ethio 24

ethio 24

Share

05/05/2020

በኢትዮጵያ የሟቾች ቁጥር 4 ደርሷል!

የ75 ዓመት ዕድሜ ያላቸው ሴት በተጓዳኝ ህመም በሆስፒታል ውስጥ ተኝተው ሲታከሙ የነበሩ ሲሆን በገጠማቸው የመተንፈስ ችግር ምክንያት በኮሮና ቫይረስ በሽታ ተጠርጥረው ምርመራ ናሙና ከተወሰደ በኃላ በምርመራ ውጤቱ ቫይረሱ እንደተገኘባቸው ከመረጋገጡ በፊት ህይወታቸው ሊያልፍ ችሏል።

03/05/2020

አጫጭር መረጃዎች ፦

- በዩናይትድ ኪንግደም የሟቾች ቁጥር 28,131 ደርሷል፤ ባለፉት 24 ሰዓት የ621 ሰዎች ሞት ሪፖርት ተደርጓል። በሌላ በኩል በአንድ ቀን 4,806 ሰዎች በቫይረሱ መያዛቸው ተረጋግጧል።

- ባለፉት 24 ሰዓት በኳታር 776 ሰዎች በኮሮና ቫይረስ መያዛቸው ተረጋግጧል። አጠቃላይ በቫይረሱ የተያዙ ሰዎች 14,872 ደርሰዋል።

- በጣልያን ባለፉት 24 ሰዓት 474 ሰዎች መሞታቸው ሪፖርት ተደርጓል። በሌላ በኩል 1,900 ሰዎች በቫይረሱ መያዛቸው ተረጋግጧል።

- በቱርክ በኮሮና ቫይረስ የተያዙ ሰዎች 124,375 ደርሰዋል፤ በአንድ ቀን 1,983 ሰዎች በቫይረሱ ተይዘዋል። የሟቾች ቁጥር በ78 ጨምሮ በአጠቃላይ 3,336 ሆኖ ተመዝግቧል።

- ግብፅ በዛሬው ዕለት 298 ሰዎች በኮሮና ቫይረስ መያዛቸው ተረጋግጧል። አጠቃላይ በቫይረሱ የተያዙ ሰዎች 6,193 ደርሷል።

- በጋና በቫይረሱ የተያዙ ሰዎች 2,169 ደርሰዋል፤ ባለፉት 24 ሰዓት 95 ሰዎች በቫይረሱ መያዛቸው ተረጋግጧል። 88% በቫይረሱ የተያዙ ሰዎች ግልፅ የሆነ የጉዞ ታሪክ የላቸውም ብሏል።

- በAfricaCDC መረጃ መሰረት በአፍሪካ 1,701 ሰዎች ሞተዋል፤ 41,330 ሰዎች በቫይረሱ ተይዘዋል፤ 13,621 አገግመዋል።

- በዓለም አቀፍ ደረጃ የሟቾች ቁጥር ከ243,024 ደርሷል፤ 1,102,551 ሰዎች ከበሽታው አገግመዋል፤ 3,456,207 ሰዎች በቫይረሱ ተይዘዋል።

Want your business to be the top-listed Media Company in Addis Ababa?
Click here to claim your Sponsored Listing.

Telephone

Address


Ethiopia, Addis Abeba
Addis Ababa
1000