Health talk

Health talk

Share

31/05/2026

▶️ሄፓታይተስ 'ሲ' የጉበት ቫይረስ ኢንፌክሽን በጊዜ ከታወቀ እንደሚታከም ያውቃሉ?

📌ሄፓታይተስ ሲ ኢንፌክሽን በቫይረስ ሳቢያ የሚመጣ የጉበት በሽታ ነው።
🔷ይህ በቫይረሱ ምክንያት የሚመጣው የጉበት ጉዳት ቋሚ ወይም ጊዜያዊ ሊሆን ይችላል።
📌ሄፓታይተስ ሲ ቫይረስ የሚተላፈው:- በደም ንኪኪ ነው ፤ ይህም ስለት ያላቸውን መሳሪያዎች እና ሲሪንጅ ጥንቃቄ በሞላበት መንገድ ባለመጠቀም ሊከሰት ይችላል።

📌የ Acute Hepatitis C ምልክቶች ፦
1-ትኩሳት
2-ድካም
3-አይን እና ቆዳ ቢጫ መሆን እና የጡንቻ ህመም ሲሆን፤ ነገር ግን ረዘም ላለ ጊዜ የሚቆይ(Chronic) የሄፓታይተስ ሲ ኢንፌክሽን ምልክት ሚታየው ቫይረሱ ጉበትን በከፍተኛ ሁኔታ ከጎዳ በኋላ ነው፤ ከታች የተዘረዘሩት ዋና ዋናዎቹ ናቸው👇
1-በቀላሉ መድማት
2-ድካም
3-አይን እና ቆዳ ቢጫ መሆን
4-የሽንት መጥቆር
5-የቆዳ ማሳከክ
6-የሆድ እና እግር ማበጥ
7-ክብደት መቀነስ
8-የምግብ ፍላጎት ማጣት ናቸው።

#

27/05/2026

ለመላው የእስልምና እምነት ተከታዮች በሙሉ እንኳን ለዒድ አል-አደሃ (አረፋ) በዓል በሰላም አደረሳችሁ!

🌙መልካም በዓል!

16/05/2026

የወር አበባ ኡደት መዛባት በርካታ ምክንያቶች አሉት፤ ከእነዚህም ውስጥ፦
➲ጭንቀት

➲የሆርሞን መዛባት

➲ፖሊሲስቲክ ኦቫሪ ሲንድሮም/ PCOS)
/
➲የታይሮይድ ሆርሞን ችግሮች

➲የማሕፀን እጢዎች ለምሳሌ:-ፋይብሮይድ

➲ኤንዶሜትሪዮሲስ

➲ኢንፌክሽኖች ሊሆኑ ይችላሉ ስለዚህ ፤

➲ ከመጠን በላይ የሆነ የወር አበባ ደም መፍሰስ
➲ለረጅም ጊዜ የሚቆይ የወር አበባ
➲በወር አበባ መሀል የሚከሰት የማህፀን መድማ...፤ የመሳሰሉ ምልክቶች ካሉ ወዲያውኑ ወደ ጤና ተቋም በመሄድ ህክምና ማግኘት አለብዎት።

#የወርአበባመዛባት #ዶክተር #የጤናምክር

13/05/2026

🚨የእርግዝና አደገኛ ምልክቶች🚨

1- በማህፀን በኩል መድማት
2-ከባድ እና የማይቆም ራስምታት
3- የእይታ መስተጓጐል : ብዥታ፣ ጭልምልም ማለት..
4-ወደ ታች የመግፋት ስሜት
5-የፅንስ እንቅስቃሴ ከወትሮው በተለየ ሲቀንስ
6-የእንሽርት ውሃ መፍሰስ ሲሆኑ እነዚህ ምልክቶች ሲሰሙሽ ወዲያውኑ ወደ ጤና ተቋም መሄድ አስፈላጊ ነው።

#የጤናምክር

12/05/2026

⁉️ራስምታት አደገኛ ነው ሚባለው መች ነው?

➲በድንገት የጀመረ እና ከፍተኛ ህመም ያለው ሲሆን
➲ከዚህ በፊት ከሚሰማዎት በላይ እጅግ ከባድ ከሆነ ('እንዲህ ያለ ራስምታት ገጥሞኝ አያውቅም'..)

➲የአንጎል እና ነርቭ ስርዓት መዛባት ሲከተለው : ለምሳሌ :- የእጅ/እግር ጡንቻ መዝነፍ/መድከም እና መደንዘዝ፣ ባላንስ መሳት፣ ለመናገር መቸገር

➲ትኩሳት ፣ የአንገት መገተር እና የቆዳ ሽፍታ አብሮት ከተከሰተ

➲የእይታ ችግር ሲጨመርበት..

09/05/2026

የሚሰማንን አይደለንም

ድካም ፣ ድባቴ ፣የስሜት መዋዠቅ ሰው የመሆናችን ምልክት እንጂ ድክመት አርገን መቁጠር የለብንም፤

ብዙ ጊዜ እንደዚህ አይነት የስነልቦና እክል ሲገጥመን ከመናገር ይልቅ
፦ራስን ለማግለል
፦ራስን ለመጉዳት
፦ተስፋ በመቁረጥ..ውስጥ እንደበቃለን፣ ራስን ከችግሮች ጋር አንድ ማድረግ /identify/ መፍትሄ ሊሆን አይችልም ም/ቱም 'እኛ ችግሮቻችንን አይደለንም'!

🌠ምክር ወይም ድጋፍ መጠየቅ ደካማነት አይደለም!
🌠ጭንቀት ፣ድባቴ እና ድብርት እንደማንኛውም የስኳር እና የደምግፊት እክሎች መታከም ይችላል!

#የሀኪምምክር #ስለጤና

08/05/2026
08/05/2026

Health Talk
#የሀኪምምክር #ስለጤና

Want your business to be the top-listed Health & Beauty Business in Addis Ababa?
Click here to claim your Sponsored Listing.

Address


Addis Ababa