Alex Dish Work
የ ቅዳሜ ትኩስ ትኩስ ስፖርታዊ ዜናዎች ባማረ አቀራረብ ይዘን መጥተናል።
…
ሁሌም ፖስቶቹን ላይክ ሳያደርጉ አይለፉ።
ላይክ ማድረጋችሁ ለኛ ብቻ ሳይሆን ለናንተም እንዲደርሳችሁ ነው።
አሌክስ ዲሽ ለተለያዩ የዲሽ እና sport መረጃዎች መከለል
ዲሾን መሰረት ከፈለጉ ይደውሉ
0925417740
0925417740
¤የ አልማዝ አያና ቃለ ምልልስ
ጋዜጠኛ:አበረታች መዳኒት ወስደሻል የሚል ጥርጣሬ አለ ስለዚህ ምን ትያለሽ?
አልማዝ: አዎ አበረታች መዳኒት ወስጃለዉ ግን እኔ ኪኒን ሳይሆን የወሠድኩት አበረታች መዳኒት ኢየሱስ ክርስቶስ ነዉ!!!!!!!
:
¤አሰልጣኛ ፔፔ ጋርዲዮላ ለዛሬው የፕርሜር ሊግ መክፈቻ ጫወታ የ 34 አመቱን ዊሊ ካባያሮን ተማራጫቸው አድርገውታል በጆኸርት ላይ እምነት የላቸውም የባርሴሎናውን ጀርመናዊ በረኛ ማርክ አንድሬስ ትሬስቴገንንም ማምጣት ይፈልጋሉ:: (daily express)
:
¤ቼልሲ የ 29 አመቱን ስፔናዊ ሴስክ ፍብሪጋስን ለጣልያኑ ሻምፕዮን ለጁቬንቱስ አቅርበውታል ጁቬም ለተጫዋቹ €45 million ገደማ ያወጣል ተብሎ ይጠበቃል:: (tutto sport)
:
¤ቶተንሀም ዴንማርካዊውን ኢንተርናሽናል ክርስቲያን ኤሪክሰንን አዲስ ኮንትራት ለማስፈረም ሳምንታዊ ደሞዙን ወደ £150000 አድርገው በዋይት ሀርትሌን ማቆየት ይፈልጋሉ:: (mirror)
:
¤ጁቬንቱስ እና ኢንተርሚላን ሁለቱም ክለቦች የ 24 አመቱን የመስመር ተጫዋች ክሪስትያን ኤሪክሰንን ይፈልጉታል:: (daily telegraph)
:
¤የክሪስታል ፓላሱ ኮንጉዋዊ የመስመር ተጫዋች ያኒክ ቦላሲ በሚቀጥለው ሳምንት ለኤቨርተን ይፈርማል:: (express)
:
¤ቶተንሀም ለእስፖርቲንግ ሊዝበኑ የ 27 አመት አማካይ ለአድሬን ሲልቫ £13 million አዘጋጅተዋል ኤቨርተንም የተጫዋቹ ፈላጊ ናቸው:: (l'equipea)
:
¤ጆሴ ሞሪኒዮ የማንችስተርን አሰልጣኛነት መንበር ከያዙ በኃላ ሶስት ወጣት እንግሊዛዊያይን ከኦልትራፎርድ አሰናብተዋል ተከላካዩን ታይለር ብላንኬትን አጥቂዎቹን ጀምስ ዊልሰንን እና ዊልኪንን:: (daily mail)
:
¤ሚድልስ ብራ የማንችስተሩን የ 20 አመት አማካይ አንድሬስ ፔሬራን ማስፈረም ይፈልጋሉ:: (mail)
:
¤የመድፈኞቹ አለቃ አርሰን ዌንገር ዛሬ በነበራቸዉ ጋዜጣዊ መግለጫ ላይ ስለ ኦዚል እና ሳንቼዝ ኮንትራት ዙርያ ጥያቄ ቀርቦላቸዉ፣ደጋፊዎች ምንም ሊያሳስባቸዉ እንደማይገባ ተናገሩ "በእርግጥ ረጅም
ፕሮሰስ አለዉ ቢሆንም መርሳት የሌለብን ከኛ ጋር የሚያቆያቸዉ ቀሪ የሁለት አመት ኮንትራት አለ፣ደጋፊዎችም ቢሆኑ ሊያሳስባቸዉ አይገባም አዲስ ኮንትራት እንደሚፈርሙ አምናለዉ"በማለት ተናግረዋል።
:
¤ኤቨርተን የቫሌንሺያውን ቱኒዝያዊ ተከላካይ አይመን አብዱልኑርን ለማስፈረም ተቃርበዋል:: (deportvio valencia)
:
¤አስቶንቪላ የቼልሲውን እንግሊዛዊ አጥቂ ፓትሪክ ባምፎርድን ማስፈረም ይፈልጋሉ ካርዲፍ ሲቲ ደግሞ አየስላንዳዊውን አማካይ አሮን ጉኔርሰንን ማስፈረም ይፈልጋሉ:: (sun)
:
¤የሊቨርፑሉ አጥቂ ማርዮ ባሊቶሊ በዚህ አመት ወደ ሴሪያው አይመለስም ሲል የፒሲካራውን ፕሬዝዳንት ዳንኤል ሴባስትያን በመጥቀስ gazzetta worls አስነብቡዋል::
:
¤የሳውዝሀምፕተኑ ተከላካይ ጆሴ ፎንቴ ማንችስተርዩናይትድ "አንዱ የአለማችን ታላቁ ክለብ ነው" ብሉዋል ተጫዋቹም ስሙ ከዩናይትድ ጋር ተያይዞ ተነስቱዋል:: (mail futebol)
:
¤የእስቶኩ አሰልጣኛ ማርክዩዝ አየርላንዳዊውን ተከላካይ ማርክ ዊልሰንን ለመሸጥ ተዘጋጅተዋል:: (stoke sentinel)
:
¤ዋትፎርድ የቼልሲውን ብራዚላዊ አማካይ ኬኔዲን ማስፈረም ይፈልጋሉ:: ሰማያዊዎቹ አሜሪካናዊውን ተከላካይ ማቲ ሚዛግን በውሰት ወደ ኢንትራንክ ፍራንክፈርት ሊልኩት ነው:: (goal)
:
¤ሲውዲናዊው የዩናይትድ አጥቂ ዛላታን ኢብራሂምኦቪች እንደተናገረው "በማንችስተር ዩናይትድ ቆይቼ ለ ቀጣዮቹ 3 አመታት መጫወት ፈልጋለው" ብሉዋል:: (sky sport)
:
¤የቶተንሀሙ አማካይ ዴል አሊ የማለያ ስሙን 'DELE በማለት በዚህ SESONE ይቀይረዋል የቀየረበትን ምክንያት ግን አልተናገረም:: (tottenham website)
:
¤የቀድሞ የዩናይትድ አማካይ የ 41 አመቱ ሴባስቲያን ቬሮን ጫማውን ከሰቀለበት በማወረድ ለአርጀንቲው estrella de berisson ሊጫወት ነው:: (sun)
:
¤የሳንቶሱ ፕሬዝዳንት እንደተናገረው ማንችስተር ዩናይትድ እና ቼልሲ ስለ ክለባቸው ኮከብ ጋብርኤል ባርቦሳ እንደጠየቁዋቸው አረጋግጠዋል:: (mirror)
:
¤ ጀርመናዊዉ የቫለንሺያ ተከላካይ ሽኮድራን ሙስጣፊ ለህክምና ምርመራ ለንደን መግባቱን Goal.comአስነበበ፣አክሎም ተጫዋቹ በሚቀጥሉት 72 ሰአታት ዉስጥ በ £25ሚ የመድፈኞቹ ንብረት እንደሚሆን ገልፁዋል::
:
¤paper talk¤
:
¤ኤስሚላን እና ቫሌንሺያ የሲቲውን ተከላካይ ኤሊኩም ማንጋላን ማስፈረም ይፈልጋሉ:: (daily star)
:
¤ጆሴ ሞሪኒዮ የአንደርሌክቱን አማካይ youri tieleman ዩናይትድን እንዲቀላቀል ጠይቀዋል:: (telegraph)
:
¤አርሰን ቬንገር ፊታቸውን ወደ ሳንቲ ካዞሮላ አዙረዋል ለአርሰናል የቡድን አንበልነት::
:
¤ጁቬንቱስ የዩናይትዱን አማካይ አንድሬ ሄሬራን ቱሪን ማምጣት ይፈልጋሉ::
:
የአለማችን ውዱ ተጭዋች ሆኖ ኦልትራፎርድ የደረሰው ፖል ፖግባ አንድ ጨዋታ በFAው ተቀጥቷል። ለዚህ ደግሞ ምክኛቱ ተጨዋቹ በኮፖ ኢጣሊያ በሁለት ተከታታይ ጨዋታዎች ላይ ቢጫ ካርዶችን በማየቱና ቅጣቱ ከሴሪአው ወደ ፕሪሚየር ሊጉ በመተላለፉ ነው።
:
ጁቬንትሶች ለፖግባ ምትክ ይሆነናል ያሉትን የቸልሲውን የመሀል ሜዳ ተጫዋች ሴስክ ፋብሬጋስ ላይ አነጣጥረዋል ቸልሲዎች የነ ንጎሎ ካንቴ እና ማቲች በአሰልጣኙ መፈለግ ልጁን ለመልቀቅ እድል ይፈጥርለታል ተብሏል
ቶተንሀም ሆትስፐርስ chadilን ለሚፈልግ ክለብ 20mil ፓውንድ ማቅረብ ይኖርበታል ብለዋል ስዋንሲ እና ዶርትሙንድ የልጁ ፈላጊዎች ናቸው
የማንችስተር ሲቲው ግብ ጠባቂ ጆ ሀርት በክለቡ የመቆየቱ ነገር ጥያቄ ምልክት ውስጥ ከቶታል ነው የተባለው
ጆሴ ሞሪንሆ አንድ የመሀል ተከላካይ ሊያስፈርሙ ይችላል ነው የተባለው ነገር ግን ተጫዋቹን የሚያስፈርሙት ሁዋን ማታን እና ሸዋንስታይገርን በመሸጥ በሚያገኙት ብር ነው ተብሏል
የሊቨፑሉ አሰልጣኝ የርገን ክሎፕ ለባላቶሊ እና ቤንቴክ የሚሆን ቦታ በሊቨርፑል የለም በማለት ተናግረዋል የሚሆነውን ነገር በቅርቡ እናያለን በማለት የዝውውር መስኮቱን መጨረሻ እየጠበቁ ይገኛሉ
ሚድስቦሮ የቀድሞ የማንችስተር ዩናይትድ ተጫዋች ፋቢዮ ዳ ሲልቫን ማስፈረማቸው አረጋግጠዋል
አርሰናሎች ተከላካያቸውን gabriel ን ቀዶ ህክምና ሊያደርግ መሆኑ ተገልጿል
አርሰናሎች የተከላካይ ክፍላቸው በጉዳት መዋዥቅ ተከትሎ የባርሴሎናውን ማቲውን ለማስፈርም ፍላጎት እንዳላቸው ተገልጿል
ጃክ ዊልሸር አርሰናል በአሁኑ ስብስብ ሻምፒዮን መሆን የሚችል ቡድን ነው በማለት በቡድኑ ትልቅ እምነት ጥሏል
የፒኤስጂው አሰልጣኝ emery ማቲውዲ የአለማችን ምርጥ ተጫዋች በማለት ተናግረዋል ልጁንም ለማቆየት የተጠቀሙት ዘዴ ነው ተብሏል
12/08/2016
እንኳን ደስ ያላቹ ኢትዮጵያዊያን እና የፔጁ ቤተሰቦች
አልማዝ አያና ወርቅ እና ክብረ ወሰን ለሀገሯ አበረከተች
አትሌት አልማዝ አያና ከሪዮ ኦሎምፒክ ለሀገሩዋ ኢትዮጵያ የመጀመሪያውን ወርቅ እና ክብረ ወሰን በ10ሺህ ሜትር አስገኘች፡፡
http://www.ebc.et/web/sport/-/---421
አልማዝ አያና ውድድሩን አስቀድማ በመውጣት አዲሱን የኦሎምፒክ ታሪክ ሰርታለች፡፡
ከብረ ወሰኑ በቻይናዊቷ ዋንግ ዥያን እ.አ.አ በ1993 ተይዞ ለ23 ዓመታት የቆየ ነው፡፡
አዲሱ ክብረ ወሰን 29፡17፡45 ነው፡፡ ይህ ሰዓትም የዓለም እና የኦሎምፒክ ክብረ ወሰን ሆኖ ተመዝግቧል፡፡
ጥሩነሽ ዲባባ ሶስተኛ ደረጃን በመያዝ ነሐስ አግኝታለች፡፡ ጥሩነሽ ዲባባ የገባችበት ሰዓት 29፡42.56 ነው፡፡
ኬኒያዊቷ ቪቪያን ችሪዮት የብር ሜዳሊያውን መውስድ ችላለች፡፡ ሌላዋ ኢትዮጵያዊ ገለቴ ቡርቃ 8ኛ ሆና አጠናቃለች፡፡
ውጤቱን ተከትሎ ለቀናት በውድድሩ ያለ ወርቅ የሰነበተችው አፍሪካ የመጀመሪያውን ወርቅ በአልማዝ ማግኘት ችላለች፡፡
ቀደም ብሎ በተካሄደው የ8 መቶ ሜትር ማጣሪያ ደግሞ ሙሀመድ አማን ሁለተኛ በመሆን ወደ ቀጣዩ ዙር ማለፍ ችሏል፡፡
ኢትዮጵያ ከ207 ተሳታፊ ሀገራት በአንድ ወርቅ እና ነሐስ ከዓለም 31ኛ ደረጃ መቀመጥ ችላለች፡፡ ከአፍሪካ ደግሞ ቀዳሚ ናት፡፡
አልማዝ አያና ወርቅ እና ክብረ ወሰን ለሀገሯ አበረከተች - Sport Display - Ethiopian Broadcasting Corporation አትሌት አልማዝ አያና ከሪዮ ኦሎምፒክ ለሀገሩዋ ኢትዮጵያ የመጀመሪያውን ወርቅ እና ክብረ ወሰን በ10ሺህ ሜትር አስገኘች፡፡አልማዝ አያና ውድድሩን አስቀድማ በመውጣት አዲሱን የኦሎምፒክ ታሪክ ሰርታለች፡፡
Click here to claim your Sponsored Listing.
Category
Telephone
Website
Address
Addis Ababa