Esea Tube
24/11/2025
ግብፅ በአባይ ላይ የምታዣብበው ሳታላይት ኦነግ ሸኔ ከ40 ሰዎች በላይ ገደለ እንኳን በደህና መጣችሁ ወደ ሚዛናችን ሚዲያእዚህ ቻናል ላይ፣ በየጊዜው በሚለዋወጠው ዓለማችን ውስጥ ስላሉት ወቅታዊ ጉዳዮችና አዳዲስ ዜናዎች ጥልቅ ትንተና እና አስተማማኝ መረጃ እና.....
08/11/2025
የምርጫ ቦርድ የጌታቸው ረዳን 'ዴሞክራሲያዊ ስምረት ትግራይ' ፓርቲ የምዝገባ ጥያቄ ለሕዝብ ይፋ አደረገ
የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ በዐዋጅ የተሰጠውን ሥልጣን በመጠቀም፣ በአቶ ጌታቸው ረዳ ካሕሳይ አመራር የቀረበለትን የአዲስ ክልላዊ የፖለቲካ ፓርቲ የምዝገባ ጥያቄ ለሕዝብ ይፋ ማድረጉን አስታውቋል
ቦርዱ ባወጣው ማስታወቂያ መሠረት፣ የምዝገባ ጥያቄው የቀረበለት ፓርቲ "ዴሞክራሲያዊ ስምረት ትግራይ (ስምረት)" በሚል ስያሜ ሲሆን፣ በእንግሊዝኛ ደግሞ "Tigray Democratic Solidarity Party (Solidarity)" በመባል ይታወቃል።
የብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ይህን ያደረገው "በኢትዮጵያ የምርጫ፣ የፖለቲካ ፓርቲዎች ምዝገባ እና የምርጫ ሥነ-ምግባር ዐዋጅ ቁጥር 1162/2011" መሠረት የፖለቲካ ፓርቲዎችን የመመዝገብ ኃላፊነት ስላለው እንደሆነ የገለፀ ሲሆን በዚኹ መሠረት እነአቶ ጌታቸው ረዳ ካሕሳይ “ዴሞክራሲያዊ ስምረት ትግራይ (ስምረት) ወይም Tigray Democratic Solidarity Party (Solidarity)“ በሚል ስያሜ ክልላዊ የፖለቲካ ፓርቲ የምዝገባ ጥያቄ ያቀረቡ በመሆኑ፤ በዐዋጅ ቁጥር 1162/2011 አንቀጽ 68 ንዑስ አንቀጽ 2 እና 3 መሠረት በፓርቲው ስም፣ ዐርማ ወይም ሌሎች ጉዳዮች ተቃውሞ ያለው ሰው፤ ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ከዛሬ ከጥቅምት 29 ቀን 2018 ዓ.ም ጀምሮ በ14 ቀናት ውስጥ ተቃውሞውን ለቦርዱ ጽሕፈት ቤት እንዲያቀርብ ቦርዱ አሳውቋል፡፡
የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ
08/11/2025
📌የዳዊት መለሰ አልበም የሚለቀቅበት ቀን ታወቀ
ድምጻዊ ዳዊት መለሰ የመጨረሻ አልበሙን በ1995 ዓ.ም ለአድማጮች ያቀረበ ሲሆን ለዓመታት ተጨማሪ አልበም ሳይሰራ ቆይቷል።
ከሰሞኑም ድምጻዊ ዳዊት መለሰ አዲስ አልበሙን እንዳጠናቀቀ እንዲሁም የሚለቀቅበት ቀን እንደተቆረጠለትም ኤቨንት አዲስ ሚዲያ ያገኘው መረጃ ያመለክታል።
ይህ ከሁለት አስርት ዓመታት በኃላ ለአድማጮች የሚቀረበው አልበም "ምስጢር" የተሰኘ ርዕስ ተሰጥቷል።
ከቀናትም በፊት ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች በተገኙበት የአልበም ማድመጫ ሥነሥርዓት ተከናውኗል።
ከአልበም ማድመጫ ሥነሥርዓት በኃላም ድምጻዊው በማህበራዊ ትስስርና ገፁ" ሚስጢር የተሰኘውን መጪውን አልበሜን በማካፈል ክብር አግኝቻለሁ።ሚስጢር የዘፈን ስብስብ ብቻ አይደለም። ታሪክ ነው። በመሥራት ላይ 20 ዓመታት ያለፈው። ለሁላችሁም በጣም በቅርቡ እስከ ማካፍላችሁ አጅግ ጓጉቻለሁ" ሲል ጽፏል።
Click here to claim your Sponsored Listing.
Category
Culinary Team
Attire
Telephone
Website
Address
Addis Ababa