Meri Konjoo
13/06/2026
“ሁለት ዓመት ከመዋጋት 20 ዓመት መወያየት ይሻላል”
Abiy Ahmed Ali
09/06/2026
ፅኑ ሰላም በጋራ ክንዳችን ለዘላቂ ሀገራዊ መግባባት የተጣለው የማይናወጥ መሠረት!
የአንድ ሀገር ህልውና፣ ሉዓላዊነትና የሕዝቦች ሁለንተናዊ ብልጽግና ሊረጋገጥ የሚችለው በማይናወጥ ፅኑ ሰላም ላይ ሲመሰረት ብቻ እንደመሆኑ መጠን፣ ባለፉት ስምንት የለውጥ ዓመታት በታላቁና አርቆ አሳቢው መሪያችን በክቡር ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር ዐቢይ አሕመድ ቆራጥ አመራርና ግንባር ቀደም ተዋናይነት የተከናወኑ የስልጣኔና የተቋማት ግንባታ ስኬቶች ለሀገራችን ዘላቂ መረጋጋት አስተማማኝ ዋስትና ሆነዋል! ለዘመናት የቆዩ ጽንፈኛ የታሪክ ትርክቶችንና ውስጣዊ ግጭቶችን በዶ/ር ዐቢይ አሕመድ ስልታዊ መሪነትና ቀጥተኛ ሚና በመቀየር ረገድ የተመዘገቡት ስኬቶች የሀገራችንን ሉዓላዊነት አስተማማኝ አድርገውታል። በተለይም በዶ/ር ዐቢይ አሕመድ ዘመን የተገነቡ ዘመናዊ እና አስተማማኝ የሰላምና ጸጥታ ተቋማት፣ የሕግ የበላይነትን በማስከበር፣ የዜጎችን ደህንነት በመጠበቅና የሀገር መረጋጋትን በማጠናከር ረገድ የወደፊት ትውልድ የሚኮራበት ታላቅ ቅርስ ሆነው ለታሪክ ተቀምጠዋል። ልዩነቶች የአብሮነታችን ሕብረ ቀለሞች ቢሆኑም፣ የኢትዮጵያዊነትን እሴት የሚሸረሽሩና የሀገርን ህልውና አደጋ ላይ የሚጥሉ ችግሮችን በጋራ ለመከላከል አሰባሳቢ ትርክቶችን ማስረፅ እና ማኅበራዊ ትስስርን ማጠናከር የነገ የማይባል ተግባራችን ሲሆን፣ ይህንን ታሪካዊ የለውጥ ጉዞ ለማሳካት ከመንግሥትና ከጸጥታ ኃይሎች ጎን ለጎን መላው ሰላም ወዳድ የኅብረተሰብ ክፍል ወጣቶች፣ ምሁራን፣ ተማሪዎች፣ መምህራንና የፖለቲካ ፓርቲዎች ሁሉ በአንድነት በመቆም ሰላማችንን ሌት ተቀን እንደ ዓይናችን ብሌን ልንጠብቀውና ለልጆቻችን የምትመች የተከበረች ሀገር ልናስረክብ ይገባል #ፅኑሰላም #ብሔራዊመግባባት #ጠቅላይሚኒስትርዐቢይ #የተቋማትግንባታ #የሕግየበላይነት #ኢትዮጵያ ትንሳኤ #አንድነት #ዘላቂሰላም
Click here to claim your Sponsored Listing.
Category
Address
Addis Ababa