ZOBEL TIMES

ZOBEL TIMES

Share

05/08/2023

ከኮለኔል ፈንታው ሙሃቤና ከኮለኔል ሞገስ ዘገየ በወቅታዊ ጉዳዮች ላይ የተሰጠ አስቸኳይ መግለጫ‼

እንደሚታወቀው ትዕግስታችን ሆደ ሰፊነታችንና ሃገር ወዳድነታችን እንደ ፍርሃት ተቆጥሮ እኛን መጨፍጨፉና ማፈናቀሉ የዕለት ተዕለት ቀላሉ የአበል ስራቸው መሆኑ አልበቃ ብሏቸው በተደጋጋሚ ክልላችንን ሆን ብለው የጦርነት ቀጠና በማድረግ አራሹና መጋቢውን ህዝባችን የሩዝና የዱቄት ተመፅዋችና የሰው እጅ ጠባቂ እንዲሆን ማድረጋቸው አንሷቸው ዛሬም አዲስ ስልት በመንደፍ ህዝባችንን የከፋና ህጋዊ ደሃ ለማድረግ የፌዴራል መንግስቱና የክልሉ መንግስት ተጣምረው በጋራ እየተናበቡ በመስራት ላይ ይገኛሉ።

አሁን ባለው ወቅታዊ ሁኔታና የትግል ምዕራፍ በአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ድንጋጌ የሚመጣ አንዳችም ሰላም የለም። ምናልባት የከፋ ደህንነትና ስራ አጥነት እንጂ። እንደሚታወቀው አስቸኳይ ጊዜ አዋጅ በሚጣልባቸው ስፍራዎች ላይ ቱሪስትም ሆነ ባለሃብቶች ወደዚያ ስፍራ አቅንተው ጉብኝትም ሆነ አዳዲስ ኢንቨስትመንቶችን እንዳያደርጉ ይገደዳሉ። ይህ ሆነ ማለት በኦሮሚያ ክልል ሰፍኖ በነበረ የጸጥታ ስጋት ቆሞ የነበረውን የቱሪስትና የኢንቨስትመንት ፍሰት ዳግም እንዲያብብና የእኛ እንዲቀጭጭ በር ከፋች የሆነ ሆን ተብሎ ታስቦበት በስሌት የተሰራ የከፋ ውሳኔ ነው። ስለሆነም አጥብቀን እንታገላለን እንጂ በመግልጫ የሚቆም ተራ ትግል አልጀመርንም።

ለመከላከያ ሰራዊታችን ደጀን ለሃገር ካስማ የሆነው ህዝባችን ሳያሳዝናቸው አዝመራውን መዝራት ባለበት ወቅት እንዳይዘረና ነገ በረሃብ እንዲያለቅ ሆን ብለው በማሰብ ማዳበሪያ ጭምር ሲከለክሉት የከረሙትን አርሶ አደሩ ህዝባችንን ዛሬ ጥያቄያችን ይሰማ ባለና የህልውና አደጋችንን መንግስት እስኪያረጋግጥለንና እንዲሁም ገዳዮቻችን እሰኪሰንፉና አቅማቸው ተሟጦ ሳይዳከም ትጥቅ አንፈታም በማለታችን ብቻ ተጨማሪ ምክንያት በመፈለግ ዳግም ክልላችንን ከኢኮኖሚ ተጠቃሚነቱና ከሰላሙ ሊያርቀው የሚችል አዋጅ በማወጅ ኢ-ዴሞክራሲ የሆነ ውሳኔ መወሰንና በመግለጫ ማውጣታቸው ይታወቃል።

ስለሆነም ህዝባችን የታቀደለትን በሲስተም አደህይቶ የማስገበር ሴራ ቀድሞ በማውቅ የጀመረውን ሁሉን አቀፍ ህዝባዊ ትግል አጠንክሮ በመቀጠል የታቀደለትን ሴራ በጣጥሶ እንደሚወጣና ዳግም ሰላሙን በአጭር ጊዜ በክንዱ አረጋግጦ ወደ ነበረበት ሰላም እንደሚመለስ በፅኑ እናምናለን።

ማሳሰቢያ:-
▪1ኛ...በተቆጣጠርናቸውና ወደፊትም በምንቆጣጠራቸው ከተሞች ላይ ተሸናፊውና ተስፋ የቆረጠው የቀድሞው ስርዓት ጣር ላይ ስለሚገኝ በመንፈራገጥ ብዙ ውድመቶች ሊያስከትል ስለሚችሉ የጣሩንም የግነዛውንም የቀብሩንም ሂደት በጥንቃቄ ማድረግ ይጠበቅብናል።

▪2ኛ...ከተሞችን በመቆጣጠር ሂደት ውስጥ ተመሳስሎ መዝረፍም ሆነ ከማህበረሰቡ ሊለየን የሚችልን ማንኛውንም ጥፋት መፈፀም እስከ ወዲያኛው የሚያሸኝ አጸያፊ ተግባር መሆኑ እንዲታወቅ ማሳወቅ እንፈልጋለን።

▪3ኛ...በመንግሥት የጸጥታ ተቋም ውስጥ ማለትም በፖሊስ በሚሊሻና በመከላከያ ተቋም ውስጥ የምታገለገሉ አባሎችን ይፋዊ የትግል ጥሪያችንን ተቀብላችሁ እንድትቀላቀሉን ዛሬም ጥሪያችንን እናቀርባለን።

▪4ኛ...ህዝባችን በጀመረው መራር የህልውና ትግል ምክኒያት ለዚህ እንደተዳረገ ለማስመሰል የሚደረግን ለካድሬ ሸፍጥ ጆሮ ባለመስጠት ወደ ፊት ፀንቶ በመታገል ራሱንና ህዝቡን ነፃ እንዲያወጣና እስካሁን ከሆነው በላይ የሚሆነውም የሚደርስበትም አንዳች መከራ የለምና በተራ መግለጫ እንዳይደናገጥና የጀመረውን ትግል አጠናክሮ እንዲቀጥል አበክረን እናሳስባለን።

▪5ኛ...በሁሉም አቅጣጫ ያለ ፋኖ ከእንግዲህ ለሚኖረን መራር የህልውና ትግል ለዘመቻው ስያሜ እየሰጠን የራሳችንን ታሪክ በደማችን እየጻፍን የምንሄድበት ቁመና ላይ መድረሳችንን እናበስራለን።

▪6ኛ...ከመቼውም ጊዜ በላይ እያሳየን ያለነውን የመነጋገር የመደማመጥና የመከባበር ፍቃደኝነታችንን ከዚህ በላይ አጠናክረን እንድንቀጥል በታላቁ ህዘባችን ስም እንለምናለን አደራም ማለት እንወዳለን።

በመጨረሻም ላንጨርስ የጀመርነው ትግል የለምና እንኳን በእናንተ ተራ መግለጫ በያዛችሁት ግዙፍ ሰራዊት የሚበረግግ ትንሽ ልብ የለንምና ህዝብን ከማሸበር ስራ ብትወጡ ለማለት እንወዳለን::

ቅዳሜ 29/12/2015 ዓም
ጋሸና ሰሜን ወሎ ዞን

30/07/2023

የችሎት ጥቆማ!

የታሪክ ምሁሩ ጋሽ ታዲዮስ ታንቱ በነገው ዕለት ሀምሌ 24 ቀን 2015 ዓ/ም ከቀኑ 8:00 ሰዓት ላይ ልደታ ከፍተኛ ፍርድ ቤት ይቀርባሉ።

የምትችሉ ሁሉ ነገ ልደታ ምድብ ችሎት ከፍተኛ ፍርድ ቤት በመገኘት አጋርነታችሁን እንድታሳዩ!

ፍትህ ለታሪክ ምሁሩ ጋሽ ታዲዮስ ታንቱ!

ZOBEL TIMES

Want your business to be the top-listed Media Company in Addis Ababa?
Click here to claim your Sponsored Listing.

Website

Address


Addis Ababa