KOBO TIMES

KOBO TIMES

Share

25/10/2021

ሀይቅ ትጣራለች እንድረስላት❗️
➖➖➖➖➖➖➖➖
ሀይቅ በወራሪው ጁንቴ ከተያዘች 4 ቀን ሆናት፣ ይሄ ንግድ ባንክ አጠገብ ፎቶ ተነስተው ካላየ በስተቀር ከተማ ያልተያዘ ለሚመስለው ገልቱ አይገባውም: ብዙ ሰው እየሞተ ነው: ዋሄሎ፣ ቀጤ፣ አሙሞ፣ ዳውቻ፣ ጎበያ እና ሌሎችንም የገጠር አከባቢዎች ነፃ ሳይወጡ ሀይቅ ነፃ አቶጣም፡ ቡዙ ኪሳራ ከመድረሱ በፊት እንፍጠን❗️
( )

25/10/2021

ለማሻ ከተማ ነዋሪወች በሙሉ!!
================
እስካሁኑ ሰዓት ባለን መረጃ መሰረት አንድም የጠላት ሀይል የበሽሎ ድልድይን ያለፈ የለም በተሳሳተ መረጃ ቤት ንብረታችሁን ለሌባ ለቃችሁ አትሂዱ!
#1ኛ.በያላችሁበት ቦታ ተረጋግታችሁ ሀብትና ንብረታችሁንና አካባቢያችሁን ጠብቁ
#2ኛ.የከተማችን ወጣቶች በየቁልፍ በሩና በመግቢያ መንገዶች ሁሉ ፀጉረ ልውጦችን ተከታተሉ
#3ኛ.የጠላት ሀይል ባሰፈሰፈበት የተሬ አካባቢ የተሳካ የድሮን ድብደባ ተካሂዷል።
#4ኛ በጉና ግንባር ተጨማሪ ሀይል እየጠየቅን መሆኑን አውቃችሁ የሚፈጠሩ አዳድስ ክስተቶች ካሉ የምናሳውቃችሁ ይሆናል።

#የወረዳው ወቅታዊ ጉዳዮች ኮማንድ ፓስት!!

Photos from KOBO TIMES's post 25/10/2021

የተደበደብኩበት እውነተኛ ምክንያት! (እስከንድር ነጋ)

" ከጎኔ ለቆማችሁት ሁሉ፣ ልባዊ ምስጋና ይድረሳችሁ። "

እስክንድር ነጋ፤
የኅሊና እስረኛ፤
ቂሊንጦ፤ አዲስ አበባ

ለሰሚው ግራ እንደሚገባ እረዳለሁ። በእኔ ዕድሜ ተደብዳቢም ሆነ ደብዳቢ የሚባል ሰው አያምርበትም። መደባደብ የሕፃናት ዘመን መለያ ነው። ግን እኮ በአንድ እጅ ማጨብጨብ አለመቻሉም ሌላ እውነታ ነው። በየትኛውም ዕድሜ ቢሆን፣ የግድ መደባደብ የሚፈልግ ካለ፣ ደብዳቢና ተደብዳቢ ይኖራል። ምንም ማድረግ አይቻልም። በዚህኛው ትዕይንት ደግሞ፣ አስደብዳቢም የተጨመረበት ስለሆነ፣ ነገሩን አወሳስቦታል።

ተደብዳቢ የሆንኹበትን ሂደት አልገባበትም። የአስደብዳቢዎቼ ወጥመድ ውስጥ መዘፈቅ ነው የሚሆነው። ለመማታት መጀመሪያ የሰነዘርሁት እኔ እሆናለሁ ብሎ የሚያስብ ይኖራል ብዬ አልገምትም። አውዱን ለማስቀመጥ ይህ ይበቃል። ሊደበድበኝ አስቀድሞ ስለሰነዘረብኝ በዙ ማለት ከንቱ ልፋት ነው የሚሆነው። ታላቁ መፅሐፍ እንደሚለው፣ የሚያደርገውን አያውቅምና፣ ወደ ቀናው መንገድ እንዲመለስ ፈጣሪ ይርዳው። በዚህ ልለፈው።

ከደብዳቢው በስተገርባ ስላሉት አስደብዳቢዎቼ ግን፣ ቢያንስ ትንሽ ማለት አለብኝ። ለሕዝባችን ጠቃሚ መረጃ አለኝ።

በዚህ ጊዜ፣ ሀገራችን የሞትና ሽረት ትንቅንቅ ላይ ናት። ትንቅንቁን እነ ዐብይ አህመድ ካሸነፉ፣ ኢትዮጵያ በኦ.ህ.ዴ.ድ. በሚመራ ጠንካራ ማዕከላዊ መንግሥት ሥር ሆና እንደ ሀገር ትቀጥላለች።

በአንፃሩ፣ ሕወሓት ካሸነፈ፣ ሁለት አማራጮች ይኖራሉ። ሕወሓት በቀዳሚነት በሚፈልገው አማራጭ፣ ኢትዮጵያ እንደ ዩጎዝላቪያ ወደ አራትና አምስት ሀገራት ትበተናለች። ይህ የማይሆን ከሆነ፣ እንደ ቦዝኒያ ትሆናለች። ፈረንጆቹ እንደ ቦዝኒያ መሆንን "ቦዝንፊኬሽን - Bosnification" ይሉታል። ይህ ማለት፣ ማዕከላዊ መንግሥቱ በይፋ የለም ባይባልም፣ በተግባር ግን እንደ ሌለ የሚቆጠር ይሆናል። እንዲህ ዓይነቱ ሁኔታ ለእኛ እንግዳ አይደለም። በታሪካችን "ዘመነ መሳፍንት" በሚለው መጠሪያ እናውቀዋለን።

ጉዳዩ ይህንን ያህል ክብደት እያለው፣ እንደ እኔ ፖለቲካ ውስጥ ያለ ሰው ዝም ማለት አይችልም። ፖለቲካ ያለ ሀገር ሊኖር አይችልም። ሁለቱም የሕወኃት መንገዶች ሀገር የሚያጠፉ ናቸው።

ግን፣ ይህ ማለት፣ ኢትዮጵያን የምንፈልጋት ሰዎች ለእነ ዐብይ ጭፍን ድጋፍ መስጠት አለብን ማለት ነው ወይ? እኔ፣ "አይደለም፤ ድጋፋችን ጭፍን መሆን የለበትም" ባይ ነኝ። በተለይ፣ እነ ዐብይ ጦርነቱን መምራት እንዳቃታቸው በግልፅ እየታየ ባለበት በዚህ ጊዜ።

ይህ አቋሜ ነው ደብዳቢ እንዲላክብኝ ያስደረገው። ለአሁኑ ይህን ብቻ የኢትዮጵያ ሕዝብ ይወቅልኝ። ሌላውን ሌላ ጊዜ እመለስበታለሁ።

ለጊዜው አጥንቴ ተሰብሯል። በዚህ ብቻ በማለፉ ቸሩ መድኃኒዓለምን አመሰግነዋለኹ። ከዚህ በኋላ ተጨማሪ ጥቃት ማድረስ ይከብዳቸዋል።

ከጎኔ ለቆማችሁት ሁሉ፣ ልባዊ ምስጋና ይድረሳችሁ።

ፈጣሪ ኢትዮጵያን ይጠበቅ፣ ይባርክ!

Photos from KOBO TIMES's post 23/10/2021

ጥንቃቄ ይደረግ❗️
➖➖➖➖➖
ከሰአታት በፊት ማንነታቸው ያልታወቁ 28 ግለሰቦች በሎጊያ ከተማ በቁጥጥር ስር መዋላቸውን ገልጬ ነበር: ይህም ዜና በሌሎች ሚዲያዎችን ሲዘዋወር ታዝቤለሁ: አሁን ባደረኩት ማጣራት ግለሰቦቹ ከራያ ቆቦ መተው ብር ከደሴ እና ከኮምቦልቻ አውጥተው ወደ ራያ ቆቦ የሚመለሱ የራያ ቆቦ ተወላጆች መሆናየውን ሰምቻለሁ፣ ብራቸው እንዲመለስላቸውና ጉዟቸውን እንዲቀጥሉ ለሚመለከተው አካል አሳስባለሁ❗️
( )
Afarovich mohammed

Want your business to be the top-listed Media Company in Addis Ababa?
Click here to claim your Sponsored Listing.

Culinary Team

Attire

Telephone

Website

Address


Addis Ababa