Agelgl Media

Agelgl Media

Share

Photos from Agelgl Media's post 24/12/2025

ከህብረተሰቡ ባህል፣ ሞራልና እሴት ተቃራኒ የሆኑ መልዕክቶችን በማህበራዊ ሚዲያ ሲያሰራጭ የነበረን ግለሰብ በቁጥጥር ስር አዋልኩኝ አለ የአዲስ አበባ ፖሊስ፡

የአዲስ አበባ ፖሊስ በመግለጫው ናትናኤል ባደግ ገብሬ የተባለን ተጠርጣሪ በቁጥጥር ስር የዋለው የማህበራዊ ሚዲያን (YouTube እና tiktok platform) ን በመጠቀም በንግግር ልቅ ፆታዊ ግንኙነትን የሚያበረታታና የሚያስፋፋ አፀያፊ መልዕክቶችን ሲያሰራጭ በመቆየቱ ነው ብሏል።

ተጠርጣሪው በተለምዶአዊው ንግግር ሊገለፁ የማይችሉ አስፀያፊ ቃላትን በመጠቀም በትውልዱ ላይ አሉታዊ ተፅዕኖ ሲያሳድር እንደነበር እና መሰል ይዘቶችን በተደጋጋሚ ጊዜ በመስራት በማህበራዊ ሚዲያ (YouTube እና tiktok platform) በመጠቀም ሲያሰራጭ እንደነበር ፖሊስ አብራርቷል፡፡

Agelgl Media

Photos from Agelgl Media's post 24/12/2025

በትግራይ ክልል አሰገደ ወረዳ ሕጻጽ የስደተኞች መጠለያ ላይ የሚደረገው የሰብዓዊ ድጋፍ ዓመቱን በሙሉ ሳይቆራረጥ ተደርጓል አለ የኢትዮጵያ አደጋ ስጋት አመራር ኮሚሽን

ኮሚሽኑ በቅርቡ በማህበራዊ ሚዲያ አማካኝነት እየተሰራጨ ያለው መረጃ ሀሰት ነው ሲል አጣጥሏል።

"በሕጻጽ ጊዜያዊ መጠለያ ጣቢያ የሚገኙ ዜጎቻችን አመቱን ሙሉ ተመሳሳይ ድጋፍ ሲደረግላቸው ነበር" ያለው ኮሚሽኑ ከመስከረም ወር 2018 ዓ.ም ጀምሮ እስከ ታህሳስ ወር 2018 ድረስ የተሟላና ያልተቆራረጠ የምግብ ስብአዊ ድጋፍ እየተደረገላቸው ነው ሲል ዛሬ ረቡዕ ታህሳስ 15 ቀን 2018 ዓ.ም በሰጠው መግለጫ ጠቅሷል።

"ባለፉት አራት ወራት ለ14 ሺህ 413 ዜጎች ድጋፍ ሲደረግ ቆይቷል" ያለው ኮሚሽኑ "በተጨማሪም ከአጎራባች መጠለያ ጣቢያ የሚገኙ ዜጎችን ጨምሮ በመስከረም ወር 16 ሺህ 775 በጥቅምት ወር 18 ሺህ 290 በህዳር ወር 17 ሺህ 813 እንዲሁም በታህሳስ ወር የሚያስፈልገው ለ14 ሺህ 413 ዜጎች የሚያስፈልግ ምግብ ተሰራጭቷል" ብሏል።

"በድምሩ 11 ሺህ 406 ኩንታል ምግብ (ስንዴ፣ ማሽላ፣ ጥራጥሬና የምግብ ዘይት) ባለፉት አራት ወራት እንዲዳርሳቸው ተደርጓል፡፡ ይህ ድጋፍ በገንዘብ ሲተመን ከ257 ሚሊየን ብር በላይ ይሆናል።" ነው ያለው።

በክልሉ ጊዜያዊ አስተዳደር የተለያዩ የሰብአዊ ድጋፍ ችግሮች መኖራቸውንና ተጨማሪ የፌዴራል ድጋፍ እንደሚያስፈልግ አለመጠየቁን የገለፀው ኮሚሽኑ ለተፈናቃይ ማሕበረሰብ የሚላከው ድጋፍ ለታለመለት አላማ ብቻ መዋሉን የማረጋገጥና ክፍተቶች ቢኖሩም እንዲሟላ የማድረግ ሃላፊነት የክልሉና የአካባቢው ጊዜያዊ አስተዳደር ነው ሲልም ዛሬ በሰጠው መግለጫ አሳውቋል።

በክልሉ ደደቢት አቅራቢያ በሚገኘው ሕጻጽ የመጠለያ ጣቢያ 1,700 ሰዎች ለከፋ ረሀብ መጋለጣቸውንና 350 ገደማ ሰዎች በከባድ ረሀብ ምክንያት ህይወታቸው እንዳለፈ መዘገባችን ይታወሳል።

Agelgl Media

Want your business to be the top-listed Media Company in Addis Ababa?
Click here to claim your Sponsored Listing.

Address


Addis Ababa
1000