Dr Temesgen
07/04/2025
አልኮሆል ከመጠን በላይ ለረጅም ጊዚያት መጠጣት የአንጎል መጎዳትና መጠኑ መቀነስ ያስከትላል።
ይህም የማስታወስ አቅም መቀነስ, የፀባይ ለውጥ, የባላንስ አለመጠበቅ እና ተያያዢ ችግሮችን ያስከስታል።
If its needed, please use only standard drink.
Thank you!
14/03/2025
የአንገት ላይ የድስክ መንሸራተት (የሰርቫይካል ስፖንዲሎቲክ ማዮሎፓቲ)
[ ] የአንገት ላይ ድስካ, የአከርካሬ አጥንት, እጢ ወይም በጉዳት ምክንያት ከአንጎል ወደታች የሚወርደው መስመር ላይ በመንሸራተት ጫና ሲያሳድር ይከሰታል።
[ ] እድሚያቸው በገፋ ሰዎች ላይ በብዛት ይስተዋላል።
🇪🇹የምልክቶች ምንድ ናቸው?🇪🇹
[ ] አንገት ላይ ህመም መሰማት ወይም ድርቅ ማለት(አንገትን ለማንቀሳቀስ መቸገር)።
[ ] በእጆችዎ ላይ የመደንዘዝ ወይም የመጠዝጠዝ ስሜት።
[ ] የእጆችዎ እና ክርንዎ ጡንቻ መድክም እና መዛል።
[ ] ሚዛን ማጣት እና የመራመድ ችግር/ደረጃዎችን መውጣት መቸገር/።
[ ] ቀልጣፋነት መቀነስ (እንደ ሸሚዝ መቆለፍ መቸገር፤ ትንንሽ እቃዎችን ከጅ ላይ ማምለጥ)።
[ ] ሽንት የመቆጣጠር ችግር።
🇪🇹ህክምናው 🇪🇹
[ ] ፊዚዎቴራፒ መስራት
[ ] መድሀኒት መውሰድ
[ ] የቀዶ ጥገና ማድረግና ነረቩን የተጫነውን ነገር ማስተካከል
🇪🇹የቀዶ ህክምና አማራጮች 🇪🇹
[ ] 1. የተንሸራተተውን ድስካ በማውጣት የድስክ ቦታ ላይ ከዳሌ አጥንት ትንሽ ወስዶ ማስቀመጥ
[ ] 2.የተንሸራተተውን ድስካ በማውጣት የድስክ ቦታ ላይ ከዳሌ አጥንት ትንሽ ወስዶ ማስቀመጥ ከዛም ከታችና ከላይ ካለው የአከረከሬ አጥንት ጋር በፕሌት ማሰር
[ ] 3.የተንሸራተተውን ድስካ በማውጣት የድስክ ቦታ ላይ ኬጅ(ብረት) ማስገባትና ከከታችና ከላይ ካለው የአከረከሬ አጥንት ጋር በቡለን ማሰር።
[ ] 4.ከኋላ በኩል ያለውን የአከረከሬ አጥንት ክፍል(ላሜላ) ማንሳትና ህብረ ሰረሰር እሚያልፍበት ቦታ ሰፋ እንድል ማድረግ።
🇪🇹በፍፁም ማረግ የለለብዎት ነገር 🇪🇹
[ ] አንገቴን ህመም ተሰማኝ ብለው መታሸት(ያንገት ማሳጅ), በአከረከሬ አጥንት ውስጥ አልፈው ወደ አንጎል የሚሄዱትን የደም ስር በመጎዳት እስከ ሞት አልያም መሉ ሰውነት የመዛል ችግር የማጋለጥ አደጋ አለው።
ምስሎች ለታካሚዎቻችን ከሰራናቸው ቀዶ ህክምናዎች ላይ የተወሰደ
ዶ/ር ተመስገን ሹሜ የአንጎልና ህብረ-ሰረሰር ቀዶ ህክምና ሬዚዴንት, አድስ አበባ ዩኒቨርሲቲ.
መጋቢት 5/2017 ዓ.ም
Click here to claim your Sponsored Listing.
Category
Contact the practice
Telephone
Website
Address
Addis Ababa