Lenat-MOM
23/01/2026
ከማህፀን ውጪ የሚፈጠር እርግዝና የት ሊከሰት ይችላል? በአብዛኛው በማህፀን ቱቦ 'fallopian tube' ውስጥ ሲሆን ካልሆነም በ'ovary' ወስጥ ፣ በሆድ እቃ ውስጥ እንዲሁም በማህፀን በር ላይ ሊከሰት ይችላል። ከማህፀን ውጪ የተፈጠር እርግዝና ምልክቶች ምን ሊሆኑ ይችላሉ? የማህፀን አካባቢ እና የሆድ ህመም እሱም ወደ ትከሻ እና አንገት የሚሄድ ፣ ደም በማህፀን በኩል መውጣት ፣ በድንገት ማዞር እና መውደቅ ሊሆኑ ይችላሉ። ከማህፀን ውጪ የሚፈጠር እርግዝና በቶሎ ህክምና ካላገኘ ወደ አስከፊ አደጋ ሊያጋልጥ ይችላል። የማህፀን ቱቦ 'fallopian tube' መተርተርን ተከትሎ የሚከሰት የውስጥ ደም መፍሰስ እስከሞት የሚዳርግ ሊሆን ይችላል። ከማህፀን ውጪ የሚፈጠር እርግዝናን ለመለየት የማህፀን ምርመራ ፣ አልትራሳውንድ (በማህፀን በኩል የሚገባ) እንዲሁም የእርግዝና መለኪያ ሆርሞን ምርመራዎችን ያካትታል። ከማህፀን ውጪ የሚፈጠር እርግዝና በጊዜ ከተደረሰበት በሀኪም ትዕዛዝ መሰረት በመድሃኒት አልያም ማህፀን ውጪ የተፈጠር እርግዝና ምልክቶች ምን ሊሆኑ ይችላሉ? የማህፀን አካባቢ እና የሆድ ህመም እሱም ወደ ትከሻ እና አንገት የሚሄድ ፣ ደም በማህፀን በኩል መውጣት ፣ በድንገት ማዞር እና መውደቅ ሊሆኑ ይችላሉ። ለማህፀን ውጪ የሚፈጠር እርግዝና ከሚያጋልጡ መንስኤዎች መካከል ከዚህ ቀደም የተፈጠረ የማህፀን ውጪ እርግዝና ፣ የማህፀን አካባቢ ኢንፌክሽን ፣ የስነ - ወሊድ ህክምና እንዲሁም ማጨስ ሊሆኑ ይችላሉ። አንድ ጊዜ የማህፀን ውጪ እርግዝና መከሰት ለወደፊት እርግዝና የሚከለክል አይሆንም። አብዛኞቹ ሴቶች ጤናማ እርግዝና ይኖራቸዋል። ሆኖም በእርግዝና ወቅት በቂ የህክምና ክትትል ማድረግ አስፈላጊ ነዉ። ስለማህፀን ውጪ የሚፈጠር እርግዝና መንሴዎች እና ምልክቶች ከታየ እንዲሁም እርግዝና መፈጠሩ ከተጠረጠረ ቀደም ብሎ ወደ ህክምና ሄዶ የፅንስ ቦታ መታየት ከፍተኛ ለውጥ ይፈጥራል ህይወትንም ከከፋ አደጋ ይከላከላል።ከማህፀን ውጪ የሚፈጠር እርግዝና በአለም አቀፍ ደረጃ የስነ ተዋልዶ ጤና አሳሳቢው ነው። በዓለም አቀፍ ደረጃ ያለው ከማህፀን ውጪ የሚፈጠር እርግዝና ክስተት ከሁሉም እርግዝናዎች ከ1-2 በመቶው እንደሚሆን ይገመታል። ይህ ማለት ለእያንዳንዱ 100 እርግዝና በግምት 1-2 የሚሆኑት ከማህፀን ውጪ ናቸው።ከማህፀን ውጪ የሚፈጠር እርግዝና ክስተቱ እንደ የቦታው ሊለያይ ይችላል፣ እንደ የጤና አጠባበቅ ተደራሽነት፣ በግብረ ሥጋ ግንኙነት የሚተላለፉ ኢንፌክሽኖች (STIs) መስፋፋት እና የተደገፉ የስነ ተዋልዶ ቴክኖሎጂዎች (ART) በመሳሰሉት ተጽእኖዎች ላይ ይወሰናል።
Click here to claim your Sponsored Listing.
Category
Contact the business
Website
Address
Adwa Street
Addis Ababa