Entoto PTC.tms

Entoto PTC.tms

Share

Photos from Entoto PTC.tms's post 09/03/2026

የትብብር ስልጠና ለሚወጡ የቢዝነስ ስልጠና ዘርፍ የማርኬቲንግ ሰልጣኞች ኦረንቴሽን ተሰጠ ።
🇪🇹30/06/2018 ዓ.ም🇪🇹

በተፈሪ መኮንን ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ የትብብር ስልጠና ጥራት ለማሳደግ ሰልጣኞች በትብብር ስልጠና ወቅት የሚያጋጥሙአቸውን የኢንድስትሪ ነባራዊ ሁኔታ በማስገንዘብ እራሳቸውን ዝግጁ እንዲያደርጉና ያልተረድት ሀሳብ እና አሰራር ካለ ግልጽ ለማድረግና አላማውን እንዲርዱት የሚያስችል ነው ።

የኮሌጅ አ/ጉ/ም/ዲ አቶ ደምበላሽ ተስፋዬ ሰልጣኞች በኮሌጁ የነበራቸውን የቆይታ ጊዜ የጨረሱ ሲሆን ወደ ትብብር ስልጠና ከመሄዳቸው በፊት በትብብር ስልጠና ወቅት ከሰልጣኝ ምን እንደሚጠበቅ፣ማሟላት ያለባቸው ቅድመ ሁኔታዎች እና መተግበር የሚገባቸው የስራ ስነ ምግባር ኦረንቴሽን አስፈላጊ መሆኑን ገልፀዋል ።

ትብብር ስልጠና የሚወጡ ሰልጣኞች ለአንድ ወር በካምፖኒ የስራ ላይ ስልጠና መውሰድ እንዳለባቸውና በስምንቱም የብቃት አሀዶች ውጤታቸውን አስሞልተው በተቀመጠው ጊዜ ማምጣት እንዳለባቸው የተገለፀላቸው ሲሆን ሰልጣኞች ለትብብር ስልጠና ሲሄድ መያዝ ያለባቸው የውል ደብዳቤ ፣ የብቃት አሀድ ፣ አቴንዳንስ እና የውጤት ማስሞያ ተዘጋጅቶ ተሰቷቸዋል ።

መረጃዎችን በፍጥነት ለማግኘት ማሰፈንጠሪያውን ይጫኑ!
https://vm.tiktok.com
https://t.me/EntotoPtc1917
https://youtube.com/
https://www.facebook.com
ከኮሚኒኬሽን ቡድን

09/03/2026

ባሳለፍነው ሳምንት

Photos from Entoto PTC.tms's post 07/03/2026

በተፈሪ መኮንን ፖሊቴክኒክ ኮሌጅ የሳንፎርድ ት/ቤት ተማሪዎች ጉብኝት አደረጉ ።
🇪🇹27/06/2018 ዓ.ም🇪🇹
በተፈሪ መኮንን ፖሊቴክኒክ ኮሌጅ የእስቴቲክስ የስልጠና ዘርፍ ጉብኝት ያደረጉት የሳንፎርድ ት/ቤት የ10 እና 11 ክፍል ተማሪዎች ለስልጠና የሚውል አላቂ እቃዎችን ለኮሌጁ አ/ጉ/ም/ዲ አቶ ደምበላሽ ተስፋዬ በኩል አስረክበዋል ።ተማሪዎቹም እንደገለፁት አላማ አድርገው የተነሱ የአርት ሰዎችን በሀገራችን የሚሰጣቸውን ትኩረት ለመጨመር መሆኑን ገልፀው ።
በኮሌጅ የነበራቸው ጉብኝት ለተቋሙ ድጋፍ ለማድረግ እንዳነሳሳቸውና በቀጣይ ባላቸው የተማሪዎች ድረገፅ ኮሌጁን የማስተዋወቅ ስራ እንደሚሰሩ አስታውቀዋል ።
የኮሌጅ አ/ጉ/ም/ዲ አቶ ደምበላሽ ተስፋዬ ድጋፍ ያደረጉትን የሳንፎርድ ት/ቤት ተማሪዎች አመስግነው አገር ተረካቢ ዜጎች በዚህ ልክ አስበው ባደረጉት አስተዋፅዎ ኮሌጁ ስልጠና ለሚፈልጉ ተማሪዎች በእስቴቲክስ የስልጠና ዘርፍ ስልጠና እንደሚመቻችላቸው ገልፀዋል ።
መረጃዎችን በፍጥነት ለማግኘት ማሰፈንጠሪያውን ይጫኑ!
https://vm.tiktok.com
https://t.me/EntotoPtc1917
https://youtube.com/
https://www.facebook.com
ከኮሚኒኬሽን ቡድን

Want your university to be the top-listed University in Addis Ababa?
Click here to claim your Sponsored Listing.

Address


Gulele
Addis Ababa
1033