ABBA Heylemelekot
24/11/2025
፨ጾማችን ምን ይምሰል???
*ንጹም ጾመ ወናፍቅር ቢጸነ
ወንትፋቀር በበይናቲነ(ቅ/ያሬድ
*ጾምን እንጹም ባልንጀራችነንም እንውደድ
እርበርሳችንም እንዋደድ( እንተሳሰብ)ይለናል ሃይማኖተኛው ሊቅና ጻድቅ ኢትዮጵያዊ ቅዱስ
*አዋጁ ይኽ ነው ጾሙንም ጀመርነው
ግን እኛ እንዴት ነው የምንጾመው?ሊቁ እንደነገረን
ከባልንጀሮቻችን ጋራ ተስማምተን ተግባብተን እርስበርሳችን ተፋቅረን ከቤተሰቦቻችንስ ጋር ተሳስበን ተከባብረንና ተዛዝነን ነው?
ወይንስ ዝም ብለን በተለምዶ ነው የምንጾመው?
መጠየቅ አለብን እኮ ሰዎች እንደ ባለአእምሮ
በያለንበት እንደተቋም ምን ላይ ነው ያለነው?
እንደ ሀገርስ እንዴት እየኖርን ነው ?
አሁን ለመተርጎም የሚያስቸግር ሁኔታ ነው ያለው
አንባ ጓሮ የበረከተበት ዘመን ፈታኝና መዘዘኛ
ሃይማኖተኛው ጠበኛ ፖለቲከኛው ጦረኛ
በአነስተኛ ኑሮ ውስጥ ያለው ቧልተኛ
ሥራየ ብሎ ነገር እሚያቀሳስር ሟርተኛ
በተለያየ መንገድ ኅነት ያስጨነቀው ወሬኛ
ልዩነትን የበለጠ የሚያሰፋ ቁስል የሚፈጥር እንጅ ፈዋሽ አጽናኝ ያልሆነ የተሰበሰበውን የሚበትን ተስፋ ያለውን ተስፋ የሚያስቆርጥ ሰላማዊውንም አእምሮ የሚበጠብጥ ክፉ ወሬ እያወራን እየሰማን?
እንዴት ነው መጾም ያለብን?
ሁለንተናችን እንዲጾም ወስነን ነው?
እንደሱ ከሆነ ጾማችን ውጤታማ ይሆናል
እንደ አባቶቻችን ጩኸታችን መልስ ያስገኛል
ይኽን ጾም የጾሙት አበው ነቢያት ሲሆኑ የመከራውን ዘመን አርቀውቀታል አሳልፈውበታል
የተነገረውን ተስፋም እውን ሆኖ አይተውበታልና
እኛም እራሳችነን ከክፉ ነገር ሁሉ ቆጥበንና አርቀን
አእምሮአችነንም ሰብስበን በክት ልቡና ከጾምነው
የምንሻውን ውጤት እናገኝበታለን።
ካልሆነ ግን ከንቱ እንደክማለንና ክርስቲያናዊ ምክሬ
እንደ ሊቁ ምክርም እንመጽሐፍ ቃልም እንጹመው
01/10/2025
መኑ ሰብእ ዘየሐዩ ወኢይሬእያ ለሞት።
ሕያው ኾኖ የሚኖር ሞትንስ የማያይ ማን ነው?እንዳለ ባለቅኔው ነቢይ ሊቅነት ፣ደግነት፣ርኅራኄ፣ ትዕግስት፣ጾም፣ተኀራሚነት፣ገድልና ትሩፋት የማይገድበው አዳም ያመጣው ሞት ከኄራን ተሐራምያን ምሁራን አንዱን ሃይማኖት ያጸኑ በምግባር የተቃኑ 318ቱ ሊቃውንት በተሰበሰቡት ታሪካዊ ቀን ነጠቀን አዛኝ፣ደግ፣ጸሎተኛ፣በዚህ ክፉ ዘመን በጸሎት ያስቡን የምንላቸው ቢለምኑ ቸሩ አምላክ የሚሰማቸው ዓለምን የተጸየፉ ፍትወት፣ስስት፣ ቁጣ፣በጥቅሉ የዚህ ዓለም ጣጣ የራቀላቸው አረጋዊ ሊቅ አጣን እሳቸው ጨረሱ ደጋጎቹ አበው ከደረሱበት ደረሱ ሲዘምሩ ሊዘምሩ ሲቀድሱም ሊቀድሱ ወደ አባቶቻቸው ገሰገሱ።
እናት ቤተክርስቲያንንና እኛ ልጆቿ ልጆቻቸውን እግዚአብሔር ያጽናን ሰው ይተካልን በረከታቸው ይድረሰን ነፍስ ይማር እንዳልል እምትጸድቀውን ነፍስ ጎረቤት ያውቃታል እንዲሉ አበው አንዳች ምክንያት አበሳም የለባቸው ምክንያተ ኃጢአት የማይገኝባቸው ፍጹም ምሁር ናቸውና ደግሜ እላለሁ የሚታካቸው ይተካልን በረከታቸው ይድረሰን ይደርብን!!!
18/07/2025
፨ቤተክርስቲያ አንድ ከሩቅ የሚያበራ እነቁዕ አጣች የተፈጥሮ ግዴታ ሆኖ እኒህን እንቁዕ ሁለንተናዊ ሊቅ መንፈሳዊ ረቂቅ አወቅሁ ብለው የማይታበዩ ትሁት ሳላጋንን በእውነት በምድር (በዚህ ዓለም)ያየናቸው እምትጸድቀውን ነፍስ ጎረቤት ያውቃታል እንዲሉ አምነን አፋችንን ሞልተን የምንመሰክርላቸው እውነተኛ ጻድቅ
በሥጋ ሰብእ የሚታዩ በምሥጢር ሠረገላ ዓለመ ነፍስን የቃኙ ባለአእምሮ እሩቅና ምጡቅ ነበሩ።
ሊቁ የኔታ ወልደ ትንሣኤ ዘታዕካ ነገሥት በአታ ለማርያም አብነት
የኔታ የተፈጥሮ ሕግ ነውና እንግዲህ ምን እንላለን ነፍስዎት በሰላም ትረፍልን!!!
09/05/2025
TikTok · አባ ኃይለመለኮት ይኄይስ 58 likes, 7 comments. “ልደታ ለማርያም❤ ሙሉውን ♦️በዩቲዩብ♦️ ገጻችን ያገኙታል።”
19/04/2025
✨ ገብረ ሰላመ በመስቀሉ ትንሳኤሁ አግሀደ ✨
🙏 እንኳን ለዚህች ቀዳም ስዑር አደረሳችሁ።🙏
ቀዳም ስዑር ማለት የተሻረች ቅዳሜ ማለት ነው።
ለምን ተሻረች ከምን ተሻረች ካልን ደግሞ
ቀድሞ በጥንተ ፍጥረት ቸሩ አምላክ ከእለተ እሑድ እስከ እለተ ዓርብ ዓለምን ሠርቶ ጨርሶ ስነ ፍጥረቱን አጠናቆ በእለተ ቀዳም አርፏል ሢሠራት አረፈባት የሠራት ለእረፍት ነው ማለት ነው ።
⛪️⛪️⛪️⛪️⛪️⛪️⛪️⛪️⛪️⛪️⛪️⛪️⛪️⛪️⛪️⛪️⛪️⛪️⛪️
ኢትዮጵያዊው ሊቅ ቅዱስ ያሬድም ሰንበትየ ቅድስትየ እንተ አእረፍኩ እምኩሉ ግብርየ ብሎ ገልጧታል።
ነቢዩ ኤርምያስም ወኢታብኡ ጾረ ክቡደ ውስተ ኀዋኅዊኀ ለኢየሩሳሌም ብሎ በዚህች ቀን በእለተ ቀዳሚት ሰንበት እንዲያርፉባት እንጂ ሸክም እንኳን እዳይሸከሙባት ትዕዛዝ ሰጥቶ እናገኘዋለን።
በሐዲስ ኪዳንም ጠዋት ቀድሰን እናቆርባለን ያገኘነውን ምግበ ሥጋም በጥዋት እንመገባለን እንጅ ጾምም ቢሆን ቀዳሚት ሰንበትን አንጾምም ጾመንን አንውልም‼️
⭕️⭕️⭕️⭕️⭕️⭕️⭕️⭕️⭕️⭕️⭕️⭕️⭕️⭕️⭕️⭕️⭕️⭕️⭕️⭕️
የምንጾማት በዚህ እለት ብቻ ነው ምክንያቱም ሰንበትየ ቅድስትየ ብሎ ያከበራት ስነ ፍጥረቱንም አጠናቆ ያረፈባት ጌታ በመቃብር አድሮ ስለዋለባት ውሎም ስአደረባት ቅድስቱ እናቱና ቅዱሳን ሐዋርያትም በኃዘን አድረው ስለዋሉባት ውለውም ስለአደሩባት ለእኛ ለክርስቲያኖች አምላክ መቃብር የነበረባት የኃዘን መታሰቢያ እንጅ የደስታ ቀናችን ስለአይደለች አረፍትነቷን ሽረን ጾም አድረን ጾም ስለምንውልባት ጾም ውለንም ትንሣኤው እስከሚበሠርልን ስለምናከፍልባት ቀዳም ስዑር(ስዑር የተሻች ቅዳሜ) ተብላለች።
🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿
፨በሌላ መልኩ ደግሞ የኃጢአቱ የፍዳው የመከራው ዘመን ማለፉን የኃጢአቱ ባሕር መጉደሉን ለማብሠር አባቶቻችን (ካህናት)በርግበ ኖኅ የታየውን ለምለም ምልክት(ቄጤማ) ያድሉናል ገብረ ሰላመ በመስቀሉ በማለትም የሰላም ድምጽ ያሰሙናል።
Click here to claim your Sponsored Listing.
Category
Contact the place of worship
Telephone
Website
Address
Addis Abeba
Addis Ababa
1000