Deacon Girma

Deacon Girma

Share

08/11/2025

በቤተ ክርስቲያን አይኮረፍም!
በቤተ ክርስቲያን ውስጥ ብዙ ሰነፍና ዋልጌ ሰዎች መኖራቸው መቼም የማናስተባብለው ሐቅ ቢሆንም በቤተ ክርስቲያን ግን አይኮረፍም!
የቤተ ክርስቲያንን እንጀራ እየበሉ የምእመናን ሕይወት የማይገዳቸው፤ ስለደመወዛቸው ካልሆነ በቀር ስለምእመናን መብዛትና ስለዘለዓለም ሕይወታቸው የማያስቡ ምንደኞች ቢበዙባትም በቤተ ክርስቲያን አይኮረፍም!
ተናግረው የሚያናግሩ፤ ለሰው ስሜት የማይጠነቀቁ፤ አማረልኝ ብለው እንዳመጣላቸው የሚያወሩ፤ ንግግራቸው ቤተ ክርስቲያንንና አገልግሎቱን ሊጎዳ እንደሚችል ማሰብ የማይፈልጉ፤ ሥራዬ ብለው ምእመናን እንዲበተኑ የሚተጉ፤ ከሩቅ የሚመልሱ . . . ሰነፍ እረኞች ቢኖሩም በቤተ ክርስቲያን አይኮረፍም!
ከቤተ ክርስቲያን ወጭት እያጠቀሱ ግን ደግሞ ምእመናንን የሚያሳፍሩ፤ የሚያስቆጡ፤ የሚያስከፉና የሚገፉ . . . ብዙ የቤተ ክርስቲያን ሰዎች ቢኖሩም በቤተ ክርስቲያን አይኮረፍም!
ከዘመኑ ጋር የማይሔዱ፤ የምእመናን ሁለንተናዊ እድገትና መሻሻል ግድ የማይሰጣቸው፤ ምንም ርዕይ የሌላቸው፤ ዛሬ ብቻ እንጂ ነገ የማያሳስባቸውና የማይገዳቸው ብዙ የቤተ ክርስቲያን አገልጋዮች ቢኖሩም በቤተ ክርስቲያን አይኮረፍም!
“የአባትህ ቤት ሲዘረፍ አብረህ ዝረፍ” በሚል ብሒል እንጀራ የሚበሉበትን መሶብ የሚገለብጡ፤ ወርቅ ያለበሰቻቸውን ቤተ ክርስቲያን የሚያራቁቱ፤ የቤተ ክርስቲያናችን ነገዋ ግድ የማይሰጣቸው ብዙ “አገልጋዮች” ቢኖሩም በቤተ ክርስቲያን አይኮረፍም!
በቤተ ክርስቲያን አይኮረፍም! . . . ምክንያቱም እርሷ እናታችን ናትና! በእናት እንዴት ይኮረፋል!!!
በቤተ ክርስቲያን አይኮረፍም! . . . ምክንያቱም እርሷ የነውራችን ክዳን፤ የዕርቃናችንም ልብስ ናትና!!!
በቤተ ክርስቲያን አይኮረፍም! . . . ምክንያቱም እርሷ ፍጽምት የምትሆን የክርስቶስ አካሉ ናትና!
በቤተ ክርስቲያን አይኮረፍም! . . . ምክንያቱም የአገልጋዮች ድካም የክርስቶስን ጸጋ አያስቀርብንምና፤ መስዋዕቱ እንዳያርግ፤ ምሥጢራቱም እንዳይፈጸሙ አያግዳቸውምና!!!

በቤተ ክርስቲያን አይኮረፍም! . . .

በኤዶም ኃይሉ

08/11/2025
🔴 አዲስ ዝማሬ " ምስክሩ ነኝ " ዘማሪ ዲያቆን ግርማ ንጉሤ @-mahtot 06/11/2025

🔴 አዲስ ዝማሬ " ምስክሩ ነኝ " ዘማሪ ዲያቆን ግርማ ንጉሤ @-mahtot 🔴 በማኅቶት ቲዩብ የተለቀቁ ተወዳጅ መዝሙሮችን ለማግኘት ይህንን ሊንክ ይጫኑ፡፡ 👇 👇 👇 https://bit.ly/3C2YHGpአዲስ ዝማሬ " ምስክሩ ነኝ " ዘማሪ ዲያቆን ግርማ ንጉሤ

04/11/2025

Arsii, dachee dhiiga Ortodoksii
🙏 Du'uun ni gaha 🙏
Arsii, dachee dhiiga Ortodoksii
🙏 Du'uun ni gaha 🙏

04/11/2025

ይኼንን ጽሑፍ ቁጭ ብለህ እያነበብህ ያለኸው በዚህ ሰዓት ምሥራቅ አርሲ ገጠር ውስጥ ስላልተገኘህ ብቻ ነው:: በዚህች ቅጽበት በሥጋት ውስጥ ሆነው "ከአሁን አሁን ምን ይመጣብን ይሆን?" እያሉ ያሉ የኦሮሚያ ምእመናን ቁጥራቸው ብዙ ነው:: ከቀናት በፊት የተገደሉትን ተናግረን ሳናበቃ አሁን ደግሞ ሌላ ቦታ አምስት እንደተገደሉ እየሰማን ነው::

ሰሞኑን ከሁለት ሺህ ዓመታት በፊት ሔሮድስ ስላሳደዳት እመቤታችን "ሰቆቃወ ድንግል" እያልን እያዘንን ነው:: ከሰይፍ ልጅዋን ማስጣል ያልቻለች የአርሲዋን እናትስ እንዴት ዝም እንበላት? ይህንን የማያቆም ሞት ዜና ሰምተን ወደ ጉሮሮአችን የሚወርድ ምግብና መጠጥ የምንተኛውም እንቅልፍ የለም:: የእነርሱ ሞት የእኛ ሞት ነው:: የእነርሱ መቁሰል የእኛ ቁስል ነው:: የቦታ ለውጥ እንጂ በእነርሱ የደረሰው በእኛም ሊደርስ ይችላል::

ቤተ ክርስቲያን ምሕላ እንድታውጅ ፣ ለተሠዉት ተገቢውን ክብር እና ጸሎተ ፍትሐት እንድታደርግ እንጠብቃለን:: ቤተ ክርስቲያን በየትኛውም ቦታ የንጹሐን ደም ዳግመኛ እንዳይፈስስ እንደ ራሔል ዕንባዋን የምትረጭበት ጊዜ አሁን ነው::

የቤተ ክርስቲያን አስተዳደር ትኩረት ያልሠጠውን ችግር ሌላ አካል ሊጨነቅበት አይችልም:: ስለዚህ ቤተ ክርስቲያን በአስተዳደራዊ መዋቅርዋ መንግሥት ተገቢውን እርምጃ እንዲወስድ በሙሉ ትኩረት የምትሠራበት ጊዜም አሁን ነው:: ቅዱስ ሲኖዶስ በዚህ ዓይነት ጊዜ የሚያሳየው ምላሽ ከሌለ ሌላ ቀን ቢጣራ የማይሰማውን ቤተ ክርስቲያን አልባ ክርስቲያን በራሱ ላይ ይፈጥራል:: ሐዋርያዊትዋ ቤተ ክርስቲያንም በክህነት የማትመራ የመሆን አደጋ ይገጥማታል:: ክህነት ከሌለ ደግሞ ቤተ ክርስቲያንም ምሥጢራትም የሉም::

ኦርቶዶክሳውያን ምእመናንም ይህንን ጊዜ ለመካሰስ ፣ አባቶችን ለመሳደብ ፣ አንዱ ሌላውን ለማስጠቆርና ለመናቆር ሳይሆን ለጸሎት ለምሕላና ለሰብአዊ ሥራና መሬት ላይ ቢወርዱ ችግሮችን የሚፈቱ ዘላቂ መፍትሔዎች ላይ በትብብር ለመሥራት ምክንያት ብናደርገው የተሻለ ነገር ማምጣት እንችላለን::

የሌላ እምነት ተከታዮች ሆነው ይህ በኦርቶዶክሳውያን ላይ ብቻ ሳይሆን በኢትዮጵያውያን ላይ የተቃጣ ጥቃት ብለው ጉዳዩን በተቋምም በግልም ያወገዙ ሰዎችን እናከብራለን:: "ይበላችሁ" ብለው የተሳለቁትን እና በክፉ ቀን ክፋታቸውን ላሳዩን ደግሞ እውነተኛ ማንነታቸውን ስላሳዩን እያመሰገንን "አቤቱ፥ በኢየሩሳሌም ቀን የኤዶምን ልጆች አስብ፦ “እስከ መሠረትዋ ድረስ አፍርሱ አፍርሱ፡” ያሉአትን" ብለን ለሰማያዊው ዳኛ ሠጥተናቸዋል:: መዝ. 137:7

01/11/2025

ወረብ
ትመስል እምኪ ማርያም ዕለተ ሣልስተ ወራብዕተ ትመስል እምኪ/፪/
ዘወለደት ጽጌ ጽጌ ጽጌ ወፀሐየ ዓለም/፪/

ትርጉም፦
ማርያም ! የዓለም ፀሓይ የሆነ ክርስቶስን እና ጽጌ የተባልሽ አንቺን የወለደች እናትሽ ሦስተኛዋን እና አራተኛዋን ቀን ትመስላለች ።

Want your practice to be the top-listed Law Practice in Addis Ababa?
Click here to claim your Sponsored Listing.

Category

Address


Ortodoks Tewahido Zemari
Addis Ababa