Guna Media Service

Guna Media Service

Share

10/01/2022

ሰበር ዜና - አስቸኳይ የቅዱስ ሲኖዶስ ምልዓተ ጉባኤ ተጠራ !!!

***

የቅዱስ ሲኖዶስ ጽ/ቤት በመስቀል አደባባይ ጉዳይ ለመነጋገር አስቸኳይ የቅዱስ ሲኖዶስ ምልዓተ ጉባኤ ጠርቷል።

በሀገር ውስጥ የሚገኙ ብፁዓን አባቶች በምልዓተ ጉባኤው እንዲገኙ የቅዱስ ሲኖዶስ ጽ/ቤት ለብፁዓን አባቶች የስልክ ጥሪ እያደረገ እንደሚገኝ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል።

የቅዱስ ሲኖዶሱ ምልዓተ ጉባኤ ነገ ከቀትር በኋላከ 9:00 ሰዓት ጀምሮ እንደሚከናወን ይጠበቃል

ምንጭ
ተዋሕዶ ሚዲያ ማዕከል

16/12/2021

የደቡብ ሱዳን ፕሬዝዳንት ሳልቫኪር ማያርዲት መንግሥትና ሕዝባቸው ከኢትዮጵያ ጎን እንደሚቆሙ አረጋገጡ‼️

ፕሬዝዳንቱ ይህን ያሉት ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትርና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ደመቀ መኮንን ለአንድ ቀን የሥራ ጉብኝት ደቡብ ሱዳን ጁባ ተገኝተው ሲመክሩ ነው፡፡

ፕሬዝዳንት ሳልቫኪር ደቡብ ሱዳን ሁሌም ከኢትዮጵያ ሰላም፣ መረጋጋት፣ ፀጥታና የግዛት አንድነት መጠበቅ ጎን እንደምትቆም ለምክትል ጠቅላይ ሚኒስትርና ውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ ማረጋገጣቸውን ነው የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር መረጃ የሚጠቁመው፡፡

ኢትዮጵያ የራሷን ችግር በራሷ አቅም የመፍታት ሙሉ አቅም እንዳላት አገራቸው የማይወላውል እምነት እንዳላት ጠቁመውም በኢትዮጵያ የውስጥ ጉዳይ ጣልቃ ለመግባት መሞከርን በፍፁም እንደማትቀበልም አፅንኦት ሰጥተዋል።ሁለቱ መሪዎች በሁለቱ አገራት የጋራ ጉዳዮች ላይ መክረዋል፡፡

Want your business to be the top-listed Media Company in Addis Ababa?
Click here to claim your Sponsored Listing.

Culinary Team

Attire

Website

Address


Addis Ababa