና ድጋፍ በምናስተምራቸው ልጆቻችን ስም ከልብ ልናመሰግን እንወዳለን። በቀጣይም በብዙ ነገር አብረን ስለምንሰራ እጅግ ደስ ይለናል።💙
✨ ነህምያ ኦቲዝም ማዕከል ✨
Material and Clothing Support
🌟 Today, the leadership of the Women and Social Affairs Implementation Office visited our center; during their visit, they were able to gain a broad understanding of the work our center is doing related to autism and receive a detailed explanation about our center; this was a valuable visit that will take the work we are doing to a better level and create an opportunity for the Nehemiah Autism Center to work more closely with the Ministry of Foreign Affairs and other government offices and entities.
Among the support that the Women and Social Affairs Implementation Office provided to our center, there are many items including learning materials; hygiene items, and children's clothing; we have found that these materials are very helpful in educating and training our children.
✨ We would like to express our sincere gratitude to the leaders of the Women and Social Affairs Implementation Office for your kind words and for your sincere cooperation and support, expressing our joy at the time you visited our center and spent a very valuable time at our center. We look forward to working together in many ways in the future. 💙
09/06/2026
🌟 ዛሬ በኢትዮጵያ የሜክሲኮ አምባሳደር H.E Alejandro Ives Estivill Castro በማዕከላችን በመገኘት ጉብኝት አድርገዋል።
📌 አምባሳደር H.E Alejandro Ives Estivill Castro ማዕከላችን ከኦቲዝም ጋር ተያይዞ እየሰራ ስላለው ስራ በተላያዩ ሚዲያ አውታሮች ወይንም መድረኮች ከመስማት ባለፈ ወደ ግቢያችን በአካል በመምጣት ጠቃሚ የሚባል ጉብኝትን ማድረግ እና ስለ ማዕከላችን የተብራራ ገለፃን ማግኘት ችለዋል ፤ ይህም ጠቃሚ ጉብኝት እየሰራን ያለውን ስራ ወደ ተሻለ ደረጃ የሚያደርስ እና ለነህምያ ኦቲዝም ማዕከልም የበለጠ አብሮ የመስራት እድልን የሚፈጥር ሆኗል።
አምባሳደር H.E Alejandro Ives Estivill Castro እኛን በማክበር ካሎት ጊዜ ላይ አመቻችተው ማዕከላችንን በአካል ተገኝተው ስለጉበኙ እና እጅግ ጠቃሚ የሚባል ጊዜን በማዕከላችን ስላሳለፉ የተሰማንን ደስታ እየገለፅን ላሳዩን ቀና መተባበር እርሶንም መላው የሜክሲኮ ኤምባሲ በኢትዮጵያ ሰራተኞች በምናስተምራቸው ልጆቻችን ስም ከልብ ልናመሰግን እንወዳለን። በቀጣይም በብዙ ነገር አብረን ስለምንሰራ እጅግ ደስ ይለናል።💙
✨ ነህምያ ኦቲዝም ማዕከል ✨
🌟 Today, the Mexican Ambassador to Ethiopia, H.E Alejandro Ives Estivill Castro, visited our center.
📌 Ambassador H.E Alejandro Ives Estivill Castro, in addition to hearing about the work our center is doing related to autism through various media outlets or forums, was able to visit our premises in person and get a detailed explanation about our center; this valuable visit will take the work we are doing to a better level and create an opportunity for Nehemiah Autism Center to work together more.
Ambassador H.E Alejandro Ives Estivill Castro, we would like to express our joy and gratitude for the time you have taken to visit our center in person and spend a very valuable time at our center. On behalf of the entire staff of the Mexican Embassy in Ethiopia, we would like to thank you for your sincere cooperation. We are very happy to work together on many things in the future. 💙
✨ Nehemiah Autism Center ✨
31/05/2026
🌟 ዛሬ በማዕከላችን አዘጋጅነት ተካሂዶ የነበረው በአይነቱ ለየት ያለ ከኦቲዝም ጋር ለሚኖሩ ልጆቻችን ለወንድሞቻቸው አና ለእህቶቻቸው የተዘጋጀ ስለ ኦቲዝም እና ከኦቲዝም ጋር ተያይዞ መታወቅ ስላለባቸው ወሳኝ ወሳኝ ነገሮች ላይ ሰፊ ስልጠና ተሰቷል። 🌟
📌 ይህም ስልጠና የልጆቻችን ወንድሞች አና እህቶች ስለ ዘርፉ በቂ የሚባል ግንዛቤን እንዲያገኙ ከማድረግ ባለፈ እነሱም ከኦቲዝም ጋር ተያይዞ ስለምንሰራው ስራ ከጉናችን ሆነው ጉልህ ሚና እንዲጫወቱ የሚያደርግ ነው ፤ ይህም ስልጠና ወ/ሮ ቆንጂት ሞገስ የማልድ ትምህርት ቤት መስራችና የሳርቤት ቅርንጫፍ ዳይሬክተር እና በማዕከላችን ሄድ-ሳይካትሪስት ራሄል አበራ ተሰቷል።
✨ በመጨረሻም ጥሪያችንን አክብራችሁ የተገኛችሁ የልጆቻችን እህት እና ወንድሞች እንዲሁም እነርሱን በመላክ የተባበራችሁን ወላጆች እና ስልጠናውን በሚገባ እንድናከናውን ካማረ የመሰብሰቢያ አዳራሽ ጋር የፈቀዳችሁልን ስካይ-ላይት ሆቴል እጅግ እያመሰገንን...💙💙
🤝 ከሁሉም በላይ ደግሞ ስልጠናውን እጅግ በሚያምር አቀራረብ ያቀረቡልንን ወ/ሮ ቆንጂት ሞገስ የማልድ ትምህርት ቤት መስራችና የሳርቤት ቅርንጫፍ ዳይሬክተር እና የማዕከላችን ሄድ-ሳይካትሪስት ራሄል አበራን ከልብ ከልብ እናመሰግናለን።💙💙
🌟 Today, our center organized a unique training for our children living with autism, and their brothers and sisters, on autism and important things to know about it. 🌟
📌 This training will not only help our children's brothers and sisters gain sufficient understanding of the field, but also help them play a significant role in our work related to autism; this training was conducted by Ms. Konjit Moges, founder of Mald School and director of Sarbet branch, and Rahel Abera, head psychiatrist at our center.
✨ Finally, we would like to thank the sisters and brothers of our children who honored our invitation, as well as the parents who supported us in sending them, and the Sky-Light Hotel for allowing us to conduct the training in a beautiful meeting room...💙💙
🤝 Above all, we would like to express our sincere gratitude to Ms. Konjit Moges, the founder of Mald School and the director of the Sarbet branch, and our center's head psychiatrist, Rahel Abera, who presented the training in a very beautiful way.💙💙
26/05/2026
🌟 አዳማ በሚገኘው በቤተል ቺልድረንስ ሆም ኤንድ ኦቲዝም ማዕከል አዘጋጅነት ተካሂዶ በነበረው የኦቲዝም ቀን ግንዛቤ ማስጨበጫ መርሐግብር ላይ ስለተገኘን እና በፕሮግራሙም ከመስራቿ ከ ወ/ሮ ገነት ንጉሴ የእውቅና የምስክር ወረቀት ስለተሰጠን ትልቅ ክብር ይሰማናል።🌟
ቤተል ቺልድረንስ ሆም ኤንድ ኦቲዝም ማዕከል ከኦቲዝም ጋር ለሚኖሩ ልጆች መልካም የሚባል ሁኔታዎችን በመፍጠር እና ከዛም ባለፈ እነርሱን እና ወላጆቻቸውን በማገዝ ላይ ያለ ማዕከል ነው ፤ በዚህ ከማዕከላችን ጋር በብዙ አብረን እየሰራን ስላለ ደስ ይለናል። ✨✨
በዚህም መርሀግብር ላይ አክብራችሁ ስለጠራችሁን ከልብ እናመሰግናለን።💙
🌟 We are honored to have attended the Autism Awareness Day program organized by Bethel Children's Home and Autism Center in Adama and received a certificate of recognition from its founder, Ms. Genet Niguse. 🌟
Bethel Children's Home and Autism Center is a center that creates positive conditions for children living with autism and beyond that, helps them and their parents; we are happy to have worked with our center in this regard. ✨✨
We sincerely thank you for inviting us to this program.💙
'sHomeandAutismCenter
Click here to claim your Sponsored Listing.
Contact the organization
Telephone
Website
Address
Https://www. Google. Com/maps/place/Nehemiah+Autism+Center/@8. 9743853, 38. 7441869, 14z/data=, 4m5, 3m4, 1s0x0:0x8fe79cdb01ddd566, 8m2, 3d8. 9875471, 4d38. 7576194
Addis Ababa
62944
Opening Hours
| Monday | 09:00 - 17:00 |
| Tuesday | 09:00 - 15:00 |
| Wednesday | 09:00 - 15:00 |
| Thursday | 09:00 - 15:00 |
| Friday | 09:00 - 15:00 |