Brother Josh Temechu

Brother Josh Temechu

Share

13/06/2023

"ሣራም፦ እግዚአብሔር ሳቅ አድርጎልኛል፤ ይህንንም የሚሰማ ሁሉ በእኔ ምክንያት ይስቃል አለች።" ኦሪት ዘፍጥረት 21: 6

ሳቅ አለ ከፊትህ

የተዘጋ ቢመስል ነገር ያከተመ
ጌታም "የዘነጋህ" ተስፋህ የሰጠመ
በንስር ክንፍ ቢበር ዘመን አንተን ጥሎ
መጽናናትን ስትሻ የሀዘን ቢሆን ውሎ
ሚረዳህ ብታጣ የልብህን ስቃይ
ለወሬም ባይመች ፍጹም ያንተ ጉዳይ
ጥበቃህ አጥብቆ ከምሬት ጋር ቢያስርህ
የስጋህን ፈቃድ ቢያመታትር እግርህ
ልብ በል ወንድሜ የተስፋ ቃል ሰጪው
ታማኝ ነው አትስጋ አታስብ ለመጪው
ውስጥህ ይደገፈው ዳር አለው ለሊትህ
ያለህን ያደርጋል ሳቅ አለ ከፊትህ::

"ክብር ለእግዚአብሔር ይሁን!!!"
ጃሽ ተመቹ

Want your place of worship to be the top-listed Place Of Worship in Addis Ababa?
Click here to claim your Sponsored Listing.

Website

Address


Addis Ababa
00252