BBE-News

BBE-News

Share

14/04/2021

በህዋሓት ቡድን ግፊት ወደ በርሃ የወሰዳቸው ወጣቶች ወደ ኑሯቸው እየተመለሱ ነው,።
- መከላከያ ሠራዊት

በህዋሓት ቡድን ግፊት ወደ በርሃ የወሰዳቸው ወጣቶች ወደ ኑሯቸው እየተመለሱ እንደሆነ የደቡብ ዕዝ ዋና አዛዥ ሜጄር ጄኔራል ሰለሞን ኢተፋ ገለጹ፡፡

የደቡብ ዕዝ ከፍተኛ ወታደራዊ አመራሮች ከአዲቀይህና አካባቢው ነዋሪ ጋር ተወያይተዋል።

በውይይቱ ላይ የተገኙት የደቡብ ዕዝ ዋና አዛዥ ሜጄር ጄኔራል ሰለሞን ኢተፋ ፣ ጁንታው በሀሰት ፕሮፓጋንዳ እያታለላቸው ወደ በረሃ የወሰዳቸው ወጣቶች የራሳችንን ኑሮ መኖር ይሻለናል በማለት ወደ ቀያቸው እየተመለሱ ነው ብለዋል።

በማወቅም ይሁን ባለማወቅ ወደ በረሃ የገቡ ቀሪ ልጆቹን የአዲቀይህ ህዝብ ወደየቤታቸው እንዲመለሱ ማድረግ አለበት ሲሉም በአፅንኦት ተናግረዋል።

"ከየትኛውም ወገን ይሁን ሰው መሞት የለበትም" ያሉት ጄኔራል መኮንኑ ጁንታው እያታለለም ሆነ እያስገደደ የወሰዳቸው የታጠቀም ይሁን ያልታጠቀ ሃይል በሰላም ትጥቁን እንዲያስረክብና ኑሮውን እንዲቀጥል አሳስበዋል።

ብ/ጄ ናስር አባዲጋ በበኩላቸው ፣ ጁንታው የሰሜን ዕዝ ላይ ጥቃት ሲፈፅም ለትግራይ ህዝብ የነገረው መረጃ ሁሉ ውሸትና ጦርነቱንም እራሱ ሠራዊቱ ላይ ከህደት በመፈፀም የጀመረው መሆኑን ለተሰብሳቢው አስረድተዋል።

በውይይቱ ላይ የተገኙት የአዲቀይህ የተለያዩ የማህበረሰብ ክፍሎችም "መከላከያ የየትኛውም ድርጅትና ክልል አለመሆኑን ፣ ለመላው ኢትዮጵያ የቆመ ሰራዊት መሆኑን ጥርጥር የለንም" በማለት ገልፀዋል።

"እኛ ከመከላከያ ጎን በሆናችን በጁንታው የብልፅግና ደጋፊ እየተባልን ነው" ያሉት ተሳታፊዎች "መከላከያ ከእኛ ጋር አብሮ ከሰራ አካባቢያችንን መጠበቅ የታጠቀውን ሃይልም መያዝ አያቅተንም" ሲሉ ተናግረዋል።
ምንጭ፡ የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት @ ደሬቴድ

👇


👉 https://t.me/bbe_newss አግኙን

👇
👉 https://www.facebook.com/107793534680780 ተከታተሉን።

👉

14/04/2021

"... ከእነሱ ጋር ጦርነት አንፈልግም ፤ ነገር ግን ዝግጁ አይደለንም ማለት አይደለም"
- ሌ/ጄነራል ባጫ ደበሌ

ሌ/ጄነራል ባጫ ደበሌ ትለንት በሰጡት መግለጫ ፥ ኢትዮጵያ ከሱዳን ጋር ጦርነት እንደማታደርግ ፥ ጦርነት ማድረጉ ምንም እነደማያደርግ ተናግረዋል።

ሌ/ጄነራሉ አሁን ሱዳኖች ያያዙትን መሬት በንግግር መጨረስ ይቻላል ፥ እምነታችንም እሱ ነው ብለዋል።

ስንት ጊዜ ነው በመሬት ችግር ዘራፍ ብለን ተዋግተን ወጣቶችን የምናስጨርሰው ? ብለው የጠየቁት ሌ/ጄነራሉ ፥ የመሬቱን ጉዳይ በቀላሉ ወደ ፍርድ ቤት ሄዶ መፍታት ይቻላል ፤ ግፋ ቢል በዓለም አቀፍ ፍርድ ቤት መፍታት ይቻላል ሲሉ ተደምጠዋል።

በሱዳን እና በኢትዮጵያ ወንድማማቾች መካከል የገባ ሶስተኛ ወገን አለ ፤ ከሱዳን ወንድሞቻችን ጋር በጋራ ሆነን ይሄን ሶስተኛ ወገን ለማውጣት ጥረት ይደረጋል ሲሉ ተናግረዋል።

ሌ/ጄነራል ባጫ ፥ "ከእነሱ ጋር ጦርነት አንፈልግም ነገር ግን ዝግጅ አይደለንም ማለት አይደለም፤ ኢትዮጵያን ለመከላከል እኛ የኢትዮጵያ መከላከያ ሰራዊት ምን ጊዜም ዝግጁ ነን" ሲሉ ገልፀዋል

👇


👉 https://t.me/bbe_newss አግኙን

👇
👉 https://www.facebook.com/107793534680780 ተከታተሉን።

👉

Want your business to be the top-listed Shop in Addis Ababa?
Click here to claim your Sponsored Listing.

Website

Address


Addis Ababa