Ethio Mereja

Ethio Mereja

Share

15/06/2025

ለሦስተኛ ምሽት የቀጠለው የእስራኤል እና ኢራን የአየር ጥቃት የኒውክሌር ስምምነት ተስፋን አጨለመ
*******************************************************************************************
በቴህራን የኒውክሌር መርሐ ግብር ዙሪያ በአሜሪካ እና ኢራን መካከል ስድስተኛ ዙር ድርድር ዛሬ ሊደረግ ነበር።

እስራኤል ለሦስተኛ ምሽት በኢራን ላይ የአየር ጥቃት ስትፈፅም፤ ቴህራን በበኩሏ ሁለት የባላስቲክ ሚሳኤሎችን ወደ እስራኤል አስወንጭፋለች።

ቴህራን በጥቃቶቹ ምን ያህል ጉዳት እንደደረሰባት መረጃ እያወጣች አይደለም። እስራኤል ግን በኢራን ጥቃት የተገደሉትን እና የቆሰሉትን እየቆጠረች ነው።

12/04/2025

ክርስቲያኖ ሮናልዶ ዛሬ ሁለት ጎል አስቆጥሯል ።

የሮናልዶ አድናቂዎች አላቸው ??
SUuuuuuu በሉ

12/04/2025

በአዳማ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ ተቀጥረው የሚሰሩ የአንዳንድ የህንድ ዜጎች ፎርጅድ ዶክመንት ሲዳሰስ

- "ቅጥር ለማግኘት ለዩኒቨርስቲው ሰራተኞች የሁለት ወር ደሞዝ የሚሰጡ አሉ"

(Ethio መረጃ)- በኦሮሚያ ክልል በሚገኘው የአዳማ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ ተቀጥረው የሚሰሩ አንዳንድ የህንድ ዜግነት ያላቸው አስተማሪዎች ሀሰተኛ የትምህርት ማስረጃ እንዳላቸው እና ይህ እንዳይታወቅ ከአንዳንድ የዩኒቨርስቲው አመራሮች ጋር እንደሚሰሩ መረጃዎች እየወጡ ይገኛሉ።

Ethio መረጃ የተመለከታቸው እና በአንዳንድ የህንድ አስተማሪዎች ጭምር እውነትነታቸው የተረጋገጠ እነዚህ መረጃዎች እንደሚጠቁሙት በወር በሺዎች የሚቆጠር ዶላር የሚከፈላቸው አንዳንድ ህንዳውያን የትምህርት ማስረጃቸው ወይ ሀሰተኛ ነው ወይም ያልተማሩትን የዶክትሬት ዲግሪ እንደተማሩ ሀሰተኛ ማስረጃ አቅርበው ተቀጥረዋል።

"አንዳንዶቹ የክህሎት እና የትምህርት ማረጋገጫ ሂደትን ግልፅ ባልሆነ መልኩ አልፈው ተቀጥረው ይገኛሉ፣ ይህ ደግሞ እየተደረገው በዩኒቨርስቲው ጥቂት አመራሮች ተሳትፎ ጭምር ነው" የሚሉት የአዳማ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ የቀድሞ መምህር የነበሩት ዶ/ር ሱረሽ ኩማር ናቸው።

አንዳንድ ህንዳውያን ግዜያቸውን እና ሙያቸውን በመጠቀም ለውጥ ለማምጣት ጥረት እያረጉ ቢሆንም እነዚህ ሀሰተኛ ዶክመንቶችን ይዘው እየመጡ የሚቀጠሩ ህንዳውያን ችግር እየሆኑ እንደመጡ ዶ/ር ሱረሽ ያስረዳሉ።

"ሀሰተኛ ዶክመንት ይዘው የሚመጡ እነዚህ ግለሰቦች የኢትዮጵያን የትምህርት ስርዐት እየገደሉት ነው" የሚሉት ዶ/ር ሱረሽ የእነዚህን ህንዳውያን ስም በዝርዝር ያቀረቡበትን ዶክመንት Ethio መረጃ ተመልክቷል።

አንዳንዶቹ ህንዳውያን ህገወጥ ዶክመንታቸውን ይዘው መጥተው ቅጥር ለማግኘት ለዩኒቨርስቲው ሰራተኞች የሁለት ወር ደሞዝ እንደሚሰጡ ታውቋል።

ከእነዚህ ህንዳውያን መሀል እስከ 14 አመት በኢትዮጵያ ያስተማሩ እንደሚገኙ የተጠቀሰ ሲሆን በዚህ ዙርያ የተሰጠ ማብራርያ የለም።

"አንዳንዶቹ ይባስ ብሎ ከሁለት ዩኒቨርስቲ ደሞዝ ይቀበላሉ፣ አንዳንዶቹ የስራ ፈቃድ የላቸውም ወይም ፈቃዳቸው ተቃጥሏል፣ ይህ ጉዳይ በአስቸኳይ ተጣርቶ እርምት ካልተደረገበት በሀገር ሀብት እና በተማሪዎች ትምህርት መቀለድ ነው" ያሉት ስማቸው እንዲጠቀስ ያልፈለጉ አንድ የዩኒቨርስቲው ኢትዮጵያዊ መምህር ናቸው።

ከዩኒቨርስቲው ምላሽ ካገኘን ይዘን እንመለሳለን።

Ethio መረጃ

Want your public figure to be the top-listed Public Figure in Addis Ababa?
Click here to claim your Sponsored Listing.

Category

Address


Adis Ababa
Addis Ababa