Kingship Christians Partnership Network
22/09/2016
ይድረስ ለደቀ መዝሙር – መጽሐፉ አላረጀም – deqemezmur ቤተ ክርስቲያን • ትኩረት ይድረስ ለደቀ መዝሙር – መጽሐፉ አላረጀም 27 mins agoby DeqemezmurAdd Comment4 Views ይድረስ ለደቀመዝሙሩ – መጽሐፉ አላረጀም በሥራ ጉዳይ አንዲት እንግዳ ከወደ እንግሊዝ አዲስ አበባ መጥታ ተገናኘን፡፡ የመጣች እለት አብረን ምሳም ልንበላ ወደ አንድ ምግብ ቤት ገባን፡፡ ከእንግዳዬ ጋር ምሳ እየበላን ብዙ ጉዳዮችን አነሳን ጣልን፡፡ ስለ ሥራ፣ አብረውኝ ስለሚሰሩ ሰዎች ሁናቴ፣ ስለ እንግሊዝ ፕሪመርሊግ፣ ስለ እንግሊዝ እና…
አንድነት፡፡ አንድ ልብ መሆን፡፡ በመቀባበል አንድን ጉዳይ ዳር ማድረስ፡፡ በአብ እና በወልድ መካከል እንዳለ አንድነት አንድ እንሆን ዘንድ ጌታ ኢየሱስ ስለ ተከታዮቹ እንዲጸልይ ያደረገው ጉዳይ፡፡ አንድነት፡፡................
የወንጌል አማኝ ክርስቲያኖች በርካታ መገለጫዎች አሉን፡፡ ከመገለጫዎቻችን መካከል አንዱ በየሄድንበት ህብረት ለመፍጠር የምናደርገው ጥረት አንዱ ነው፡፡ ተማሪዎች ሲገናኙ ህብረት ያደርጋሉ፣ ነጋዴዎች ሲገናኙ ህብረት ያደርጋሉ፣ ሰራተኞች ሲገናኙ ህብረት ያደርጋሉ፣… ወዘተ፡፡
እኛ አማኞች በተገናኝንበት የሥራ ቦታ ሆነ መንደር ህብረት ለማድረግ ጥረት በማድረግ እንታወቃለን፡፡ ይህ ህብረትን የመፈለግ መንፈስ በእያንዳንዱ አማኝ ላይ ጎልቶ የሚታይ ነው፡፡
በግለሰብ ደረጃ ህብረትን የመፈለግ ጉዳይ ቢኖርም ክርስቲያኑን ማህበረሰብ በመወከል የሚሰሩ ተቋማት ግን ለህብረት የሚያደርጉት አስተዋጾ ጉልቶ አይታይም፡፡ ከህብረት እንቅስቃሴ ይልቅ ያልተቀናጀ ግለኛ የሆነ እንቅስቃሴ ይበዛል፡፡
በሀገራችን በርካታ የግብረሰናይ ድርጅቶች አሉ፡፡ እኒህ የልማት ግብረሰናይ ድርጅቶች ህብረትን በመፍጠር ወይንም Consortium በመፍጠር ስራዎችን ይሰራሉ፡፡ ይህ አይነቱ አብሮ የመስራት ባህል በቤተክርስቲያን ዙሪያ ግን አይታይም፡፡ አንድን ጌታ እያመለክን፣ አንድ አይነት ዝማሬ እየዘመርን፣ ተመሳሳይ በሆነ አካሄድ ላይ ተገኝተን፣ … ነገር ግን በህብረት ስራዎችን የመስራት ባህላችን ደካማ ነው፡፡
ይህን ድካም የፈጠረው ምንጩ የእውቀት ማነስ ይሁን መንፈሳዊ ተጽእኖ በእርግጥ ሊመረመር ይገባል፡፡ ምክንያቱ መንፈሳዊ ተግዳሮት ከሆነም በጸሎት፣ የእውቀት ማነስም ከሆነ ስለ ህብረት አስፈላጊነት ከመጽሐፍ ቅዱሳችን ከመማር፣ የራስን ክብር ከመፈልግ ከሆነም በግሳጼ … ልንፈታው ይገባል፡፡
እኔ የእዚህ ነኝ እኔ የእዚያ ነኝ የሚለው ብዙም ጥቅም የለውም፡፡
የኢትዮጵያ ቤተክርስቲያን ዛሬ በእጆ ያለውን እድል ከመጣሏ በፊት በአንድነት ልትገመድ ይገባታል፡፡
መሪዎች ከራሳችሁ በላይ ከእናንተ በላይ የሆነውን የስራውን ባለቤት ተመልከቱ ለህብረት አጀንዳችሁን ክፈቱ፡፡
ወጣቱ ትውልድ ለአንድነት ቅድሚያ በመስጠት የተሻለ አገልግሎት ለማገልገል ሊሰራ ይገባዋል፡፡
እግዚአብሔር ኢትዮጵያን ይባርክ፣
ኪንግሽፕ
ኢየሱስን እንደ ግል አዳኝዎት የተቀበሉበትን ቀን ሲያስቡ ምን ይሰማዋታል?
Click here to claim your Sponsored Listing.
Category
Contact the place of worship
Website
Address
Addis Ababa