Ethio Health Tips

Ethio Health Tips

Share

06/09/2021

ቴምር በርካታ የጤና ጠቀሜታዎች አሉት።
1) ስብና ኮልስትሮል፡ ከየትኛውም የኮልስትሮል ዓይነቶች የጸዳና በጣም
አነስተኛ የስብ መጠን ያለው መሆኑ ክብደት መቀነስ ለሚፈልጉ ተመራጭ ነው፡፡
2) ፕሮቲን፡ ቴምር በፕሮቲንና አስፈላጊ ማዕድናት የበለጸገ መሆኑ ለሰውነት
እጅጉን ጠቃሚ ያደርገዋል፡፡
3) ቫይታሚን፡ በቫይታሚን የበለጸገ ነው ቴምር፡፡ ከቫይታሚን ዓይነቶች ቢ1፣
ቢ2፣ ቢ3፣ ቢ5፣ ኤ1 እና ሲ ንም አካትቶ ይዟል፡፡
4) ሀይል እና ጉልበት፡ ቴምር ቀላል የማይባል የሀይል ክምችት ስላለውም ንቁና
በሀይል የተሞላን እንድንሆን ያስችለናል፡፡
5) ፖታሲየምና ካልሲየም፡ ቴምር የፖታሲየም ክምችቱ ከፍተኛ ነው፡፡ ይህም
በልብ በሽታ እንዳንጠቃና አካላችን ውስጥ ያለው የኮልስትሮል መጠን
እንዲቀንስ ይረዳል፡፡ ቴምር በአንጻሩ አነስተኛ የሶዲየም መጠን ነው ያለው፡፡
ብዙ ፖታሲየምና ትንሽ ሶዲየም ደግሞ ለጤናማ የነርቭ ስርዐት ወሳኝ ነው፡፡
6) ብረት፡ ቴምር በብረትና በፍሎሪን የበለጸገ መሆኑ ደግሞ ብረቱ የብረት
ማዕድን እጥረት ላለባቸው ሰዎች፣ ፍሎሪኑ ደግሞ ጥርስን ከመበስበስ
ይከላከላል፡፡
7) ድርቀት፡ ለድርቀትም ቢሆን ውሀ ውስጥ የተነከረ ቴምር መመገብ ፍቱን
እንደሆነ ይታወቃል፡፡
ሰውነትን ማጽዳት፡ በአልኮል መጠጣት ሳቢያ ሰውነት ውስጥ
የሚከማቸውን መርዛማ ኬሚካሎች ከሰውነታችን ውስጥ በማስወገድም
ይረዳል።
9) ካንሰር እና የዓይን ችግር፡ የዓይን ህመም ችግርንና የሆድ ነቀርሳ (ካንሰር)ን
ለማከምም ብቃት እንዳለው ይታወቃል ፡፡
10) (የቆዳ ችግር) ቴምር የቆዳ ችግሮችን በማስወገድም መልካም ዝና አለው፡፡
ጸጉርን በማፋፋት የጸጉር መሳሳትንም ይከላከላል፡፡
በርከት ያሉ ቪታሚኖችን እና ሚኔራሎች በመያዙ ለጤናችን በርካታ ጠቀሜታዎች
እንዳሉት ይነገርለታል።
ሀይል ሰጪ፣ ፋይበር፣ እንዲሁም ካልሺየም፣ አይረን፣ ፎስፈረስ፣ ሶዲየም፣
ፖታሲየም፣ ማግኒዚየም፣ እና ዚንክ ሚኔራሎች በቴምር ውስጥ የሚገኙ በመሆኑ
ቴምርን ለጤና ጠቃሚ ያደርጉታል።
ስለዚህም ቴምርን አዘውትረን መመገብ ለጤናችን ከሚሰጠው ጠቀሜታዎች
ውስጥም፦
11.የሆድ ድርቀትን ይከላከላል።
ቴምር በባህሪው የማለስለስ ባህሪ ስላለው ምግብ በአንጀታችን ውስጥ በቀላሉ
እንዲዘዋወር በማድረግ የሆድ ድርቀት ለመከላከል ይረዳል። ለዚህም ይረዳን
ዘንድ ቴምሩን በውሃ
ውስጥ ዘፍዝፈን በማሳደር ጠዋት ላይ መመገብ ይመከራል።
12.ለአጥንት ጤንነት እና ጥንካሬ
በቴምር ውስጥ የሚገኙት ሚኔራሎች ለአጥንታችን ጥንካሬ እና ጤነነት እጅጉን
ጠቃሚ እንደሆኑ ይነገራል። ቴምር እንደ ሴሌኒየም ማንጋኒዝ፣ ኮፐር እና
ማግኒዚየም ማእድናትን በውስጡ በመያዙም ለአጥንት ጤናማ እድገት እና
ጥንካሬ ጠቃሚ ነው።
13.ደም ማነስን ይከላከላል
ቴምር በውስጡ በያዘው ከፍተኛ የምግብ ማእድናት ንጥረ ነገሮች ክምችት
የደም ማነስ ችግር ላለባቸው ሰዎች እጅጉን ጠቃሚ ነው።
14.አለርጂን ይከላከላል
ቴምርን ከሌሎች ለየት የሚያደርገው አለርጂን ለመከላከል የሚረዳውን ሰልፈር
ንጥረ ነገር በውስጡ በመያዙ ነው። ስለዚህም ቴምርን አዘውትረን የምንመገብ
ሰዎች ለተለያዩ አይነት አለርጂዎች የመጋለጥ እድላችን እጅጉን እንዲቀንስ
እንደሚያደርገው ይነገርለታል።
15.ለነርቭ ጤንነት
በቴምር ውስጥ የሚገኙት ቪታሚኖች የተስተካከለ እና ጤናማ የነርቭ ስርዓት
እንዲኖረን ስለሚያደርግም ለጤናችን ጠቃሚ ያደርገዋል።
16.ለልብ ጤንነት
ቴምር ለልባችን ጤንነት በርካታ ጠቀሜታዎች ስላሉት ተመራጭ ያደርገዋል።
ቴምር የልብ ጤንነትን ይጎዳል የሚባለውን የኮሌስቴሮል መጠን የመቀንስ
እቅም ስላለው ለድንገተኛ የልብ ህመም እንዳንጋለጥ በመርዳትም ለልባችን
ጤንነት

16/06/2021

የሽንትዎ ቀለም ስለሰውነትዎ ጤና ምን ይነግርዎታል?
ሽንት ኩላሊት ደምን አጣርቶ የሚያስወጣው ክፍል ሲሆን 95%
ውሀ 5% ኤሌክትሮላይቶች እና ቆሻሻዎች ናቸው ።
ጤናማ እና በቂ ፈሳሽ በሚዎስዱበት ጊዜ ሽንትዎ ብዙ የጎላ
ቀለም በሌለው እና ነጣ ያለ ቢጫ ቀለም መካከል ነው፡፡በቂ
ፈሳሾችን በማይወስዱበት ጊዜ ሽንትዎ ይበልጥ የተከማቸ ሲሆን
ወደ ጠቆር ያለ ቢጫ ወይም የዓምበር ቀለም ይለወጣል ፡፡
ከዚህ በተጨማሪ የሽንት ቀለም እና መጠን እየዎሰዱ ያሉትን
የውሀ መጠን ፣ ምግብ ፣ ቫይታሚን ጠቋሚ ነው።
የተወሰኑ ምግቦች ፣ አንቲባዮቲኮች ፣ የህክምና ሁኔታዎች እና
ቀለሞች እንዲሁ ለጊዜው የሽንት ቀለም ይቀይራሉ ፡፡ ከዚህ
ቀጥሎ የተለያዩ የሽንት ቀለም አይነቶች እና ምክንያቶች እናያለን

1. በጣም ነጭ ከሆነ ከመጠን በላይ ውሀ እየጠጡ እንደሆነ
ያመለክታል ። ይህም የተለያዩ በደም ውስጥ የሚገኙ ንጥረ
ነገሮችን በተለይም ፓታሽየም እና ሶድየም መጠናቸው
እንዲያንስ ያደርጋል ይህም የልብ ጡንቻን ይጎዳል ።
2. ጥቁር ቢጫ - ይህም በቂ ውሀ እየወሰዱ እንዳልሆነ ወይም
ኬቶን በሽንት ውስጥ መኖር ሊሆን ይችላል ። በቂ ውሀ
አለመውሰድ ደግሞ ለኩላሊት ጠጠር ፣ የሰውነት ፈሳሽ መቀነስ
፣ የኤሌክትሮላይት መዛባት ያስከትላል ። ኬቶን የሚፈጠረው በቂ
የሆነ ስኳር (glucose ) ሳያገኝ ሲቀር እና ቅባት (fat)
ለሴሎች ጉልበት ሲጠቀም ነው ። ይህም በሽንት መልክ
ይወጣል ። ከፍተኛ የኬቶን መጠን አደገኛ የስኳር በሽታ ጉዳትን
(DKA) ተከትሎ ሊመጣ ይችላል ። አነስተኛ መጠን ከሆነ
ለረጅም ጊዜ ካልተመገብን ሊከሰት ይችላል ።
3. ደማቅ ቢጫ - ከበቂ በላይ ሰው ሰራሽ ቫይተሚን ቢ
እየወሰዱ ከሆነ
4. ቀይ- ይህ የሚፈጠረው ደም በሽንት ውስጥ ሲኖር ነው ።
ይህም በኩላሊት ጠጠር ፣ የኩላሊት እና የሽንት ፊኛ ኢንፌክሽን
፣ የፕሮስቴት እጢ ካንሰር ፣ የኩላሊት ካንሰር ፣ ከባድ ስፓርት
5. ጥቁር ብርቱካናማ / ቡናማ - የጉበት ችግር ያመለክታል ።
የጉበት ፣ የሀሞት ቀረጢትና የቱቦዎች ችግር ተከትሎ የቢሊሩቢን
በደም ውስጥ መብዛት ጋር ተያይዞ የሚከሰት ነው።
6. ሀምራዊ - አነስተኛ ደም በሽንት ውስጥ ሲኖር ወይም ቀይ
ስር ከበላን
7. ሰማያዊ - የካልስየም መብዛት /hypercalcemia
7. አረፋ ካለ - ፕሮቲን በሽንት ውስጥ መኖር ፤ ይህም የኩላሊት
ቁስለት ፣ የኩላሊት ጠጠር ፣ የልብ እና የኩላሊት መድከም ፣
የተለያዩ የካንሰር አይነቶች
8. ብዙ የሚሸኑ ከሆነ - በሽንት ውስጥ የስኳር መኖር ነው ፤
ይህም የስኳር በሽታ ያመለክታል ።
መልካም ጤና!!!

April 1, 2021 05/04/2021

https://youtu.be/7FZcRWq3SLE
don't forget subscribe 👆👆👆

April 1, 2021

Want your business to be the top-listed Beauty Salon in Addis Ababa?
Click here to claim your Sponsored Listing.

Category

Telephone

Address


Addis Ababa