At Auto Import
17/11/2025
የሀገራችንን ነባራዊ ሁኔታ በጥልቀት የተረዳ ፣ መፃኢ ተስፋዋን አርቆ የተመለከተ ትርክት፡- ብሔራዊነት!
ኢትዮጵያውያን በአብሮነት የተጋመድን፣ በህብረ ብሄራዊነት የተሳሰርን፣ ሳይደፈር ለዘለቀው የሀገራችን ሉዓላዊነት እኩል ዋጋ የከፈልን፣ መልካም እድሎችንና መከራዎችን እኩል የተጋራን መሆናችን ዓለም የሚያውቀው ሀቅ ነው።
ተደምረን በሰራናቸው አኩሪ ተግባራት ትናንት በአባቶቻችን በአድዋ ድል ዛሬ ደግሞ በእኛ ትውልድ ዳግማዊ አድዋ በሆነው ታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ እና በሌሎችም አንፀባራቂ ድሎች በአብሮነት ደምቀን ከፍ ብለን መታየት ችለናል፡፡
የጥንካሬዎቻችን ምንጭ የሆነውን ብዝሀ ማንነትን በአግባበቡ ማስተናገድ ባለመቻሏ ኢትዮጵያ ቁልቁል ስትጓዝ ስለቆየች ፤ የለውጡ መንግስት የኢትዮጵያ ብልፅግና የሚረጋገጠው ሁሉንም አቅሞች በማስተባበር ፀጋዎቿን አልምቶ መጠቀም ሲቻል መሆኑን አስምሮበታል፡፡
አሰባሳቢውን የብሔራዊነት ገዢ ትርክት በመገንባት፣ ህብረ ብሔራዊ አብሮነትን በማጠናከር የሀገራችንን ማንሰራራት ጉዞ እውን ለማድረግ የተጀመረው ሁሉን አቀፍ ርብርብም የሀገራችንን ነባራዊ ሁኔታ በጥልቀት የተረዳ እና መፃኢ ተስፋዋን አርቆ መመልከት የቻለ አዲስ እይታ ነው፡፡
ብሔራዊነት በዜጎች መካከል እውነተኛ ወንድማማችነትን የሚያጎለብት እና ብሔራዊ መግባባትን የሚያረጋግጥ ዘመኑን የዋጀ ተራማጅ ገዢ ትርክታችን ነው።
ታላቁ ገዥ ትርክት የልዩነት መነሻ የሆኑትን ችግሮች በውይይት በመፍታት፣ በልዩነቶች ውስጥም የመግባባት፣ የመከባበር እና የመተባበር ባህል መገንባትን ዓላማው አድርጓል፡፡
ያለፈውን ስህተት ማረም፣ አለመግባባቶችን እና ግጭቶችን በይቅርታና በዕርቅ መፍታት በዜጎች መካከል እውነተኛ ፍቅርን ያጠናክራል።
የህዝባችንን የጋራ ጉዳይ የሚያጎላው የብሄራዊነት ትርክት አንድነታችን ለማጥበቅ፣ ህብር ማንነታችን ለማስጠበቅ ፣ ዛሬን ተግተን ለመስራት፣ የነገን ተስፋችንን በማለምለም ለቀጣዩ ትውልድ የበለፀገች ሀገር ለማሻገር ወሳኝ ቁልፍ ነው።
ለሀገር ግንባታ ጉዞአችን የድርሻችንን ታሪካዊ አሻራ በማሳረፍ፣ የሀገራችንን ሰላም፣ አንድነትና ሁለንተናዊ ብልፅግናን እውን ማድረግ እንዲሁም አሰባሳቢውን የብሄራዊነት ገዢ ትርክት መገንባት ከሁላችንም ይጠበቃል፡፡
በብልፅግና ፓርቲ የአዲስ አበባ ቅ/ፅ/ቤት
Click here to claim your Sponsored Listing.
Contact the business
Telephone
Website
Address
Balderas
Addis Ababa