M.O.R East Addis Ababa Branch

M.O.R East Addis Ababa Branch

Share

Photos from M.O.R East Addis Ababa Branch's post 18/05/2026

ቅርንጫፍ ጽ/ቤቱ በሚያዚያ ወር 1.44 ቢልዮን ብር ገቢ ሰበሰበ።
…………
ግንቦት 10 /2018 የምስራቅ /አ/አ/አነ/ግ /ከ /ቅ/ጽ/ቤት
ይህ የተገለጸው የሚያዚያ ወር የስራ አፈፃፀም ከቅ/ጽ/ቤቱ ማኔጅመንት ጋር ውይይት ሲደረግ ነው።
የቅርንጫፉ ስራ አስኪያጅ ወ/ሮ ወርቃለም ተሾመ የገቢ እቅዱን 1.44 ቢልዮን በመሰበሰብ 103.05 በመቶ አፈጻጸም ተመዝግቧል ብለዋል ፡፡ ይህ ስኬት በየደረጃው ያሉ ሃለፊዎችና ሰራተኞች እንዲሁም ግብራቸውን በሃላፊነት የከፈሉ ግብር ከፋዮች ውጤት መሆኑን ገልጸው አመሰግነዋል ፡፡በአስር ወራት እየተመዘግበ ያለው አፈጻጸምም የበጀት ዓመቱ ሲጠቃለል የዓመቱ እቅድ እንደሚሳካ የሚያሳይ እንደሆነ ገልጸው ግምገማው በቀጣይ ሊሰሩ በሚችሉ ስራዎች ላይ ትኩረቱን እንደሚያደርግ ተናግረዋል ፡፡
ይህንም ተከትሎ ወሪ/ት ፍሬህይወት ተፈራ የዕቅድና በጀት አፈፃፀም ክትትል ከፍተኛ ባለሙያ የሚያዚያ ወር የስራ አፈፃፀም ሲያቀርቡ ቅ/ጽ/ቤቱ ከቀጥታ ታክሶች፤ ቀጥታ ካልሆኑ ታክሶች እና ታክስ ካልሆኑ ገቢዎች በአጠቃላይ 1.4 ብሊዮን ብር ለመሰብሰብ አቅዶ ብር 1.44 ብሊዮን በመሰብሰብ አፈፃፀሙ 103.05% መሆኑን በሪፖርታቸው አሳይተዋል፡፡
በበጀት ዓመቱ ከተሰበሰበው አጠቃላይ ገቢ ብር 1.44 ብሊዮን መካከል ብር 1.03 ብሊዮን ከቀጥታ ታክሶች፣ብር 404.92 ሚልዮን ቀጥታ ካልሆኑ ታክሶች እንዲሁም ብር 3.08 ሚሊዮን ታክስ ካልሆኑ ገቢዎች የተሰበሰበ መሆኑ ተገልጿል።
ወ/ሮ ወላንሳ ወጋየሁ የሰው ሀይል መረጃና አገልግሎት ቡድን አስተባባሪ በሰራተኛ እርካታ ዙሪያ ዳሰሳዊ ጥናት እና ምክረ ሀሳብ አቅርበዋል ፡፡ የማኔጅመንቱም አባላት በጥናቱ ላይ ውይይት በማካሄድ ይህን መሰል ጥናት መጠናከር እንደሚገባው ጠቁመዋል ፡፡
ቅርንጫፍ ጽ/ቤቱ ከቅርብ ጊዜያት ወዲህ ስራን ከመገምገም ጎን ለጎን የገቢ አሰባሰብ አቅም ላይ ከፍተኛ መሻሻል ሊያመጣ ያስችላል ያላቸውን የስልጠና ርዕሰ ጉዳይ በመምረጥ አመራሮቹ በሥራቸው ውጤታማነት፣ ውሳኔ መስጠት፣ ቡድን መምራት እና የማስፈጸም አቅም ከፍ እንዲልና የእውቀት አድማሳቸውን ለማስፋት የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠናዎችን እየሰጠ ይገኛል ፡፡ በዛሬውም እለት” የስሜት ልህቀት” ”Emotional Intelligence”) በሚል ርዕሰ ጉዳይ ስልጠና በአቶ ሳሙኤል ካሳሁን በዛፋር የንግድ ስራ የሥልጠና እና የኢንቨስትመንት የማማከር አገልግሎት አማካኝነት ተሰጥቷል ፡፡
ወ/ሮ ወርቃለም ስልጠናውን ለሰጡ ለአቶ ሳሙኤል እና ድርጅታቸውን አመስግነው በቀሩት ሁለት ወራት የገቢ አሰባሰብ ሂደት ሁሉም አመራርና ፈጻሚ ሙስናን በመዋጋት፣የአገልግሎት አሰጣጡን በማሻሻልእና ገቢ ሊያስገኙ በሚችሉ ጉዳዮች ላይ ትኩረት ማድረግ እና ሰላማዊ በሆነ የስራ እንቅስቃሴ በቅንጅት መስራት እንደሚገባ አጽንዖት ሰጥተዋል፡፡ የግንቦት ወር የትኩረት አቅጣጫ ያሉትን አመላክተዋል ፡፡ ምክትል ስራ አስኪያጆችም ከተሰጠው አቅጣጫ አንጻር በዘርፍ የተለዩትን ተቀበለው እንደሚያስፈጽሙ ተናግረዋል።
የማኔጅመንት አባላቱም ዕቅዱን ለማሳካት ያላቸውን ቁርጠኝነት በመግለጽ ስልጠናው ለገቢው ስኬት ያለው ጠቀሜታ ከፍተኛ መሆኑንና ለስራቸውም አቅም እንደሚሆናቸው ተናግረዋል ፡፡
………….

Want your organization to be the top-listed Government Service in Addis Ababa?
Click here to claim your Sponsored Listing.

Website

Address


Lem Hotel, Megenagna
Addis Ababa

Opening Hours

Monday 08:00 - 17:00
Tuesday 08:00 - 17:00
Wednesday 08:00 - 17:00
Thursday 08:00 - 17:00
Friday 08:00 - 17:00
Saturday 08:00 - 00:00