Anwar seid
03/06/2023
"Some have reasons to Live for
Some have reasons to Kill for, and
Other have reasons to die for” … John Wick 4
የአርበኞች ቀን ሲነሳ በተለያዬ ጊዜ ለሃገር (ህዝብ) ብለው የወደቁትን እናስታውስና እኛስ ስለ እኛና ስለሃገራች የት ነው ያለነው ብለን እንጠይቃለን? መልሱ የሚያስፈራን ከሆነ ማንሳትም አንፈልግ!
አባቶቻችን እንደነገሩን አንድን "ጠላት" ሲታገሉ የሃሳብ ልዩነት ሳይኖራቸው አልነበረም - ይልቁንም የህልውና ጉዳይ ሲሆን አንዱ ያንዱን እንዳከበረ ቅድሚያ ሰጥተው ሃገር ላይ አንድ ናቸው::
ለምሳሌ:- ከጣልያን ጋር የታገሉትን አርበኛ ሼህ ጠልሃ ጃእፈርን ታሪክ ብንወስድ ከሼህ አህመድ ዳና (ዳንዩል አወል) ጋር ሰፊ ተቃርኖ ነበራቸው:: ጉዳዩ ደግሞ እንዲህ ነው:
እፄ ዩሃንስ በወሎ ዘማቻቸው ያድኑ የነበሩት የሙስሊሙን ታላላቅ ምሁናራን ነበር:- በዋናነት ከሚጠቀሱት ጀማሉዲን አንይና ተማሪወቻቸው እንዲሁም ጦልሃ ጃእፈር ናቸው:: በቀጥታ መያዝ ያልቻሉትን ሼህ ደግሞ በጣም በሚወዱዋቸው መምህራኖቻቸው በግድ ያጠምዱ ነበር::
ሼይ ጠልሃ ጃእፈር ሼይሃቸው በጣም ይወዳሉ እና ይህን ኢንተለጀንስ የደረሳቸው አፄ ሼሃቸውን አድነው ከያዙ በሁዋላ ተማሪያቸው ጠልሃን በጣም ናፍቀህኛልና በቶሎ መጥተህ እየኝ ብለው መልእክት ያሳያሉ::
የጦልሃ ጃእፈር ደርሶች ሼሃቸው ያሉበት የዩሃንስ ክልል ነው ብለው ቢያስጠነቅቁም የሼሃቸው ነገር ያልሆነላቸው ጦልሃ ጃእፈር - አልቀርም ብለው ይሄዳሉ:: ደረሶቻቸውም ካልክ እንግዲህ ብለው እጅበው ይሄዳሉ::
እንደደረሱም - መጀመርያ የሼሁን መኖሪያ ካጠሩ በሁዋል ጠልሃን አስገብተው እነሱ ዙሪያውን ከበው ይጠብቁ ጀመር:: ጠልሃ ሼይሃቸውን ሲዘይሩ- እንዲት ልጅ እየሮጠች ከቤት ወጣች:: የዚህች ልጅ ሩጫ ያላማራቸው ደረሶች ጠልሃ ቶሎ እንዲወጡ ሊናገሩ ገቡ::
ልጅቱ የወጣችው የጠልሃን መምጣት ለዩሃንስ ወታደሮች ለመንገር ነበርና ሰፈሩ ወዲያውኑ በጦርነት ተተራመሰ:- በዩሃንስና በጦልሃ ጃእፈር ወታደሮች መካከል::
ጦልሃም የሼሃቸውን ግንባር ስመው ሊወጡ ሲሰናበቱ - ሼሃቸው እጃቸውን ይዘው "እጅህን ለዩሃንስ ስጥ ባንተና/ደረሶችህ የተነሳ ሙስሊሞች እያለቁ ነው" ይላሉ:: ጦልሃም ሊያስለቅቁ ሞክረው እምቢ ሲሉዋቸው ግዜ በሳንጃ የሼሃቸውን እንገት ቆርጠው እጃቸውን በማስለቀቅ ያመልጣሉ::
ከብዙ ትግልና ግዜ በሁዋል ዩሃንስን በሌላ ግንባር ከሼይሃቸው ጀማሉዲን አንይ ጋር ሆነው ሲታገሉ ተማርከው ያመለጡት ዳንዩል አወል ጋር ይገናኙና ያወራሉ:: ከወሬወቻቸው መሃል:-
ዳንዩል አወል:- " ያ ጦልሃ እኔ ግን የሚጨንቀኝ ጌታህ ሙስሊሞችን (ሼይህህን እና ደረሳወቹን) ለምን ጨፈጨፍክ ብሎ ሲጠይቅህ ምን ብለህ እንደምትመልስ ነው?"
ጦልሃም መለስ አድርገው "ያ ሼይህ እኔ ደግሞ የሚጨንቀኝ እሱ ሳይሆን - ሙስሊም ወንድሙን አሳልፎ የሰጠን "ከሃዲ" ለምን አስተረፍካቸው? ለምን አልጨረስካቸውም? ብሎ ቢጠይቀኝ ምን ብዬ እንደምመልስ ነው::" ብለው መለሱ::
አስቡት ሁለቱ ጉምቱ ምሁራን (አንድ ህዝባዊ አላማ ቢኖራቸውም) የተለያዩበት ጉዳይ ምን ያክል ከባድ እንደነበር:: ያም ሆኖ ግን ከልዩነታቸው ጋር ሆነው በሰለጠነ መንገድ ነበር የሚነጋገሩት!
ልዩነትን ጠረጴዛ ዙሪያ ማምጣት ከመማርም ከማወቅም በላይ ስልጣኔንና ብስለትን (wisdom) ይጠይቃል::
ያ ሁሉ የታገሉት ድካማቸውንና ደማቸውን እንዲህ ከንቱ እንደምናደርገው ቢያውቁ ምን ይሉ ይሆን?!
#የአባቶቻችን ልጆች ያድርገን
Nush
Harare, .
ViaM sani
Click here to claim your Sponsored Listing.
Category
Contact the university
Website
Address
Addis Abebe
Addis Ababa