Selah

Selah

Share

29/09/2025

ዮሐንስ 15:5
… ያለ እኔ ምንም ልታደርጉ አትችሉምና።

በቀናት ጥድፊያ እና ማለቂያ በሌለው የህይወት ሩጫ፣ ጥንካሬያችን ብቻ ወደ ፊት እንደሚወስደን ማመን ቀላል ነው። ነገር ግን እውነተኛ እድገት፣ ዘላቂ ፍሬ እና ትርጉም ያለው ህይወት የሚወለዱት፣ የሚጸኑት በእርሱ ከመኖር ብቻ ነው። ቆም እንበል፣ እንመን፣ እና መልካሙን ነገር ወደ ሚያለመልመው ምንጭ እንመለስ።

30/12/2024

ዮሐንስ 8:12
ኢየሱስ እንደ ገና ለሰዎቹ፣ “እኔ የዓለም ብርሃን ነኝ፤ የሚከተለኝም የሕይወት ብርሃን ይሆንለታል እንጂ ከቶ በጨለማ አይመላለስም” አላቸው።

በዚህ ዓለም ውስጥ የዚህን ብርሃን መምጣት ለማክበር እየተዘጋጀን ነው፤ ይህም በጨለማ ላሉት ታላቅ ብርሃን እንደሚበራ የተነገረውን ትንቢት የሚያሟላ ነው (ኢሳይያስ 9፡2)። ቃል ኪዳኑ ግልጽ ነው፡ እርሱን ስንከተል በከንቱ አንባዝንም። ይልቁንም ብርሃኑ ወደ ሙሉ እና ዘላለማዊ ሕይወት ይመራናል። ይህ መልእክት በእርሱ መገኘት ስላለው አስደናቂ ኃይል እንድናሰላስል ይጋብዘናል። ኮከቡ ጥበበኞቹን ወደ ግርግም እንደመራቸው ሁሉ ብርሃኑ ዙሪያችን ያለው ዓለም ምንም ያህል ጨለምተኛ ቢሆንም ወደ ሰላም፣ ወደ መልካም ዓላማና ተስፋ ሊመራን የታመነ ነው።

John 8:12
When Jesus spoke again to the people, he said, “I am the light of the world. Whoever follows me will never walk in darkness, but will have the light of life.”

We are getting ready to celebrate the arrival of this light in the world, a fulfillment of the prophecy that a great light would shine upon those in darkness (Isaiah 9:2). The promise is clear: when we follow Him, we are not left to wander aimlessly. Instead, His light leads us toward life—full, eternal, and abundant. This message invites us to reflect on the transformative power of His presence. Just as the star guided the wise men to the manger, His light continues to guide us to peace, purpose, and hope, no matter how dark the world around us may feel.

25/11/2024

መዝሙር 62:11
እግዚአብሔር አንድ ነገር ተናገረ፤
እኔም ይህን ሁለት ጊዜ ሰማሁ፤
ኀይል የእግዚአብሔር ነው።

ይህ መዝሙር በዳዊት በግል ወይም በአገር ቀውስ ወቅት የተጻፈ እንደሆነ ይታመናል። በዚህ ታሪካዊ ሁኔታ ውስጥ ገዢዎችና ሐገራት ብዙውን ጊዜ ኃይልን ከአማልክታቸው ወይም ከወታደራዊ ጥንካሬያቸው እንደሚያገኙ ይታመን ነበር። ዳዊት “ኃይል የእግዚሐብሔር ነው” በማለት ይህንን የአስተሳሰብ ዘይቤ በቀጥታ ይቃወማል። የእግዚአብሔርንም ከፍተኛ ሥልጣን ያውጃል። ጥቅሱ ሁሉም ኃይል በሰው ወይም በምድራዊ ሥርዓት ሳይሆን በአምላክ እጅ እንደሚገኝ ያስታውሰናል። “አንድ ነገር... ሁለት ነገር” የሚለው ሐረግ የአምላክን መገለጥ ሙሉነትና እርግጠኝነት ያጎላል፤ ድግግሞሹም የመልእክቱን አስፈላጊነት አጽንዖት ይሰጣል። ለአማኞች ይህ ጥቅስ ጥልቅ እረፍትን ይሰጣል፤ የአምላክ ሉዓላዊነት ከሁሉም የሰው ኃይልና ሴራ በላይ ነው፤ በአለመረጋጋት ወይም በጭቆና ጊዜ ድጋፍን ይሰጣል። መዝሙር 62፡11ን ማሰላሰል በአምላክ በማይተካ ሥልጣን ሙሉ በሙሉ እንድንተማመን እና ሕይወታችንን ከፍትህና ፍቅር ጋር እንድናስማማ ይጋብዘናል።

This Psalm is believed to have been written by David during a time of personal or national crisis. In that historical context, rulers and nations often attributed power to their gods or military strength. David’s declaration that "power belongs to God" directly challenges this mindset, proclaiming Yahweh as the ultimate authority. The verse emphasizes that all power resides with God, not with humans or earthly systems. The phrase "one thing...two things" highlights the completeness and certainty of God’s revelation, with its repetition underscoring the importance of the message. For believers, this verse offers profound reassurance: God’s sovereignty far exceeds all human strength and schemes, providing comfort in times of uncertainty or injustice. Meditating on Psalm 62:11 invites us to trust fully in God’s unrivaled authority and to align our lives with His justice and love.

Want your place of worship to be the top-listed Place Of Worship in Addis Ababa?
Click here to claim your Sponsored Listing.

Address


Bole Dildiy, On Your Way To Bora Amusement Park, Beside MulMul Bakery
Addis Ababa