YoniTech & Mobile
https://a.pbfbb.net/go/MY?u=SWMFBXIL&sid=&c=MY&s=cp&lang=EN&ch=68&cl=44
Poly Beau Sign up for a gift of $200, complete the novice process, and you can withdraw your income
🛡 ፍላሽ ዲስክ ከኮምፒውተራችን ጋር ተጠቅመን ከጨረስን በኋላ Eject ማድረጋችን ምንድን ነው ጥቅሙ?
- አብዛኞቻችን ልብ የማንለው ጉዳይ!
👉 ፍላሽ፣ External Hard Disk፣ እንዲሁም CD/DVD ከኮምፒውተራችን ሰክተን ተጠቅመን ስንጨርስ በቀጥታ የሚታየን ነገር ቢኖር በቶሎ ፍላሹን፣ External Hard Disk መንቀል ወይም CD/DVD ከሆነ ደግሞ ሲዲው ዝምብሎ ማውጣት ነው።
- ነገር ግን አብዛኛዎቻችን ፍላሼ፣ External ሀርድ ዲስኬ፣ የምጠቀምበት ሲዲ አልሰራልኝ አለ?
ኮራፕት አደረገብኝ፣ ፍላሽ ዲስኬ Write Protected ሆነብኝ፣ ፍላሽ ዲስኬ ከነጭራሹ ከኮምፒውተሬ ጋር ብሰካው እይሰራም፣ ፍላሽ ዲስኬን ከኮምፒውተሩ ጋ ስሰካው ድምጽ ያሰማኛ ግን My computer ጋ ስሄድ የለም የሚል በብዛት የሚነሳ ጥያቄ ነው።
~ ለዚህ ሁሉ ችግር ተጠያቂዎቹ እኛው ነን።
👉 ቅድመ ጥንቃቄ ማድረግ አለባችሁ።
- በመጀመሪያ ደረጃ ፍላሽ ዲስክ፣ External ሀርድ ዲስክ፣ ሲዲ/ዲቪዲ ወደ ኮምፒውተር ስንሰካና ኮምፕዩተሩ Read/ Write process ያደርጋል.... ይህ ማለት ስራ እየሰራ ነው ማለት ነው።
👉 ፍላሽ ዲስክ፣ External ሀርድ ዲስክ፣ ሲዲ/ዲቪዲ ወደ ኮምፒውተር ሰክተን ፋይል ለምሳሌ ከኮምፒውተር ወደ ፍላሽ፣ ከፍላሽ ወደ ኮምፒውተር, ከExternal Hard Disk ወደ ኮምፒውተር ...... መረጃ ስናገላብጥ አሁን ሁሉም ስራ ላይ ናቸው ማለት ነው።
ስለሆነም መረጃ እያላላክን ሳለ ከተሰካበት ብንነቅለው። ከገባበት ብናወጣው ስራውን ሳይጨርስ አቋረጥነው ማለት ነው በዚህ አጋጣሚ የመበላሸት አጋጣሚው በጣም ሰፊ ነው በተለይ ደግሞ ለExternal Hard Diskና CD/DVD እንዲሁም ፍላሽ ዲስኮች።
👉 ስለሆነም ማንኛውንም ከኮምፒውተር ጋር የሚሰኩ Storage Device በጥንቃቄ በሚከተለው ፕሮሰስ ፍላሽ ዲስክ፣ External ሀርድ ዲስክ፣ ሲዲ/ዲቪዲ ከኮምፒውተራችን ሳንነቅለው በፊት Eject ማድረግ አለባችሁ።
👉 Start -> All Program -> Computer or This PC -> ወደ ፍላሻችን ወይም External Hard Disk..... በመሄድ Right click በማድረግ Eject የሚለውን ይጫኑ። - ከዛም ቢያንስ ለ5 ሰከንድ ይጠብቁ በቅድሚያ ግን ከፍላሽ ዲሳክችን....... የተከፈተ ማንኛውንም ፕሮግራም መዝጋት አስፈላጊ ነው።
🚩 Eject ጥቅም ከኮምፒውተር ጋ የተሰካን ማንኛውንም ነገር ግንኙነቱን ያቋርጣል ማለት ነው እንደገና ግንኙነቱ እንዲቀጥል ከፈለጋችሁ እንደአዲስ በመንቀል መሰካት ያስፈልጋል።
👉 ይህ ተግባር የሁልጊዜ ስራችንና ተግባራችን ይሁን!
📢: ✅Credit :-
📤 ➩ ሀሳብ/አስተያየት :↩️
📣:
Click here to claim your Sponsored Listing.
Category
Contact the business
Website
Address
Addis Ababa