Alebachew Worku

Alebachew Worku

Share

17/06/2025

የምስራቅ ኦርቶዶክስ ቤተ ክርስቲያን መጽሐፍ ነው። በዚህ መጽሐፍ የተቀመጡት የግርጌ ማስታወሻዎች መጽሐፍ ቅዱስን አንብቦ የተጻፈበትን አውድ ለመረዳት መንገድ ጠራጊ ናቸው።

አጠቃላይ የገጽ ብዛት 1,868 ሲሆን በኢትዮጵያ ገበያ ላይ ይገኛል (ዋጋው ውድ ቢሆንም)።

መጽሐፉን ለማግኘት https://t.me/MekaneTibeb1/1200
ይጎብኙ፤ ቤተሰብ ይሁኑ!

27/05/2025

📖 መጽሐፍ ቅዱስ "ዲያብሎስም ረዥም ወደ ሆነ ተራራ አውጥቶ የዓለምን መንግሥታት ሁሉ #በቅጽበት አሳየው" ሉቃስ 4:5 በማለት ዲያቢሎስ ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስን በገዳመ ቆሮንጦስ ሲፈትነው እንዲህ እንዳደረገና ቀጥሎ ጥዠየማሰናከያ ጥያቄውን እንደጠየቀው ያስረዳናል።

✍️ በዚህ ምንባብ ላይ ትኩረት ላደርግ የፈለኩት #በቅጽበት #አሳየው የሚሉትን ቃላት ነው። ያው መጽሐፍ ላይ ስለተጻፈ ብቻ ጴ*ን*ጤውም ተሐ*ድሶውም ሳያቅማማ አሜን ብሎ ይቀበለዋል። ነገር ግን ስለ ቅዱሳን መላእክት ምልጃ ኦርቶዶክሳውያን ስናስተምር "እንዴት አንድ መልአክ በአንዴ ሁሉም ቦታ ይገኛል" በማለት ትችታቸውን ይዘረጋሉ። በእርግጥ ፍጡራን ስለሆኑ ውስንነት እንዳለባቸው ይታወቃል። ነገር ግን እግዚአብሔር በሰጣቸው ጸጋ መገኘት ባለባቸው ቦታ ሁሉ በቅጽበት ለመገኘት የሚከለክላቸው ነገር እንደሌለ በዚህ የቅዱስ መጽሐፍ ክፍል እንመለከታለን።

✝️ ታዲያ ዲያቢሎስ ለመድኃኒታችን ለኢየሱስ ክርስቶስ #በቅጽበት የዓለምን ነገስታት አሳየው የሚለውን (ያውም ለዓለሙ ሁሉ አስገኝ አምላክ) አሜን ብሎ ተቀብሎ፤ ቅዱስ ሚካኤል ቅዱስ ገብርኤል ሲባል መቃወም የጤና ይሆን?🤔🤔 ነው ቅዱሳን መላእክት ከዲያብሎስ ያነሱ ናቸው ብለው ነው የሚያስቡት?

https://t.me/MekaneTibeb1

የሥላሴ ሥዕል 03/05/2025

📖 ሥዕለ ሥሉስ ቅዱስን በተመለከ አንዳንድ ሰዎች "መቼም ቢሆን እግዚአብሔርን ያየው አንድ ስንኳ የለም" ዮሐ 1:18 የሚለውን በማንሳት እግዚአብሔርን ማን አይቶት ሥላሴን ሳላችሁ የሚሉ አሉ (ምንም እንኳ እግዚአብሔር ለሰወች የተገለጠበት ጊዜ ቢኖርም)።

✍️ በአጠቃላይ ቅዱሳት ሥዕላትን በተመለከተና የኢትዮጵያውያን አሳሳልን በተመለከተ ከዚህ በፊት አስተማሪ የሆኑ ስራወችን የሰራልን መምህራችን ዲ/ን ሄኖክ ወልደ ኃይሌ በዚህ ቪዲዮ ደግሞ ሥዕለ ሥሉስ ቅዱስን በተመለከ ከበቂ ማብራሪያ ጋር አቅርቦልናል።

📖✍️ ማየት ከመጀመራችን በፊት ማስታወሻ ብንይዝ እንጠቀምበታለን።

የሥላሴ ሥዕል የቅድስት ሥላሴ ሥዕል በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ሥርዓት ውስጥ ማእከላዊ ቦታ ይሠጠዋል:: ይህ ትምህርት የዚህን ሥዕል የትመጣ ከዓለም አቀፋዊ ቅኝት ጋር የሚዳስስ ት.....

Photos from Alebachew Worku's post 30/04/2025

በሊቀ ሊቃውንት Simur Alamrew

'Alexia'

ጸጋ የበዛለት ወንድማችን፦ ቤዛነትን ተነተነው፤አተነነው፡፡ ዱሮም ስብከት እንጂ ትምህርት አይኾንለት ነበር፡፡ እውነት!

ይኽን የማያምን ሰው ካለ ስለ ክርስቶስ ፈራጅነት እሰብካለኹ ብሎ ኤርምያስ 7:25ን ያብራራበትን ትምህርት መስማት ይችላል፡፡ እዚኽ ምዕራፍ ላይ "በእየዕለቱ እየማለድሁ ባሪያዎቼን ነቢያትን ሁሉ ልኬባችሁ ነበር" ይላል ቃሉ፡፡ ታዲያ ይኽ ወንድማችን 'እየማለድሁ' የሚለውን ቃል እያማለድኩ ብሎ ነው የተረዳው፡፡ ቃሉ ግን ከማማለድ ጋር አይገናኝም፡፡ ልክ እንደዚኽ እንደቤዛነት ትምህርት ከኪሱ እያወጣ ቃሉን ለሚያብራራ ሰው ግን ይገናኛል😉

አኹን ደግሞ ከቤታችን የተቀበለውን ኳስ ይዞ እንዲኽ አለ፦
"ቤዛዊተ ዐለም ለመባል መስቀል ላይ መሞት አለባት"፡፡ ኧረ ቀስ! መስቀል ላይ ሳይሰቀሉ ቤዛ/መድኀኒት የተባሉ ሰዎች አሉ፡፡
ከእነዚኽ ሰዎችም አንዱ Joshua ነው፡፡ በግእዝ ኢያሱ። በመጀመሪው ቋንቋ ኢያሱና ኢየሱስ ተመሳሳይ ስም ነው ያላቸው፡፡ ኹለቱም ጆሹዋ ይባላሉ፡፡ የስሙም ትርጓሜ መድኀኒት ማለት ነው፡፡ ይኽ በኢየሱስ ስም የተጠራው ኢያሱ ተሰቅሎ ነበር ወይ?? ኧረ ተዉ! ሳይሰቀሉ አርጅተው የሞቱ ቤዛዎች አሉ፡፡

እኔ ግን ይኽ ነገር በሽታ ይመስለኛል፡፡ እያነበቡ የሚያነቡትን እንዳይረዱ የሚያደርግ በሽታ አለ፡፡ Alexia ይባላል፡፡
ይኽ በሽታ መሰለኝ የአለማወቅ ጸጋ የሚያበዛ፡፡

https://t.me/MekaneTibeb1

17/04/2025

መከራም ቢያጸኑበት አልተቀየማቸውም፤ ዕውነትን ለሚፈርድ ቸርነትን መለሰ እንጂ፤ በመቸንከሩም የሞት ችንካርን አጠፋልን። ሔዋን በእግሮቿ ወደ ዕፀ በለስ ስለ ተመላለሰች እጆቹንና እግሮቹን በመቸንከር ከፍሏልና። በእጆቿም የበለስን ፍሬ ስለቆረጠች ፈንታ በእውነት የእግዚአብሔር ቃል በሥጋው ከመስቀል እንጨት ጋራ ተቸነከረ።
የሐሙስ ድርሳነ ማኅየዊ

Want your place of worship to be the top-listed Place Of Worship in Addis Ababa?
Click here to claim your Sponsored Listing.

Website

Address


Addis Ababa
1000