Infix Computer Technology

Infix Computer Technology

Share

25/06/2022
26/02/2022

አንድ አፕሊኬሽን ዳውንሎድ ከማድረጋችን በፊት አፕሊኬሽኑ #ጎጂ ወይም #ጠቃሚ መሆኑን እንዴት ማረጋገጥ እንችላለን?

ከGoogle Play Store ላይ የምናወርዳቸው አፕሊኬሽኖች ጠቃሚ መሆናቸው የተረጋገጠላቸው እና ጎጂ እንዳልሆኑ የተመሰከረላቸው ናቸው፡፡

ነገር ግን አንድ አንድ ግዜ ጠቃሚ መስለው ጎጂ አፕሊኬሽኖችን Play Store ላይ ልታገኙ ትችላላችሁ፡፡

ታድያ Play Store ላይ አፕሊኬሽን ዳውንሎድ ስናደርግ አፕሊኬሽኑ ጠቃሚ ወይም ጎጂ መሆኑን እንዴት መለየት እንችላለን?

1. አፕሊኬሽኑ ምን ያህል ግዜ ዳውንሎድ እንደተደረገ መመልከት

ዳውንሎድ ማድረግ የፈለግንው አፕሊኬሽን ዳውንሎድ ከማድረጋችን በፊት አፕሊኬሽኑ ምን ያህል ግዜ ዳውንሎድ (Download Count) እንደተደረገ በደንብ መመልከት

ለምሳሌ ዳውንሎድ የምታደርጉት አፕሊኬሽን አንድ ሚሊዮን ግዜ ወይም ከዚያ በላይ ዳውንሎድ እንደተደረገ ካያችሁ ወድያው አፕሊኬሽኑ የተለቀቀበት ቀን በደንብ መመልከት፡፡

ምክንያቱም አብዛኛው አፕሊኬሽን ከተለቀቀበት ግዜ ጀምሮ አንድ ዓመት ወይም ከዚያ በላይ የቆየ ሲሆን ነወ ከሚሊዮን በላይ ዳውንሎድ ሊኖረው የሚችለው፡፡ ስለዚህ እናንተ ማውረድ የፈለጋችሁት አፕሊኬሽን ከተለቀቀ አንድ ዓመት ካልሞላው እና ዳውንሎድ የተደረገው ከሚሊዮን በላይ ከሆነ አፕሊኬሽኑን ከማውረድ ብትቆጠቡ ይሻላል፡፡

2. ስለ አፕሊኬሽኑ የተሰጡ የተወሰኑ አስተያየቶችን ማንበብ

ዳውንሎድ ማድረግ የምትፈልጉት አፕሊኬሽን ከማውረዳችሁ በፊት ከዚህ በፊት አፕሊኬሽኑን ዳውንሎድ ያደረጉ ሰዎች ስለ አፕሊኬሽኑ አስተያየት (Reviews)ያስቀምጣሉ፡፡ እነዚህን አስተያቶች በጥንቃቄ ማንበብ፡፡

ስለ አፕሊኬሽኑ በጣም የሚያማርሩ አስተያየቶች ካነበባችሁ አፕሊኬሽኑ ከማውረድ እንደጥቆጠቡ እመክራለሁ፡፡

3. የአፕሊኬሽኑ ስምምነት በጥንቃቄ ማንበብ

አፕሊኬሽኑ ከላይ የተጠቀሱትን ፍተሸዎች ካለፈ ዳውንሎድ ታደርጉታላችሁ፡፡ ከዚያ ኢንስቶል ስታደርጉት የአፕሊኬሽኑን ስምምነት በጥንቃቄ ማንበብ ያስፈልጋል፡፡

ሁላችንም ማለት ይቻላል አፕሊኬሽን ኢንስቶል ስናደርግ ስምምነቱን ሳናነብ "Accept" እንላለን፡፡ ልክ አይደለም፡፡
ምክንያቱም የሳይበር ወንጀለኞች ይህንን ባህሪያችን ስለሚያውቁ እኛን ሊጎዱ የሚችሉ ነገሮችን ስምምነቱ ላይ በማስገባት ጥቃት ሊፈፁሙብን ይችላሉ፡፡

ስለዚህ ስምምነቱን ስታነቡ ለምሳሌ data mining, data sharing, pop-ups ወዘተ የሚሉ ቃላት ከተመለከታችሁ የአፕሊኬሽኑን ኢንስቶሊንግ ሂደት እንድታቋርጡ እመክራለሁ፡፡፡


ስለዚህ ዳውንሎድ ማድረግ የፈለጋችሁት አፕሊኬሽን ቢያንስ እነዚህን 3 ፍተሸዎችን ካለፈ ጎጂ አይደለም ማለት ነው፡፡

24/02/2022

5 ምርጥ አለምአቀፍ ነፃ የትምህርት ዕድል ማግኛ ድህረ ገፆች(Websites)

1 - StudentScholarships.org
2 - collegeboard.org
3 - StudentScholarships.org
4 - ScholarshipExperts.com
5 - SuperCollege.com
መልካም እድል
ስለኮምፒውተርና ቴክኖሎጅ ያለዎትን እውቀት ያሳድጉ በተጨማሪም በቴሌግራሜ ቻናል ምርጥ ምርጥ ስለኮምፒውተር የምለቃቸውን መረጃዎችን ለመከታተል እንዲያመችዎ ሼር ማድረጋችሁን አትርሱ በፍጥነት መረጃ እንዲደርሳችሁ

Want your business to be the top-listed Computer & Electronics Service in Addis Ababa?
Click here to claim your Sponsored Listing.

Address


Addis Ababa
1000