Girum.com

Girum.com

Share

21/05/2026

🛖የጉራጌ ወማካ(የጉራጊኛ አባባሎች)

ጉራጊኛ= በአብ አፈር ይትዋኴ በአዶት አፈር ይትሻኮቺ
አማርኛ =በአባት መሬት ይዋጋሉ በእናት መሬት ይታረቃሉ

ጉራጊኛ =አብ ኤባር ንበረት ወካ ኤነን ቤት እማቱ
አማርኛ = አባት የሌለበት ኑሮና መሶሶ የሌለው ቤት አንድ ነው

ጉራጊኛ = አት ኧጨ ኤረድድ እማት ምስ ኤፈርድ
አማርኛ = አንድ እንጨት አይነድም አንድ ሰውም አይፈርድም

ጉራጊኛ = አትᎊጠᎀዊም ቢሞኲ ተጌከረም ነማም
አማርኛ = አስጎንብሰው በቀብሩት ተስተካክሎ በቀለ

ጉራጊኛ = አነበትም ፏᎈየ ይከዌኸማ ኤበሁሪ
አማርኛ = ምላስና ሸማ እንደፈለጉት ይተጣጠፋል

ጉራጊኛ = አናከረ ቃውጣ አንቃታ በኤብ ያጣጣ
አማርኛ = ከብት ያላረባ ጉረኛ አፉን በወተት ይለቃለቃል

ጉራጊኛ = አንቅም ወለብነት ኤትሼምታ
አማርኛ =ሃቅና ጨዋነት አይሸሸግም

ጉራጊኛ = አቦገዳ ቲኸዳ የቸኮሪ በሰር አንበራ ይብር
አማርኛ = ጓደኛ ሲከዳ የተቀቀለ ስጋ አልበላም ይላል

ጉራጊኛ = ያጀጎረን ታጀጎረን ይትጮድ
አማርኛ = የቸገረው ከተቸገረ ጋር ይወያያል

ጉራጊኛ = አንፊና ቲደርጒ ኤን ይበሂ
አማርኛ = አፍንጫ ሲመታ አይን ያለቅሳል

🛖🛖🛖

"ከፈንጅ አምካኝነት እስከ ድምጻዊነት፤ የጀማል መሀመድ አስገራሚ የህይወት ጉዞ 21/05/2026

የልጅነት ትዝታችን
ድምጻዊ ጀማል መሀመድ🙌

"ሙዚቃ ያቆምኩት ከመጠቀም ካለመጠቀም ጋር በተያያዘ አይደለም!" — ድምጻዊ ጀማል መሀመድ

በኢትዮጵያ የሙዚቃ ታሪክ ውስጥ በተለይም በጉራጊኛ ባህላዊና ዘመናዊ ሙዚቃዎች የሚታወቀው አንጋፋውና ተወዳጁ አርቲስት ጀማል መሀመድ በፖድካስታችን እንግዳ ሆኖ ቀርቧል። በዚህ ልዩ ቆይታ የኪነጥበብ ጉዞውን ስኬቶች፣ ተግዳሮቶች እና ሙዚቃ ያቆመበትን እውነተኛ ምክንያት በግልጽ ያጋራናል።
የእንግዳው ታሪክና የሙዚቃ አሻራ፦

ድምጻዊ ጀማል መሀመድ በልዩ ድምፅ አወጣጡና ዘመን አይሽሬ በሆኑ ዜማዎቹ የጉራጌን ባህል፣ ጥበብና ማንነት በሙዚቃው በስፋት ያስተዋወቀ ታላቅ አርቲስት ነው። ለረጅም ዓመታት በሕዝብ ዘንድ ተወዳጅነትን ያተረፉ 9 አልበሞችና በርካታ የሙዚቃ ሥራዎችን አበርክቷል። ከእነዚህም መካከል፦

• ሰብ ኸርኸም (Seb Herhem)
• የጉራጌ አዶ (Yegurage Ado)
• ዝ ንማጀ አንኸረ እሳቱ
• ሎሚ ብርቱኳን
• ታይ ገረ
• ኦጃማ እና ሌሎችም ይገኙበታል።

የእሱ ሥራዎች በባህላዊ የሙዚቃ መሣሪያዎችና በዘመናዊ ቅንብር የታጀቡ በመሆናቸው በመላው ኢትዮጵያ የሙዚቃ አፍቃሪዎች ዘንድ ትልቅ ቦታ አላቸው።

🖋️ሓሪ ዲጂታል

ግቡና እዩት

"ከፈንጅ አምካኝነት እስከ ድምጻዊነት፤ የጀማል መሀመድ አስገራሚ የህይወት ጉዞ "ሙዚቃ ያቆምኩት ከመጠቀም ካለመጠቀም ጋር በተያያዘ አይደለም!" — ድምጻዊ ጀማል መሀመድበኢትዮጵያ የሙ...

20/05/2026

እሹሩሩ ጉራጌ ደግ ነው 🔥🔥

Photos from Girum.com's post 20/05/2026

ክልሉን በሁሉም መስኮች ተወዳዳሪ ለማድረግ የተጀመረው ጥረት ስኬታማ ነው:- ርዕሰ መስተዳድር እንዳሻው ጣሰው (ዶ/ር)

ርዕሰ መስተዳድር እንዳሻው ጣሰው (ዶ/ር)ከምሁር አክሊል ወረዳ ከተውጣጡ ነዋሪዎች ጋር በወረዳው በሰላም፣በልማት እና በመልካም አስተዳደር ላይ ያተኮረ የምክክር መድረክ በሀዋሪያት ከተማ እያካሔዱ ነው

የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ርዕሰ መስተዳድር እንዳሻው ጣሰው (ዶ/ር) በምክክር መድረኩ እንደገለጹት ክልሉን በሁሉም መስኮች ተወዳዳሪ ለማድረግ የተጀመረው ጥረት ስኬታማ ነው ብለዋል።

ክልሉ ተመስርቶ ወደ ስራ ሲገባ በበርካታ ፈተናዎች ውስጥ በማለፍ ነበር ሲሉም ርዕሰ መስተዳድሩ አስረድተዋል።

ከነባሩ ክልል የተላለፈ እዳ፣ለሰራተኞች ደመወዝ በአግባቡ ያለመክፈል፣የተፋዘዘ የስራ ባህል እና ሌሎች በርካታ ችግሮች መስተዋላቸውን ርዕሰ መስተዳድሩ አብራርተዋል።

ስራ ስንጀምር ከነባሩ ክልል 6 ቢሊየን ብር እዳ ተረክበን ነው ያሉት ርዕሰ መስተዳድሩ ከዚህ ውስጥ 5 ነጥብ 4 ቢሊየን ብር ዕዳ መክፈል ስለመቻሉም አብራርተዋል።

ከ 3 ቢሊየን ብር በላይ የማዳበሪያ እዳ እንደነበር ያስታወሱት ርዕሰ መስተዳድሩ ይህም ለክልሉ መንግስት ካጋጠሙት ተግዳሮቶች ውስጥ ተጠቃሽ መሆኑን ጠቁመዋል።

በክልሉ ከ60 ሺ በላይ የመንግሥት ሰራተኞች ከ2 እስከ 6 ወራት ደመወዝ ሳይከፈላቸው የቀሩ ሰራተኞች እንደነበሩም ተናግረዋል።በአሁኑ ሰዓት ለሁሉም የመንግስት ሰራተኞች ደመወዝ በወቅቱ መክፈል ስለመቻሉም ጠቅሰዋል።

መምህራን፣የጤና፣የግብርና፣የፍትህ እና የጸጥታ አካላት የችግሩ ተጎጂ መሆናቸውን ርዕሰ መስተዳድሩ ጠቁመዋል።

የተቀዛቀዘው የስራ ባህል እንዲነቃቃ ምቹ ሁኔታ መፈጠሩን ርዕሰ መስተዳድሩ በንግግራቸው አመላክተዋል።

በክልሉ በ 4 ነጥብ 3 ቢሊየን ብር በሰባቱም የክልል ማዕከላት የቢሮ ግንባታ እየተካሔደ መሆኑን በአብነት ጠቅሰዋል።

የርዕሰ መስተዳድር ጽ/ቤት፣ቤተ መንግስት፣የመሰብሰቢያ አዳራሽ በ6 ወራት ጊዜ ውስጥ በማጠናቀቅ ስራ መጀመር መቻሉን ርዕሰ መስተዳድሩ በአብነት ጠቅሰዋል።

የህዝብ ተሳትፎ እና ተጠቃሚነት ማረጋገጥ ላይ በትኩረት እየተሰራ ስለመሆኑም አብራርተዋል።

በሰላምና ጸጥታ፣በግብርና፣በጤና፣በትምህርት፣በስራ እድል ፈጠራ፣በኢንቬስትመንት ፣በንግድ፣በመሰረተ ልማት ዘርፎች የላቀ ውጤት ማስመዝገብ የሚያስችል ስርዓት መዘርጋት መቻሉን ርዕሰ መስተዳድሩ ጠቅሰዋል።

የምሁር አክሊል ወረዳ ዋና አስተዳዳሪ አቶብስራት ገብሩ እንደገለጹት መድረኩ በህዝብ እና በመንግስት መካከል ጠንካራ ትስስር መፍጠር ነው።

በውይይቱ ጠንካራ አፈጻጸሞችን ማስቀጠል እና የሚያጋጥሙ ውስንነቶችን ማረም የሚያስችል መድረክ መሆኑን ነው ዋና አስተዳዳሪው የገለጹት።

ያሉትን ጸጋዎች ወደ ልማት በመቀየር በሁሉም መስክ የላቀ ውጤት ለማስመዝገብ መስራት የሚያስችል መድረክ ስለመሆኑም አብራርተዋል።

Want your public figure to be the top-listed Public Figure in Addis Ababa?
Click here to claim your Sponsored Listing.

Category

Address


Addis Ababa