Dymans-Eth
12/11/2020
የሕዝብ ተወካዮች ም/ቤት ባካሄደው 4ኛ መደበኛ ስብሰባው ላይ 'በወንጀል የተጠረጠሩ' የምክር ቤት አባላትን ያለመከሰስ መብት ማንሳቱን አሳወቀ።
በዚህም መሰረት፦
- ዶክተር ደብረጸዮን ገብረሚካኤል
- አቶ አስመላሽ ወልደሰንብት
- አቶ አባይ ፀሃዬ
- ዶክተር አምባሳደር አዲስ ዓለም ቤሌማ
- አቶ ጌታቸው ረዳ
- አቶ አፅበሃ አረጋዊ
- አቶ ገብር እግዚአብሄር አርአያ ጨምሮ ሌሎችን ግለሰቦችን ያለመከሰስ መብታቸውን ምክር ቤቱ አንስቷል።
ግለሰቦቹ የተጠረጠሩባቸው ወንጀሎች የጦር መሳሪያ ይዞ በማመፅ ፣ የሀገር መከላከያን በመውጋትና በሌሎች ተያያዥ ወንጀሎች ዋና አድራጊነት ነው ተብሏል።
በሌላ በኩል፦
የህ/ተ/ም/ቤት አቶ ፍቅሩ ገ/ሕይወትን የምርጫ ቦርድ አባል አድርጎ ሾሟል። (ኢቲቪ-HoPR)
DYMANS - ETH
11/04/2020
የኮቪድ-19 ወረርሽኝ ስርጭትን ለመከላከል፣ ለመቆጣጠርና የሚያስከትለውን ጉዳት ለመቀነስ የወጣው የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ማስፈፀሚያ ደንብን የፌዴራል ጠቅላይ አቃቤ ህግ ይፋ አደረገ።
ክልከላን በሚመለከት፦
- ማንኛውም ሃይማኖታዊ ይሁን ፖለቲካዊ ስብሰባዎች፣ እድር፣ ደቦ፣ እቁብና ሌሎችም ከ4 ሰው በላይ ስብሰባዎች ክልክል ናቸው።
-አራት ሰዎችም ቢሆኑ ሁለት የአዋቂ ሰው እርምጃ የጠበቀ መሆን አለበት።
- ቀብርና ሌሎች አስፈላጊ ጉዳዮች ሲኖሩ ግን እየታዩ ሊፈቀዱ የሚችሉበት አሰራር ይኖራል።
- ታራሚዎች ከጠበቆቻቸው ጋር አስፈላጊው ጥንቃቄ ተደርጎ እንዲገናኙ የሚፈቀድ ቢሆንም ጥየቃ ለሚሄዱ ሰዎች አይፈቀደም።
- በፖሊስ የተያዙ እስረኞችንም ስንቅ ከማቀበል በስተቀር መገናኘት የተከለከለ ነው።
- በድንበር አካባቢ ከካርጎ፣ የደረቅና ፈሳሽ ጭነት አገልግሎቶች በስተቀር ሌሎች እንቅስቃሴዎች ዝግ ተደርገዋል።
- የቤት ተከራዮች በራሳቸው ፍላጎት ካልወጡ በስተቀር ማስወጣትና ኪራይም መጨመር በአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ ተከልክሏል።
- ሰራተኞችን መቀነስና የስራ ቅጥር ውል ማቋረጥም ተከልክሏል።
- ተማሪዎችና መምህራን በኦን ላይን ካልሆነ በአካል እንዲገናኙ አይፈቀድም።
Click here to claim your Sponsored Listing.
Category
Contact the business
Website
Address
Addis Ababa