TIKVAH-ETH
18/06/2026
ዓለም አቀፍ የነዳጅ ዋጋ አሽቆለቆለ።
በአሜሪካና ኢራን መካከል ለወራት የዘለቀውን ጦርነት ለማስቆምና የሆርሙዝ ሰርጥን ለመክፈት ያለመ ጊዜያዊ ስምምነት መፈረሙን ተከትሎ የዓለም የነዳጅ ዋጋ ቀንሷል።
እንደ ሮይተርስ ዘገባ የተፈረመው ስምምነት በአቅርቦት ላይ የነበረውን ስጋት በማቃለሉ የብሬንት ድፍድፍ ነዳጅ ዋጋ በበርሜል 78.66 ዶላር ሆኗል።
በተመሳሳይ ፣ የዌስት ቴክሳስ ኢንተርሚዲየት (WTI) ዋጋም ወርዶ በበርሜል $75.81 ሆኖ ተመዝግቧል።
ሰኔ 10 ቀን 2018 ዓ/ም
TIKVAH-ETH
18/06/2026
" የመጨረሻው ስምምነት ላይ መድረስ ካልተቻለ በቦምብ እንደበድባቸዋለን " - ትራምፕ
የአሜሪካ እና ኢራን ፕሬዚዳንቶች ጦርነቱን ከአሁን ጀምሮ የሚያስቆመውን የመጀመርያ ስምምነት ፈረሙ።
ስምምነቱ የሆርሙዝ ሰርጥ እንደገና መክፈት፣ የ300 ቢሊዮን ዶላር ኢራን " መልሶ የመገንባት " ዕቅድ፣ አሜሪካ ኢራን ላይ የጣለችውን " ሁሉንም ዓይነት ማዕቀቦች " የሚያስቆም ነው።
ነገር ግን የኢራን ጦርነት እንዲቀሰቀስ ዋነኛ ምክንያት የሆነው የኒውክሌር ፕርግራም ሊራዘም በሚችል 60 ቀናት ውስጥ ድርድር የሚካሄድበት ጉዳይ ሆኗል።
የአሜሪካውን ፕሬዚዳንት ፈረንሳይ በተካሄደው የቡድን ሰባት ጉባዔ ላይ በተሳተፉበት ወቅት ፊርማቸውን ሲያኖሩ " ምጣኔ ሃብታዊ ቀውስን " የሚያስቀር ዕቅድ ነው ሲሉ ተናግረዋል።
ነገር ግን ከኢራን ጋር የመጨረሻው ስምምነት ላይ መድረስ ካልተቻለ " በቦምብ እንደበድባቸዋለን " ሲሉ ዝተዋል።
የኢራኑ ፕሬዚዳንት ማሱድ ፔዜሽኪያን ረቡዕ ዕለት ስምምነቱ ላይ ፊርማቸውን ማኖራቸውን ቴህራን አረጋግጣለች።
የኢራን ቁልፍ ተደራዳሪ የሆኑት የምክር ቤቱ አፈ ጉባዔ ሞሃመድ ባግሃር ጋሊባፍ ለአገር ውስጥ መገናኛ ብዙኃን አሜሪካ ላይ ያላቸው ጥርጣሬ እንዳለ መሆኑን አስታውቀው " ጣቶቻችን አሁንም ቃታ ለመሳብ ዝግጁ ናቸው " ብለዋል።
" ጠላት የተጠየቅነውን ቋንቋ ካልተረዳ ወደ ኃይል ቋንቋ ተመልሰን እንገባለን " ሲሉ ለፋርስ ኒውስ ተናግረዋል።
መረጃው የቢቢሲ ነው።
ቲክቫህ ኢትዮጵያ
ሰኔ 11 ቀን 2018 ዓ/ም
TIKVAH-ETH
ኖርዌይ ከ ኢራቅ
15/06/2026
የአሜሪካ እና ኢራን ስምምነት የነዳጅ ዋጋን ቀነሰ
አሜሪካ እና ኢራን የሆርሙዝ የባህር መስመርን ለመክፈትና ጦርነቱን ለማቆም የስምምነት ማዕቀፍ ላይ መድረሳቸውን ተከትሎ በዓለም አቀፍ ገበያ ላይ ከፍተኛ ለውጥ ታይቷል።
ስምምነቱን ተከትሎ የጃፓንና የደቡብ ኮሪያ አክሲዮን ገበያዎች እስከ 5.7 በመቶ የደረሰ ታሪካዊ ጭማሪ አሳይተዋል።
በአንጻሩ የብሬንት ድፍድፍ ነዳጅ ዋጋ በ4.5 በመቶ በመቀነስ በአንድ በርሜል ከ83.40 ዶላር በታች ወርዷል።
የአሜሪካው ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ በኢራን ላይ የተጣለው የባህር ኃይል እገዳ እንዲነሳ ማዘዛቸውን ያስታወቁ ሲሆን፤ ይፋዊው የፊርማ ሥነ-ሥርዓት አርብ ዕለት በስዊዘርላንድ እንደሚካሄድ ተገልጿል።
ስምምነቱ ሊባኖስን ጨምሮ የተኩስ አቁም ማድረግን፣ የማዕቀብ መነሳትን እና የ24 ቢሊየን ዶላር የኢራን ሀብት መልቀቅን ያጠቃልላል ተብሏል።
የባህር መስመሩ መከፈቱ የዓለምን የነዳጅ እጥረት የሚያቃልል ቢሆንም፤ የተከማቹ መርከቦችን ለማፅዳትና የባህር ውስጥ ፈንጂዎችን ስጋት ለመቅረፍ ግን ወራትን ሊወስድ እንደሚችል ባለሙያዎች አስታውቀዋል።
ሳራ ዮሐንስ
TIKVAH-ETH
Click here to claim your Sponsored Listing.
Category
Contact the public figure
Telephone
Website
Address
Niger Street
Addis Ababa
1000