Irreecha Finfinnee

Irreecha Finfinnee

Share

01/10/2025

ኢትዮጵያ በብዝሃ ማንነት፣ ባህልና እሴቶች የደመቀች ፣ በህብረ ብሄራዊነት የተጋመደች፣ ወንድማማችነትን ከፍ አድርጋ ያፀናች ታላቅ ሀገር ናት።

የመስከረም ወር ለኢትዮጵያውያን የአዲስ ዓመት ተስፋ የሚሰነቅበት እና በርካታ ሀይማኖታዊና ባህላዊ በዓላት የሚከበሩበት ልዩ ወር ነው።

ኢሬቻ የኦሮሞ ህዝብ ከዘመን ወደ ዘመን በሰላም ያሸጋገረዉን አምላኩን የሚያመሰግንበትና መጪዉን ዘመን የሰላምና የደስታ እንዲሆንለት የሚለምንበት በዓል ነዉ።

ኢሬቻ የአንድነት፣ የሰላም እና የወንድማማችነት ምልክት በመሆኑ ከኦሮሞ ህዝብ በተጨማሪ በርካታ የኢትዮጵያ ብሄር ብሄሰቦች አብረው የሚያከብሩት፣ ለሰላምና ወንድማማችነት ከሚያበረክተው አስተዋጽኦ የተነሳ በአለም አቀፍ ደረጃ ከማይዳሰሱ ቅርሶች መካከል በዩኔስኮ የተመዘገበ የሁላችንም ኢትዮጵያውያን በዓል ነዉ ።

በኢሬቻ ቂም በይቅርታ ይሻራል፣ ጨለማ ለብርሀን እጁን ይሰጣል፣ የተለያየ ይገናኛል፣ የተጣላ ይታረቃል፣ ጥላቻ ቦታውን ያጣል ወንድማማችነት፣ እህትማማችነት እና አብሮነት ይነግሳል።

ብልጽግና የአደባባይ በዓላት ለሀገር ገፅታ ያላቸውን ጉልህ ሚና በመረዳት ባማረና በደመቀ ድባብ በሰላም ይከበሩ ዘንድ በትብብር ይሰራል። ሰላም ለልማት፣ ለዜጎች ዘላቂ ተጠቃሚነትና አብሮነትና ለሁለንተናዊ ዕድገት መሰረት የሆነ ወሳኝ ጉዳይ በመሆኑ የሰላም አማራጮችን ቅድሚያ እየሰጠን የአደባባይ በዓላቱን ለሀገር ገፅታ ግንባታ ማዋል ወሳኝ ነው።

26/09/2024

ለመላው የክርስትና እምነት ተከታዮች በሙሉ እንኳን ለብርሃነ መስቀሉ በሰላም አደረሳችሁ!

መስቀል ድንቅ ሃይማኖታዊ ስርዓት ፤ እሴትና ታይቶ የማይጠገብ ትውፊታዊ ይዘቶችና ተፈጥሯዊ መስህብ ገፅታዎች የተላበሰ የሀገር መገለጫና ኩራት ከሆኑ በዓሎቻችን አንዱ ነው፡፡

በርግጥ መስቀል ፍቅር ነው፡፡ መስቀል እየሱስ ክርስቶስ የሰውን ልጅ ሁሉ ያለዘር፣ ያለቀለም፣ ያለፆታ፣ ያለሀይማኖትና ያለልዩነት መውደዱን ህይዎቱን በመስጠት ወደር የማይገኝለትን ፍቅርን የገለፀበት ነው፡፡
ስለዚህ መስቀል የፍቅር፣ የሰላምና የአብሮነት በዓል ነው፡፡ የመስቀል ደመራ በዓል የጨለማው በብረሃን መሸነፍ ማሳያም ነው::

ስለሆነም ይህንን በዓል ስናከብር በፍቅር እርስበእርስ በመተሳሰብ ለዘላቂ ሰላማችን መረጋገጥ ስራችንም እየሰራን፣ ጀግኖቻችንን እያከበርን፣ ደጀንነታችንን የበለጠ እያረጋገጥን፣ አንድነታችንን እያጸናን፤ እንደ ደመራው ደምቀን ጨለማ በሆነብን ሁሉ ላይ እያበራን በአሽናፊነት እንቀጥል፡፡
አቶ ተድላ ታምራት
የየካ ወረዳ 09 ዋና ሥራ አስፈፃሚ

Want your organization to be the top-listed Government Service in Addis Ababa?
Click here to claim your Sponsored Listing.

Telephone

Website

Address


Addis Ababa