Rakeb Tech

Rakeb Tech

Share

ዩትዩብ እንዴት ነዉ የሚሰራዉ? | እሼ ምን ትላለህ | Comedian Eshetu 2022 | @Comedian Eshetu- OFFICIAL 23/06/2022

ዩትዩብ እንዴት ነዉ የሚሰራዉ? | እሼ ምን ትላለህ | Comedian Eshetu 2022 | @Comedian Eshetu- OFFICIAL eshetu መንገድ ላይ የአእምሮ ታማሚው አቀፈኝhttps://youtu.be/Svn8dhTu_94 የበርሊን ግንብ አያስቆምህም https://youtu.be/K1WuUXu5j0U አመስ...

23/06/2022

✳️ ለኮምፒውተር ቫይረስ ጥቃት መጋለጥዎን እንዴት ማወቅ ይችላሉ?

⚡️ስራዎችን ስናከናዉን የኮምፒዉተራችን ቀርፋፋ መሆን ፣ የተለያዩ አፕሊኬሽኖች አገልግሎት መቋረጥ እና የኮምፒዉተራችን በድንገት ስራ ማቆም አንዳንድ ጊዜ በቫይረስ የመጠቃታችን ምልክት ሊሆን ይችላል፡፡ ነገርግን እነዚህ ምልክቶች ብቻ ሁል ጊዜ በቫይረስ ለመጠቃታችን ማረጋገጫ አይሆኑም፡፡
በመሆኑም የእርስዎ ኮምፒውተር የቫይረስ ጥቃት ሰለባ መሆኑን ለማወቅ ከታች የተዘረዘሩ ምልክቶች በኮምፒዉተርዎ ሊስተዋሉ ይችላሉ፡-

🌀. ድንገተኛ የሆነ የአገልግሎት መቋረጥ፡ ከዚህ ቀደም ድንገተኛ የሆነ የአገልግሎት መቆራረጥ አጋጥሞዎት በተደጋጋሚ ሰማያዊ ቀለም ያለው ገጽታ የሚያሳይ ከሆነ ኮምፒውተርዎ አደጋ ላይ መውደቁን ጠቋሚ ነው፡፡

🌀. የኮምፒውተር ስርዓት ማዝገም /Slow System/፡ በሲስተምዎ ላይ ብዙ ቦታ የማይፈልጉ መተግበሪያዎችን(applications)ሳይጠቀሙ የኮምፒውተር ስርዓቱ ዝግ ማለት ካሳየ የኮምፒውተርዎ ስርዓት በቫይረስ መጠቃትን ሊያመለክት ይችላል።

🌀. ከልክ ያለፈ የሃርድ ድራይቭ እንቅስቃሴ( Excessive Hard Drive Activity) ምንም እንኳን ኮምፒተርዎ ስራ እየሰራ ባይሆንም ጥቂት የማይባሉ የሃርድ ድራይቭ እንቅስቃሴን ካስተዋሉ ይህ ምናልባትም በቫይረስ ስለመጠቃትዎ የማስጠንቀቂያ ምልክት ሊሆን ይችላል፡፡

🌀. ያልተለመዱ የዊንዶው ምልክቶች ሲስተዋሉ፡ ኮምፒውተርዎን በሚከፍቱበት ወቅት እንግዳ የሆኑ ነገሮች ብቅ ካሉ እና በተለይ በኮምፒተርዎ ላይ የተለያዩ ድራይቭዎች /drive/ ከጠፉ ችግር መፈጠሩን አመላካች ነው፡፡

🌀. ልዩ መልእክቶች፡ በተለያዩ መልእክቶች ወደ እርስዎ የመልእክት መለዋወጫዎች ሲገቡ እና ፋይሎችን በሚከፍቱበት ጊዜ ካልተከፈተ የተፈጠረ ችግር አለ ማለት ነው፡፡

🌀. መጥፎ የፕሮግራም እንቅስቃሴ፡- ፕሮግራሞችዎ ከጠፉ ፣ ከተበላሹ ፣ ወይም ያለ እርስዎ ፍቃድ እራሳቸውን በራሳቸው መክፈት ከጀመሩ ፣ እንዲሁም ያለ እርስዎ ትእዛዝ ኢንተርኔት ለመድረስ እየሞከሩ መሆኑን የሚገልጽ ማሳሰቢያ ከደረሰዎ ይህም የቫይረስ ሰለባ መሆንዎን ጠቋሚ ነው፡፡

🌀. የዘፈቀደ አውታረ-መረብ እንቅስቃሴ /Random Network Activity/ ምንም ጉልህ የሆኑ ፕሮግራሞችን ወደስራ ሳያስገቡ አልያም ከፍተኛ የበይነ-መረብ ዳታን በማይጠቀሙበት ጊዜ የእርስዎ ራውተር በቋሚነት ብልጭ ድርግም የሚል ምልክት የሚያሳይ ከሆነ ፣ የሆነ ችግር መፈጠሩን አመላካች ነው፡፡

🌀. የተሳሳቱ የኢ-ሜይል መልእክቶች፡- እርስዎ ለማንም ኢ-ሜይል ባይልኩም ከእርስዎ የኢ-ሜይል አድራሻ ለእርስዎ ኢ-ሜይል መልእክት ከደረስዎ የእርስዎ ስርዓተ ኮምፒውተር ተጥሷል (ወይም የኢ-ሜይል የይለፍ ቃልዎ እንደተሰረቀ የሚያሳይ ጠንካራ ማስረጃ ነው)

🌀. የአይፒ አድራሻዎ በበይነ-መረብ ፕሮቶኮል አድራሻ በጥቁር መዝገብ ከተቀመጠ/Blacklisted IP Address/ የእርስዎ የአይፒ አድራሻ በጥቁር መዝገብ መያዙን የሚገልጽ ማስታወቂያ ከደረሰዎት ኮምፒተርዎ በጥሩ ሁኔታ ላይ አለመሆኑን የሚያሳይ ምልክት፡፡

🌀. ያልተጠበቀ የፀረ-ቫይረስ አገልግሎት መቆም፡- ብዙ ተንኮል-አዘል ሶፍትዌር /malware/ ፕሮግራሞች ፀረ-ቫይረስ አገልግሎት የማስተጓጎል ወይም ከጥቅም ውጪ የማድረግ ተልእኮ በመያዝ የተቀየሱ ናቸው፡፡ ስለሆነም የፀረ-ቫይረስ ስርዓትዎ በድንገት የማይሠራ ከሆነ የኮምፒውተር ስርዓቱ ትልቅ ችግር ላይ መውደቁን የሚያሳይ በመሆኑ የመፍትሄ እርምጃዎችን መውሰድ የግድ ይላል፡፡

19/06/2022

Ethiopia. No wig. Just natural hair 🌹🌹

Want your establishment to be the top-listed Arts & Entertainment in Addis Ababa?
Click here to claim your Sponsored Listing.

Website

Address


Addis Ababa