Gurage Fact Page
15/04/2026
!!
በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ርዕሰ መስተዳድር እንዳሻው ጣሰውና የ"ሂላሪ ክሊንተን" ስትራቴጂ በደም እምባ ላይ የሚደረግ የድል ሽሚያ!
የፖለቲካ ሰዎች የሕዝብ ድጋፍ ሲርቃቸውና የገቡበት አዙሪት ሲጠባቸው የማያደርጉት ጥረት የለም። ሂላሪ ክሊንተን በምርጫ ወቅት የደጋፊዎቿ ቁጥር ሲቀንስና ተቃውሞ ሲበረታባት፣ የሕዝቡን ስሜት ለመግዛት ወደ ስታዲየሞች እየሄደች በማጨብጨብ "እኔም ከእናንተ ጋር ነኝ" ለማለት ያደረገችው ሙከራ የብዙዎች መሳለቂያ ሆኖ ነበር። ዛሬ በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ርዕሰ መስተዳድር የምናየው ድራማም ከዚህ የተለየ አይደለም።
ከቤተ እምነት እስከ ስታዲየም፤ የትኛው ነው የልብ ትርታ?
የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር ባለፉት ወራት የገጠማቸውን ሕዝባዊ ተቃውሞና የቅቡልነት ጥያቄ ለማለዘብ ያልረገጡት ደጅ የለም።
➧ አንዴ ቤተክርስቲያን...
➧ አንዴ መስጂድ...
➧ አንዴ ቸርች...
➧ አሁን ደሞ እስታዲየም...
ይህ ሁሉ ጥረት ግን ከልብ የመነጨ ሳይሆን የፖለቲካ ትኩሳቱን ለማቀዝቀዝ የሚደረግ "የመንፈሳዊ ካባ" ፍለጋ እንደሆነ ግልጽ ነው።
ዛሬ ደግሞ የሀላባ እግር ኳስ ክለብ ወደ ኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ማለፉን ተከትሎ፣ የእንኳን ደስ አላችሁ መልዕክት በማጋራት የደጋፊውን ስሜት ለመጋራት እየሞከሩ ነው።
ለመሆኑ ስፖርትና ግድያ አብረው ይሄዳሉ?
በክልሉ ንጹሐን ዜጎች በግፍ እየተገደሉ፣ ወጣቶች ያላግባብ በየእስር ቤቱ እየታጎሩና ሕዝቡ በከፍተኛ የጸጥታ ስጋት ውስጥ እያለ፣ በኳስ ደጋፊ ስም ተሸሽጎ "የሕዝብ ሰው" ለመምሰል መሞከር ተገቢ ነውን?
1. ፍትህ የታለ? ንጹሐን ደማቸው እየፈሰሰ ባለበት ሁኔታ፣ በእግር ኳስ ውጤት የሕዝቡን ቁስል መሸፈን አይቻልም።
2. ፖለቲካዊ ቁማር፡ ስፖርት አንድነትን ይፈጥራል፤ ነገር ግን በፖለቲከኞች እጅ ሲወድቅ የውድቀት መደበቂያ ይሆናል።
3. የሕዝብ ጥያቄ፡ የሀላባ ሕዝብም ሆነ የክልሉ ነዋሪ የሚፈልገው ኳስ ብቻ ሳይሆን ሰላም፣ ፍትህና ነጻነት ጭምር ነው።
በእግር ኳስ ደጋፊ ስም መሸሸግ፣ በሃይማኖት ተቋማት ፎቶ መነሳት የሕዝብን እውነተኛ ጥያቄ አይመልስም። ሕዝቡ የሚፈልገው በፎቶግራፍ የሚታይ መሪ ሳይሆን፣ የንጹሐንን ግድያ የሚያስቆም፣ ፍትህን የሚያሰፍንና ሰላምን የሚያረጋግጥ መሪ ነው።
በሀላባ ድል ደስ ብሎናል እንኳን ደስ አላቹ! የሀላባ ክለብ ድል የሕዝብ ነው! የፖለቲከኞች የውድቀት መሸፈኛ ግን መሆን የለበትም!
እውነተኛ አንድነት በስታዲየም ፎቶግራፍ የሚመጣ ሳይሆን፣ በሕዝቦች መካከል እኩልነትና ፍትሕ ሲሰፍን ብቻ ነው። የሀላባ ወንድሞቻችን የኳስ ድል የናፈቃቸው ያህል፣ የመስቃን ህዝብ ሰላምና ፍትሕም ናፍቆናል!
የጭቁኑ የመስቃን ህዝብ ድምጽ!
09/04/2026
⚖️ ፦ !
በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ርዕሰ መስተዳድር እንዳሻው ጣሰው እና አማካሪያቸው ንጉሴ አስረስ የሚታየው አምባገነናዊ አካሄድና በፍትህ ስርአቱ ላይ የሚደረገው ጣልቃ ገብነት አሳሳቢ ደረጃ ላይ ደርሷል። ያለምንም ወንጀል ከቤተሰቦቻቸውና ከመኖሪያቸው (ቡታጅራ) ተነጥቀው ወደ ሆሳና የተወሰዱት የመስቃን ጉራጌ ተወላጆች፦
1➧ አቶ ፈይሰል አወል
2➧ አቶ ሸይቾ ኢብራሂም
3➧ አቶ ቶፊቅ አወል
በህግ ጥላ ስር ከዋሉ ዛሬ ሐሙስ ሚያዝያ 1/2018 ዓ.ም 26ተኛ ቀናቸውን ይዘዋል። ዛሬ በነበራቸው 4ኛ ዙር ቀጠሮ መሠረት ፍርድ ቤት ቀርበው መርማሪው የዋስትና መብታቸው እንዳይከበር ተጨማሪ ቀጠሮ እንዲሰጠው መከራከሪያ ቢያቀርብም ፍርድ ቤቱ ግራ ቀኙን አይቶ ዋስትና ያሰጣል አያሰጥም የሚለውን ለመወሰን ለ8 ሰዓት ቀጠሮ የሰጠ ቢሆንም 8ሰዓት ፍ/ቤት ቀርበው መዝገቡ እጣ ይውጣበት በሚል ለሚያዝያ7/2018 ተለዋጭ ቀጠሮ ተሰቶባቸዋል። ይህ የሚያሳየው አሁን መዝገባቸው ከያዘው ዳኛ ነጥቆ እንደፈለገ ለሚታዘዛቸው ዳኛ ለመስጠት መዝገቡ እጣ ይውጣበት በሚል ቀጠሮ መስጠት የፍትህ ስርአቱ እንደፈለጉ ጠምዝዘው እያጨመላለቁት ነው።
መርማሪው አቃቤ ህግ እስካሁን ድረስ የቀረበባቸውን ክስ የሚያረጋግጥ ምንም አይነት ተጨባጭ መረጃ ማቅረብ ባልቻለበት ሁኔታ፣ ፍርድ ቤቱ በባለስልጣናት ቀጥተኛ ትዕዛዝ የዋስትና መብታቸውን ነፍጎ በእስር እንዲንገላቱ እያደረገ ይገኛል።
➡️ የፍትህ ነጻነት ይከበር፦ የክልሉ ርዕሰ መስተዳድርና አማካሪዎቻቸው የፍትህ አካላትን በስልጣን ሀይል መጠምዘዝ ያቁሙ! ፍርድ ቤት የፖለቲካ መጫወቻ መሆኑ ይብቃ።
➡️ መረጃ የሌለው ክስ ይቋረጥ፦ አቃቤ ህግ ማስረጃ ማቅረብ ያልቻለባቸው ግለሰቦች በነፃ እንዲሰናበቱና የዋስትና መብታቸው እንዲከበር እንጠይቃለን።
➡️ የቤተሰብ ስቃይ ይብቃ፦ ግለሰቦቹን ከቀያቸው አርቆ በማሰር ቤተሰቦቻቸው ለከፍተኛ እንግልትና ላልተፈለገ ወጪ እየተዳረጉ ነው። ይህ ሰብአዊነት የጎደለው ድርጊት በአስቸኳይ ይቆም!
➡️ ተገቢው ካሳ ይከፈል፦ ያለ አግባብ የታሰሩ ወገኖቻችን በደረሰባቸው ስነ-ልቦናዊና ኢኮኖሚያዊ ጉዳት ተገቢው ካሳ ሊከፈላቸው ይገባል።
"ህግን የሚጥሱ ባለስልጣናት ራሳቸው ከህግ በላይ ሊሆኑ አይችሉም!"
የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር እና አማካሪያቸው በንፁሃን ዜጎች ላይ እያደረሱ ያለውን አፈና እንዲያቆም እና የህግ የበላይነትን እንዲያረጋግጥ በፅኑ እናሳስባለን። ድምጻችንን ለፍትህ እናሰማ!
የጭቁኑ የመስቃን ህዝብ ድምፅ!!
07/04/2026
ብልፅግና ፓርቲ ከለውጡ በፊት የገመገመው አንዱ ችግር የሀገሪቷ መዋቅራዊ ጭቆና እና ሰው ተኮር ጭቆና የሚል ነበር።
ኢህአዴግ ወለዶቹ እንደሻውና ንጉሴ አስረስ ሁለቱንም የጭቆና አይነቶች በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል እየተገበሩ ይገኛሉ።የፓርቲ ሚዲያን ከ2ሚሊየን እና ከዚያ በላይ ያለውን አባላት የፓርቲ አባላት ንብረት የሆነውን የክልሉ ፓርቲ ሚዲያ እና ከ258k በላይ ያለውን ተከታይ ለአንድ ግለሰብ በነጋ በጠባ የእንደሻው ጣሰው ፕሮፋይል መገንባ ሆኖ አርፎታል።
ይህ አንደኛ መዋቅራዊ ጭቆና ይባላል የፓርቲውን ሚዲያ በመጠቀም የግል መፈንጫ ሆኖ በመዋቅር ደረጃ በተለይም በምስራቅ ጉራጌ ዞን ባሉ መዋቅሮች ከፓርቲው በቀጥታ ትዕዛዝ እየተላለፈ አለፍ ሲልም ደግሞ በመዋቅር ደረጃ የግለሰቡን የግል ስብዕና መገንባ የአክቲቭዝም ፖለቲካ ማካሄጃ እንዲሆን እየሰራ ያለ የተዋረደ ሚዲያ ሆኖ አርፎታል።
ሌላው ሰው ተኮር ጭቆናም የሆነበት በግል ደረጃ በእንደሻው ጣሰውና በጓደኛውና በአብሮ አደጉ የክልል ሚዲያ ኃላፊው አቶ ሰብስቤ ተካ አማካኝነት ሰው ተኮር ጭቆናው በመስቃንና መሰል ጭቁን ሕዝቦች ላይ አሳርፈዋል።ከፓርቲው እሳቤ በመውጣት የግል ዝናና ታሪክ መተረኪያ ሆኖ እንዲያርፍ የፓርቲው ሚዲያ የእንደሻው አክቲቪስት እና ስብዕና መገንቢያ ሆኖ እንዲያገለግል አድርገውታል።
አጠቃላይ የክልሉ አመራር በእንደሻው ስብዕና ግንባታ ላይ እንዲጠመድ በእንደሻው ቀጭን ትዕዛዝ ተሰጥቶ አመራሩ ከልማት አጀንዳው ተነጥሎ ተወጥሯል።
የፓርቲው ሚዲያ የእንደሻው የግል አክቲቪስትነት ወጥቶ የፓርቲውን እሳቤ ልማት የሚያጎሉ ነገሮች እንዲሰራ የፌደራሉ ፓርቲ እንዲፈትሽ እንጠይቃለን።
በአንድ ወገን የተጠረነፈው የፓርቲው ሚዲያ አደብ እንዲገዛ እናሳስባለን።የፓርቲው ሚዲያ ልማትና ፍትህ ላይ መስራት ሲገባው በየቀኑ የግለሰብ የእንደሻው ስብዕና ግንባታ ማዕከልነት መጠመዱን የሚያመላክቱ መረጃዎች ያሳያሉ።
አመራር ስራው ምድር ላይ ሊመሰክር ሲገባው ያልሆነ ስብዕና በሚዲያ ስሜ ጠፋ ስነ ልቦናዬ ተጎዳ በሚል በእንደሻው ትዕዛዝ አመራሩ የእንደሻው የግል አክቲቪስት ሆኖ አርፎታል።አመራሩ የልማት አጀንዳዎችን ከመመለስ ይልቅ ሙሉ ሰዓቱን በሶሻል ሚዲያ የእንደሻው ፕሮፋይል ለመገንባት ጊዜውን እያባከነ ይገኛል።ሰሚ ያጣው ክልል ዶር አብይ እንዲመለከቱት እናሳስባለን።
ሶስት ቀን ባለሞላው ውስጥ ብቻ ከአምስት በላይ ፖስት ያውም በአንድ ቀን እና ባላነሰ ቀናቶች ክልሉ አግላይነትና የግለሰብ መፈንጫ መሆኑን የሚያመላክቱ መረጃዎች ያሳያሉ።
ፍትህ ለታሰሩ እስረኞች።
04/04/2026
!!
ማህበራዊ ሚዲያ እንደ አራተኛው መንግስት እና የክልል አስተዳደር ተግዳሮቶች
በዘመናዊው የአስተዳደር ስርዓት፣ ማህበራዊ ሚዲያ “አራተኛው መንግስት” በመባል ይታወቃል። ከሦስቱ የመንግስት አካላት (ህግ አውጪ፣ አስፈፃሚና ዳኝነት) በተጨማሪ፣ ማህበራዊ ሚዲያ ለዜጎች አስተያየታቸውን እንዲገልጹ፣ በአመራሮች ላይ ክትትል እንዲያደርጉ እና የህዝብ ጥያቄዎችን እንዲያነሱ መድረክ ይፈጥራል።
በዚህ መልኩ፣ ለማንኛውም የህዝብ ተወካይ ወይም የክልል ርዕሰ መስተዳድር እንዳሻው ጣሰው፣ ህዝብ በማህበራዊ ሚዲያ ላይ የሚሰነዘሩባቸው ትችቶችን መቀበል የዲሞክራሲ ክብር እና የኃላፊነት መገለጫ ወደ ጎን ብለው፣ በመረጃ በተግባር አምባገነንነታቸው ሲጋለጥ፣ የመምራት ብቃት ማነስ፣ ሚዛናዊነት መጓደል፣ ትችት ሲደርስባቸው ከማስተካከል ይልቅ ወደ መከላከያ ዘዴዎች ማፈግፈግ የመሸነፍ መገለጫ ነው።
በርዕሰ መስተዳድር እንዳሻው ጣሰው እና አማካሪያቸው ንጉሴ አስረስ ላይ የሚነሱ ተደጋጋሚ ጥያቄዎች የሚከተሉትን ያካትታሉ፦
1. የርዕሰ መስተዳድሩ የእውቀት ብቃት እና የመምራት አቅም ማነስ፦ የህዝብ አገልግሎት ዘርፍ የፍትህ ስርዓት መዛባት፣ ግፍና ጭቆና እያደገ በሚሄድ ውስብስብ ሁኔታ ውስጥ፣ አመራሮች ዘመናዊ የአስተዳደር እውቀትና ችሎታ ማነስ በክልሉ የፈጠራቸው ቀውሶች የሚቀርቡባቸውን ትችቶች ተቀብሎ ማረም አለመቻል። ይህ ጉድለት በክልሉ ህዝብ አገልግሎት አሰጣጥ፣ ሰላም ደህንነት እንቅፋት ሆነዋል።
2. የርዕሰ መስተዳድሩ ብልሹ አሰራር፦ የህዝብ ሀብት አያያዝ ግልጽነትና ተጠያቂነት መጓደል ያጋልጡኛል የሚሏቸው እያሳደዱ ማሰር፣ እየገደሉ አጀንዳ ለማስቀየር አፍ ለማዘጋት፣ ለማሸማቀቅ መሞከር፣ የከልሉ ብልሹ አሰራርና ሙስና የመከሰት እድል አስፍቶት ኢኮኖሚያዊ እና ማህበራዊ ቀውስ አስከትሏል።
3. ትችትን አለመቀበል፦ የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ርዕሰ መስተዳድር እንዳሻው ጣሰው እና አማካሪያቸው ንጉሴ አስረስ በመስቃን ህዝብ ላይ ግፍና መከራ እያዘነቡበት፣ እየገደሉት፣ እያፈናቀሉት፣ እያሳደዱ እያሰሩት ያለውን ጥፋታቸውን በማህበራዊ ሚዲያ መጋለጥ ትችት እንደ ጦር ፈርተው ለመሸፈን ሲሉ፣ “በኢንተርኔት መስኮት የኢትዮጵያ ችግር አይፈታም” የሚሉ መግለጫዎችን ለአመራሮቻቸው ትዛዝ ሰተው ቻሌንጅ አስጀምረዋል። በኢንተርኔት መስኮት የኢትዮጵያ ችግር አይፈታም የሚለው እውነት ካመኑበት በክልሉ ስር ለሚገኙ መዋቅሮች አመራሮች ትዛዝ ሰተው ቻሌንጁ እንዲቀላቀሉ የአድኑኝ ትዛዝ ለምን ሰጡ? እርስ በራሱ የሚጣረስ የሚያደርጉትን የማያቁት፣ የመደመር መርህ የጣሱ ብልፅግናን በቁሙ እየናዱ ማሸነፍ አይቻልም። ይህ አካሄድ በቀጥታ ትችትን ከመቀበል ያፈነግጣል እንጂ ችግሩን አይፈታም።
ማህበራዊ ሚዲያ በራሱ ብቻ ችግር አይፈታም የሚለው ሃሳብ እውነት ቢሆንም፣ እውነትን በማጋለጥ ዜጎች በእሱ አማካኝነት የሚያነሷቸው ትክክለኛ ጥያቄዎች ግን መስማት አለባቸው። ትችትን ከማስተካከል ይልቅ በማጥቃት ወይም በማቃለል መልስ መስጠት፣ የህዝብን በደልና ጭቆና የሚያሳይ አሉታዊ ባህል ነው።
ስለዚህ የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ርዕሰ መስተዳድር እና አማካሪያቸው አምባገነናዊ የአስተዳደር አካላት ገንቢ ትችቶችን በክብር መቀበልና ማረም አለመቻል በጎሰኝነት መታወር፣ ድክመቶቻቸውን በግልጽ ማስተካከል አለመቻል የህዝብን እምነት ማጎልበት አለመቻላቸው የፌደራል መንግስት ጣልቃ ገብቶ የክልሉ ሰላም ደህንነት እንዲያረጋግጥ እንጠይቃለን።
የጭቁኑ የመስቃን ህዝብ!!
Click here to claim your Sponsored Listing.
Website
Address
Addis Ababa