Erta'ale Media
06/12/2020
የኦነግ ሸኔ አባላትን ዕድሜ ለማሳጠር የጂ ፒ ኤስ ቴክኖሎጂ ጥቅም ላይ እየዋለ ነው❗️
⚡️በኦሮሚያ በየጊዜው እያጋጠመ ለሚ ገኘው የህይወትና ንብረት ውድመት በህወሓት ጁንታ እና ተላላኪዎቹ የሚፈፀም መሆኑንና ይህንንም ለማስወገድ ብሎም የቡድንን ዕድሜውን ለማሳጠር በ‹ጂ ፒ ኤስ› ቴክኖሎጂ የታገዘ ሥራ እያከናወነ መሆኑን የኦሮሚያ ልዩ ኃይል ፖሊስ ኢንዶክተሬሽን መምሪያ አስታወቀ።
⚡️እነዚህ አካላት ዜጎችን ለምን እንደሚገድሉ እን ደማያውቁ በመጠቆም በህግ ቁጥጥር ሥር ለማዋልም በቴክኖሎጂ የተደገፈ ሥራ መጀመሩን ጠቁመዋል። ቴክኖሎጂው እነዚህ አካላት ያሉበትን ቦታ ለመከታተል የሚያስችል እንደሆነም አመልክተዋል።
⚡️በዚህ ቴክኖሎጂ በመታገዝ የኦነግ ሸኔ አባላት በቁጥጥር ስር እየዋሉ መሆናቸውን የተናገሩት ኃላ ፊው፤ በሠላማዊ መንገድ እጅ ለማይሰጡና የኃይል አማራጭ ለመጠቀም የሚሞክሩት ላይ ደግሞ እርምጃ እየተወሰደባቸው እንደሆነ አስታውቀዋል ።
⚡️እነዚህ ጸረ ሠላም አካላት አባ ቶርቤ በሚል ስያሜ የሚንቀሳቀሱ መሆኑን አመልክተው ፣ ኦሮሚያ ክልልን የግጭትና ጦር አውድማ ለማድረግ ሲንቀሳቀሱ መቆየታቸውን ገልጸዋል። ሠላማዊ ዜጎችን መግደል ሥራቸው አድርገው መቆየታቸውንም አመልክተዋል።
©ኢፕድ
28/11/2020
❗️
የጦር ሀይሎች ጠቅላይ ኢታማዦር ሹም ጀነራል ብርሀኑ ጁላ ጀግናው ሠራዊታችን መቀሌን ሙሉ በሙሉ መቆጣጠሩን አረጋገጡ ❗️
27/11/2020
በማይካድራ ተጨማሪ የጅምላ መቃብሮች ተገኙ፡ አብመድ
በማይካድራ ተጨማሪ ጅምላ መቃብሮች መገኘታቸውን የአማራ ብዙኃን መገናኛ ድርጅት(አብመድ) ዘግቧል፡፡
የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብት ኮሚሽን ከሰሞኑ ባወጣው የመጀመሪያ ደረጃ ሪፖርት ከ600 በላይ ንጹሃን መገደላቸውን ገልጾ ነበረ ቢሆንም አሁን ግን ተጨማሪ የጅምላ መቃብሮች በአካባቢው መገኘታቸው ተዘግቧል፡፡
የጅምላ መቃብሮቹ የተገኙት ከማይካድራ ከተማ ወጣ ባሉ የገጠር አካባቢዎች ሲሆን ግድያውም ዘርን መሠረት ያደረገና በአማራ ተወላጆች ላይ ያነጣጠረ ጅምላ ጭፍጨፋ እንደነበር ኢሰመኮ መገለጹ ይታወሳል፡፡ የሟቾች ቁጥር በትንሹ 600 ነው ተብሎ የተገለጸው በማይካድራ ከተማ በየቤቱ ህይወታቸው አልፎ የተገኙ እና በቤተክርስቲያን ውስጥ የተቀበሩትን ብቻ መሠረት ተደርጎ የተቆጠረ እንደሆነም በዘገባው ተጠቅሷል፡፡
በአንድ ቦታ 18 ሰው በጉድጓድ ውስጥ በጅምላ የተጣሉ መሆኑ የተገለጸ ሲሆን በሌላ የገጠር አካባቢ ደግሞ 57 ሰዎች በጎርፍ ማፋሰሻ ቦይ ውስጥ በጅምላ ተገድለው እና ተጥለው መገኘታቸውን ተረጋግጧል ነው የተባለው፡፡
በዛሬው ዕለትም በማይካድራ ሌላ የገጠር ቀበሌ ውስጥ 17 ሰዎች በጅምላ ተገድለው በጉድጓድ ውስጥ ተጥለው ተገኝተዋል ብሏል አብመድ ፡፡ አሁንም ሴንትራል፣ ደሮ እርባታ፣ በረኸት በሚባሉ አካባቢዎች ላይ አሠሳ እየተደረገ እንደሚገኝ እና ቁጥሩ ሊጨምር እንደሚችል የማይካድራ ነዋሪዎች ገልጸዋል ተብሏል፡፡
27/11/2020
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ከአፍሪካ ህብረት ልዑክ ጋር መወያየታቸውን ጠቅላይ ሚኒስትር ጽህፈት ቤት አስታወቀ፡፡
ጠቅላይ ሚኒስትሩ ልዑኩን በጽህፈት ቤታቸው ነው ተቀብለው ያነጋገሩት፡፡ከልዑካኑ መካከል የቀድሞ የላይቤሪያ ፕሬዚዳን ኤለን ጆንሰን ሰርሊፍ፣ የቀድሞው የሞዛምቢክ ፕሬዚዳንት ጆኣኪም ቺሳኖ፣ የቀድሞው የደቡብ አፍሪካ ፕሬዚዳንት ኪጋሌማ ሞትላንቴ ናቸው፡፡ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይና የአፍሪካ ህብረት ልዑካን በኢትዮጵያ ወቅታዊ ሁኔታ ላይ ተወያይተዋል፡፡
ጠቅላይ ሚኒስትሩ ልዑኩ በአፍሪካዊ ወንድማማች መንፈስ የኢትዮጵያ ሁኔታ አሳስቦት መምጣቱን አድንቀዋል፡፡በውይይቱ ወቅት ጠቅላይ ሚኒስትሩ አሁን በትግራይ ክልል እየተካሄደ ስላለው የህግ ማስከበር ዘመቻ ማብራሪያ ሰጥተዋል፡፡እንዲሁም ለሁለት ዓመታት ያህል ህወሓት ሃገሪቷን ለማተራመስ የሄደበትን ርቀትና መንግስት ያሳየውን ያላሰለሰ ሆደ ሰፊነት ለልዑካኑ አስረድተዋል፡፡
Via PMOEthiopia
27/11/2020
የግብጹ ፕሬዚዳንት ነገ ደቡብ ሱዳን ይገባሉ!
የግብጹ ፕሬዚዳንት አብዱል ፋታህ አልሲሲ ነገ ጁባ እንደሚገቡ የደቡብ ሱዳን ፕሬዚዳንት ጽ/ቤት አስታወቀ፡፡ፕሬዚዳንት ሳል ቫኪር ማያርዲት ነገ በጁባ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ ተገኝተው ለግብጹ አቻቸው አቀባበል እንደሚያደርጉ የገለጸው ጽ/ቤቱ ሕዝቡም በቦታው ተገኝቶ አቀባበል እንዲያደርግ ጥሪ አቅርቧል፡፡ሁለቱ መሪዎች የምሳ ፕሮግራም እንደሚኖራቸው የተገለጸ ሲሆን በጁባና ካይሮ ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነት ላይ እንደሚወያዩ ይጠበቃል፡፡ከዚህ ባለፈም በቀጣው የጸጥታ ጉዳዮች ላይ ውይይት እንደሚደርጉም የፕሬዚዳንቱ ጽ/ቤት ገልጿል፡፡
[Al-ain]
Click here to claim your Sponsored Listing.
Category
Contact the business
Telephone
Website
Address
Addis Ababa