Gpc market

Gpc market

Share

GPC · TikTok 18/06/2023

ባለድጋፍ ተንቀሳቃሽ መፀዳጃ
ለአቅመ ደካሞች እና በራሳቸው አቅም መንቀሳቀስ ለማይችሉ አካል ጉዳተኞች እና ኦፕራሲዮን ላደረጉ ሰዎች የሚሆን አንድ እጁ መአነቃቀል የሚችል ባለድጋፍ ተንቀሳቃሽ መፀዳጃ ከ GPC Engineering (ጌታቸው ፓተንትድ)
አድራሻ:- ፒያሳ ጊዮርጊስ ቤተክርስቲያን ጀርባ ከመንፈሳዊ ኮሌጁ ህንጻ ፊትለፊት
ጆኒ መኪና መሸጫ አጠገብ እና ላፍቶ ኮነሬል ህንፃ አንደኛ ፎቅ ስልክ :- 0912041225 ስልክ :- 0929092922 ስልክ :- 0967404462 ስልክ :- 0924855877ቴሌግራም ቻናል:- https://t.me/GPCengineering

GPC · TikTok Check out GPC's video.

28/07/2022

🧂ጨው ለምን እንከለከላን (ቀንሱ እንባላለን)❓❗🧂

☀️ መግቢያ

✍️ ሶዲየም በተፈጥሮ ብዙ ምግቦች ውስጥ ይገኛል። ሰውነታችን የደም ግፊታችንን እና የደም መጠናችንን ለመቆጣጠር አንሰተኛ መጠን ያለው ሶዲየም ያስፍውልገዋል። ነገር ግን አብዛኛዎቻችን ሰውነታችን ከሚፈልገው መጠን በላይ እንጠቀማለን። ጤናማ የሚባለው የሶዲየም የቀን ፍጆታ ከ2.3 ግራም ወይም አንድ የሻይ ማንኪያ (6 ግራም (2 የሻይ ማንኪያ) የምግብ ጨው) ያልበለጠ ነው። አንዳንድ በሽታዎች (የደም ግፊት፣ የኩላሊት በሽታ፣ የልብ በሽታ ወዘተ) ያሉባቸው ሰዎች አነስተኛ መጠን ያለው ሶዲየም (የምግብ ጨው) ቢጠቀሙ የተለያዩ የጤና ጥቅሞችን ያገኛሉ።

🧂 ጨው መቀነሳችን ለምን ይጠቅመናል❓

🫀 የደም ግፊታችንን ለመቀነስ ይረዳናል

🫁‌ በልብ በኩላሊትና በጉበት በሽታዎች ምክኒያት በሰውነታችን ውስጥ ከመጠን በላይ የሆነ ፈሳሽ እንዳይጠራቀም በማድረግ የሰውነት እብጠትና የደም ግፊት መጨመርን ይከላከላል።

💉 በቀጥታ የደም ግፊትን ከመቀነስ በተጨማሪ የደም ግፊትን ለመቀነስ የሚረዱ ህክምናዎችን (ለምሳሌ፦ የደም ግፊት መድኃኒቶችና ክብደት መቀነስ) ውጤታማ እንዲሆኑ ያግዛል።

‌🧠 በስትሮክ መሞትን፣ የልብ መጠን መጨመርን፣ የኩላሊት ጠጠርን፣ እና የአጥንት መሳሳትን ይቀንሳል።

🔥 ‌አንዳንድ ጥናቶች እንደሚያሳዩት ጨው (ሶዲየም) የጨጓራ ካንሰር ጋር ጠንከር ያለ የምክኒያትና ውጤት ግንኙነትም አለው። ምንም እንኳን አነስተኛ ጨው መመገብ የጨጓራ ካንሰርን እንድሚከላከል የሚያሳዩ ጥናቶች ባይኖሩም።

🧂 ሶዲየም (ጨው) ከምን እናገኛለን❓

✍️ አብዛኛው ከፍተኛ የጨው መጠን ያላቸው ምግቦች የፋብሪካ ውጤት የሆኑ፣ ምግብ ቤቶች ውስጥ የሚዘጋጁ እና በቤት ውስጥ ከቀረቡ በኋላ ጨው የሚጨመርባቸው ምግቦች ናቸው። ሰማኒያ ፐርሰንት የሚሆነው ጨው የፋብሪካ ውጤት ከሆኑ ምግቦች ይገኛል።

🧂 የምንመገበውን ጨው እንዴት መቀነስ እንችላለን❓

✍️ ሲጀመር የምንመገበውን የጨው መጠን መቀነስ ከባድ ቢመስልም በርካቶች አንዴ ከጀመሩት በኋላ የምግቡን ጣዕም በፍጥነት ይላመዱታል። ይህም የሆነው ጨውን የማጣጣም ችሎታ ኖሮን ሳይሆን የምንወለደው ከተወለድን በኋላ የምናዳብረው (Acquired) ስለሆነ ነው። ስለዚህ ከ10 - 14 ቀን ታግሶ አነስተኛ ጨው ያለው ምግብ መመገብ የጀመረ ሰው አዲሱን ጣዕም ለዘለቄታው መልመድ ይችላል።

07/07/2022

☑️ ለሴቶች መካንነት ዋና ዋና መንስኤዎች

1️⃣ እንቁላሎችን ወደ ማህጸን የሚያስተላልፉ ቱቦዎች ወይም ማህጸኑ በጠባሳነት በመጎዳት ምክንያት የቱቦዎች መጎዳት፤ የወንዱ ስፐርም ወደ እንቁላል እንዳይደርስ እክል ይፈጥራል።

ጠባሳዎቹ ምንም አይነት የህመም ምልክት ሳይሰጡ መሃንነትን ሊያስከትሉ ይችላሉ። ጠባሳዎቹ የሚፈጠሩበት ምክንያቶች:-

🔹 በአግባቡ ሕክምና ያልተደረገለት የአባለዘር በሽታ በማህጸን ቱቦዎች ጠባሳን ሲያስከትል ይችላል።
🔹 በውርጃ ወይም በወሊድ ጊዜ የሚከሰቱ የኢንፌክሽን በሽታዎች በማህጸን ወይም በማህጸን ቱቦዎች ላይ ጠባሳ ስያስከትሉ።

2️⃣ እንቁላል የማዘጋጀት ችግር። ለዚህ ምክንያቱ የሚፈለጉት ሆርመኖች በበቂ ሁኔታ ስለማይኖሩ ሊሆን ይችላል። የወር አበባ ከ21 ቀናት ወዲህ ወይም ከ35 ቀናት ወዲያ የሚመጣ ከሆነ ይህ ችግር ሊኖር ይችላል።

አልፎ አልፎም በጣም መወፈር ወይም በአጭር ጊዜ ውስጥ ብዙ ኪሎ መቀነስ የእንቁላል ማዘጋጀት ሊያስተጓጉል ይችላል።

ከዚህ በተጨማሪ እንደ:- የማህጸን እጢ፣ የስኳር በሽታ፣ ሳንባ ነቀርሳ ያሉ በሽታዎችም መካንነት ሊያስከትሉ ይችላሉ።

☑️ ለወንዶች መካንነት መንስኤዎች

💎 ሰውነታቸው የሚያመርተው የዘር ፍሬ ቁጥር በቂ አለመሆን፣ ወይም የተሰሩት የዘር ፍሬ ቀልጣፋነት ማነስ።
💎 በተለያዩ ምክንያቶች (ኢንፈክሽ፣ ጨረር፣ ወዘተ) የዘር ፍሬ የሚያፈልቁ ፍሬዎች ሲጎዱ። በዚህም ምክኒያት ምንም እንኳን በወሲብ ጊዜ ማፍሰስ ቢችሉም የወንድ ፈሳሽ ውስጥ የዘር ፍሬ አይኖርም፤ በመሆኑም ማስረገዝ አይችሉም።
💎 የዘር ፍሬም ከብልታቸው መፍሰስ ሳይችል ሲቀር (የዚህ ምክኒያት በአባላዘር በሽታዎች የፈሳሹን መተላለፊያ ቱቦዎች በመጎዳት ሊሆን ይችላል)።
💎 ቫሪኮሴሌ
💎 ስንፈተ ወሲብ
💎 የተለያዩ የውስጥ ደዌ ህመሞች እና የመሳሰሉት

☑️ ምርመራዎቹ

💥 የሚሰሩት ምርመራዎች ለወንዱና ለሴቷ የተለያየ ቢሆንም፤ ለሴቶች:- የሆርሞን ምርመራ፣ አልትራ ሳውንድ፣ የእንቁላል ምርመራ፣ የማህጸን ኤክስ ሬይ እንዲሁም ጀነቲክ ቴስት ናቸው።
💥 ለወንዶች ደግሞ:- የስፐርም ምርመራ፣ የቴስቴስትሮን ምርመራ (የሆርሞን ምርመራ)፣ የዘር ፍሬ አካባቢ አልትራሳውንድ፣ እና ሌሎች ናቸው።

☑️ ህክምናው

🦋 ኢንፌክሽን ካለ እሱን ማከም
🦋 ከግንኙነት ጋር ያሉ ችግሮችን ማከም
🦋 የሆርሞን ህክምና
🦋 ቀዶ ህክምና
🦋 አጋዥ ቴክኖሎጂ መጠቀም

መልካም ጤንነት!!

ወቅታዊ እና የተሟሉ የጤና መረጃ ለማግኘት፤

Want your business to be the top-listed Beauty Salon in Addis Ababa?
Click here to claim your Sponsored Listing.

Category

Telephone

Website

Address


A. A
Addis Ababa