Gohe Tv Broadcasting service
23/01/2024
ኢትዮቴሌኮም በ2016 በጀት ዓመት መንፈቅ 43 ቢሊዮን ብር አጠቃላይ ገቢ ማግኘቱን ገለፀ።
መንግስታዊው የቴሌኮም አገልግሎት አቅራቢ ኢትዮ ቴሌኮም፤ ባለፈው መንፈቅ ዓመት 42.9 ቢሊዮን ብር ገቢ ማግኘቱን አስታወቀ። ኢትዮ ቴሌኮም በዚሁ ጊዜ ውስጥ የደንበኞቹን ቁጥር 74.6 ሚሊዮን መድረሱንም ገልጿል።
ኢትዮ ቴሌኮም ይህን የገለጸው የ2016 በጀት ዓመት የመጀመሪያ ግማሽ ዓመት የስራ አፈጻጸሙን አስመልክቶ በሰጠው ጋዜጣዊ መግለጫ ነው። ተቋሙ በዚህ ጊዜ ውስጥ ያስገባው ገቢ፤ ከእቅዱ 98 በመቶውን ያሳካ መሆኑን የኩባንያው ዋና ስራ አስፈጻሚ ወ/ሪት ፍሬሕይወት ታምሩ ተናግረዋል።።
ገቢው ካለፈው ዓመት ተመሳሳይ ወቅት ጋር ሲነጻጸር 26 በመቶ ዕድገት ያሳየ መሆኑንም ዋና ስራ አስፈጻሚዋ ገልጸዋል። ኢትዮ ቴሌኮም በ2015 የመጀመሪያ ግማሽ ዓመት ያገኘው ገቢ 33.8 ቢሊዮን ብር ሲሆን በወቅቱ ያስመዘገበው ትርፍ ደግሞ 8.18 ቢሊዮን ብር ነበር። ተቋሙ ዘንድሮ በግማሽ ዓመት ብቻ 11 ቢሊዮን ብር ትርፍ ማግኘቱም ይፋ ተደርጉዋል።
21/12/2023
በኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት አስተዳደር እና በኢሚግሬሽንና የዜግነት አገልግሎት መካከል የኢ-ፓስፖርት ሥርዓትን ከዲዛይን ጀምሮ ደህንነትን መሰረት ያደረገ የሲስተም ግንባታ ላይ በጋራ መስራት የሚያስችል ስምምነት ተፈረመ።
ስምምነቱ የ24/7 የሳይበር ደህንነት ጥበቃ አገልግሎትን እንደሚያካትትም ተመላክቷል።
በስምምነቱ ላይ የኢመደአ ዋና ዳይሬክተር አቶ ሰለሞን ሶካ ባስተላለፉት መልዕክት ኢመደአ የኢንፎርሜሽንና የኢንፎርሜሽን መሠረተ-ልማት ደህንነት መጠበቅ ኃላፊነቱና ተልእኮው መሆኑን ገልጸዋል።
በዚህም ለመንግስት ቁልፍ ተቋማትን የ24/7 የደህንነት ጥበቃ ከማድረግ ባሻገር ክልከላ ያለባቸውን ሶፍትዌሮችና ሀርድዌሮችን አበልጽጎ የማስታጠቅ ሥራን እየሠራ እንደሚገኝም አክለዋል፡፡
አቶ ሰለሞን አያይዘውም ዛሬ የተደረገው ሥምምነት የኢ-ፓስፖርት ሥርዓትን ከዲዛይን ጀምሮ ደህንነትን መሰረት ያደረገ የሲስተም ግንባታና የ24/7 የሳይበር ደህንነት ጥበቃ አገልግሎትን መስጠት የሚያስችል ነው ብለዋል።
በተጨማሪም የሳይበር ደህንነት ኦዲት፣ አገልግሎቱ ያሉበትን የሳይበር ደህንነት ሥጋትና የተጋለጭነት ክፍተቶችን የመለየትና የመድፈን ስራዎችን በመስራት ተቋሙ የጀመረዉን በቴክኖሎጂ የመዘመን እንቅስቃሴ የሚደግፍ መሆኑን ጠቁመዋል።
በመግባቢያ ስምምነቱ መሰረት የኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት አስተዳደር ለኢሚግሬሽንና የዜግነት አገልግሎት የቴክኒክ ድጋፍ እንደሚያደርግ ገልጸዋል።
የኢሚግሬሽንና የዜግነት አገልግሎት ዋና ዳይሬክተር ወይዘሮ ሰላማዊት ዳዊት በበኩላቸው ከኢመደአ ጋር በጋራ ለመስራት መስማማታቸው እንዳስደሰታቸዉ ገልጸዋል።
ተቋማቸው የሚሰጠውን አገልግሎት በማዘመን የኢ-ፓስፖርት አገልግሎት ለመስጠት እና ተቋሙ በባህሪው የሚይዛቸው መረጃዎች ሚስጥራዊነት እና ደህንነታቸው የተጠበቀ እንዲሆን ከኢመደአ ጋር መሥራት አማራጭ የሌለው ጉዳይ መሆኑን ጠቁመዋል።
ወደፊትም በርካታ ሥራዎችን በጋራና በትብብር እንደሚሰሩ ዋና ዳይሬክተሯ መግለጻቸውን ከኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት አስተዳደር የተገኘው መረጃ ያመላክታል፡፡
20/12/2023
የአፍሪካ ሀገራት የኤሌክትሮኒክ አስተዳደርና የዲጂታላይዜሽን ምክክር መድረክ በሩሲያ እየተካሄደ ይገኛል
****
(ኢ ፕ ድ)
በሩሲያ ሞስኮ እየተካሄደ በሚገኘው መድረክ የአፍሪካ ሀገራት ቴክኖሎጂን በመጠቀም በሀገራቸው የሚካሄደውን የኢኮኖሚ ስርዓት ለማዘመን የሄዱበትን የስኬት ጉዞና ተግዳሮቶችን ለመቅረፍ ለሚደረጉ የቴክኖሎጂ ሽግግሮች ተሞክሮ ይቀርብበታል።
ኢትዮጵያን ወክለው በመድረኩ እየተሳተፉ የሚገኙት የአብርሆት ቤተ-መጽሐፍት ዋና ዳይሬክተር ውባየሁ ማሞ (ኢ/ር) የኢትዮጵያን የዲጂታል መታወቂያ አሰጣጥ፣ የኤሌክትሮኒክ ግብይቶችንና ኢትዮጵያ ዲጂታል ኢኮኖሚን ለመገንባት የምታደርገውን ጥረት በተሞክሮነት አቅርበዋል።
በጉባዔው የአፍሪካ ሀገራት ከሩሲያ የዲጂታል ኢኮኖሚ ግንባታ ተሞክሮዎችን በመውሰድ አዳዲስ የቴክኖሎጂ አሰራሮችን ተግባራዊ ያደርጉበታል ተብሎ ይጠበቃል።
በመድረኩ 37 የአፍሪካ ሀገራት ተሳትፎ እያደረጉ መሆኑ ታውቋል።
20/12/2023
ትላንት በተደረገ የካራባዉ ካፕ ጨዋታ ቼልሴ ፤ፉልሃም እና ሚድልስቦሮዉ ወደ ግማሽ ፍፃሜ ማለፍቸዉን አረጋግጠዋል፡፡
በካራባዉ ካፕ ሩብ ፍፃሜ ጨዋታ ትላንት ሶስት መርሃ ግብሮች የተካሂዱ ሲሆን ቼልሲ ፣ ፉልሃምና ሚድልስቦሮዉ ወደ ግማሽ ፍፃሜ ያለፉ ክለቦች መሆን ችለዋል፡፡
ከተጠባቂ መርሃ ግብሮች መካከል የነበረዉ የቼልሲ እና የኒዉካስትል ዩናይትድ ጨዋታም በመለያ ምት ቼልሲወች አሸንፈዉ ወደ ቀጣዩ ዙር ማለፍ ችለዋል፡፡
ኒዉካስትል ዩናይትድች በዚህ ጨዋታ ላይ ዊልሰን ቀድሞ ባስቆጠራት ጎል ቀድመዉ መሪ የሆኑበትን እድል ቢያገኙም ቼልሲወች ደቂቃወች ሊጠናቀቁ በሰከንዶች ልዩነት ጎል አስቆጥረዉ ወደ ጭማሪ ደቂቃ ያለፈበትን እድል ማስተካከል ችለዋል፡፡ ሙሉ የጭዋታዉ ጊዜ በአንድ አቻ የተጠናቀቀዉ ይህ ጨዋታም በመጨረሻም ቼልሲወች በመለያ ምት አሸንፈዉ ግማሽ ፍፃሜዉን ተቀላቅለዋል፡፡
ሌላኛዉ መርሃግብር የኢቨርተን እና የፉልሃም ጨዋታ በተመሳሳይ በመለያ ምት የተጠናቀቀ መርሃ ግብር ነበር፡፡
ኤቨርተኖች የፍይናሻል ፊር ፕላይ ህግን በመጣሳቸዉ አስር ነጥብ ከተቀነሰባቸዉ በኅላ ይበልጥ ጠንካራ ሆነዉ ለመቅረብ እየታገሉ ይገኛሉ ፡፡ በምሽቱ ጨዋታም ማይክል ኪን በራሱ መረብ ላይ ከረፍት በፊት ጎል አስቆጥሮ ፍልሃሞችን መሪ ያደረገ ቢሆንም ቤቶ በመጨረሻም ለኢቨርተን ጎል አስቆጥሮ ወደ ጭማሪ ደቂቃ ማምራት ችለዉ ነበር ፡፡ ጭማሪ ደቂቃወች ጨርሰዉ ወደ ፔናሊቲ ያመሩት ሁለቱ ክለቦች ኦናና እና ጎዩ የኢቨርተንን ሁለት ፔናሊቲወችን አምክነዉ ፍልሃሞች ወደ ግማሽ ፍፃሜዉ ሲያልፉ በተቃራኒዉ ኢቨርተኖች ወደ ግማሽ ፍፃሜዉ ሳያልፉ ቀርተዋል፡፡
ሜድልስቦሮዉ እና ፓርት ቫሊ ያደረጉት ጨዋታ በሚድልስቦሮዉ 3-0 አሸናፊነት ተጠናቋል፡፡
ዛሬም በካራባዉ ካፕ ሩብ ፋፃሜ ጨዋታ አንድ ቀሪ መርሃ ግብር ይደረጋል፡፡ በዚህ ጨዋታም ሊቨርፑል ዊስትሃምን በአንፊልድ ይጋብዛል፡፡ ሊቨርፑል በዘንድሮዉ የዉድድር አመት ወደ ሻንፒወን ሽፑ የተወረወረዉን ሊስተርሲቲን አሸንፎ ወደ ሩብ ፍፃሜዉ ማለፉ ይታወሳል፡፡ የሊግ ዋንጫዉን ያነሳል ተብሎ ከሚገመቱ ክለቦች መካከል የየርገን ክሎፕ ቡድን የመጀመሪያዉ ነዉ፡፡ በተቃራኒዉ ውስትሃም ዩናይትድ የሊቨር ፑል ቀላል ተጋጣሚ እንደማይሆን ይጠበቃል ፡፡ ጠንካራዉን አርሰናልን በሰፊ የጎል ልዩነት አሸንፎ ወደ ሩብ ፍፃሜዉ ማለፉ ይታወሳል፡፡ ታዲያ ሁለቱ ክለቦች ዛሬ ምሽት አምስት ሰዓት ላይ በአንፊልድ ወደ ቀጣዩ ዙር ለማለፍ የሚፍለሙ ይሆናል፡፡
Click here to claim your Sponsored Listing.
Category
Contact the business
Address
Addis Ababa