Basketo Intellectuals Association-BIA

Basketo Intellectuals Association-BIA

Share

Photos from Basketo Intellectuals Association-BIA's post 25/05/2026

ኢዜማ ባስኬቶ

በሻንካ ጋምጋይላ ቀበሌ

⚖️

ኢዜማ ባስኬቶ በሁሉም የዞኑ ቀበሌያት ሀሳቡን ለመራጩ አቅርቦ የመራጩን ጥያቄ እና የህዝቡን የጋራ አጀንዳ በማንገብ የዜግነት ፖለቲካን በመከተል መዳረሻውን ማህበራዊ ፍትህ ለማድረግ በብርቱ ጥረት እየሰራ ይገኛል።

የተሻለች ኢትዮጵያ እስክትመጣ ኢዜማ ትግሉን ከኢትዮጵያ አርሶ አደሮችና አርብቶ አደሮች ጋር ያደርጋል!
⚖️
ኢዜማን ይምረጡ!
⚖️

25/05/2026

እንኳን ለዓለምአቀፉ የእግር ኳስ መታሰቢያ ቀን በሰላም አደረሳችሁ!
⚽ ⚖️ ⚽ ⚖️

በየዓመቱ መጋቢት 17 ወይም May 25 የተባበሩት መንግስታት ቀን በዓለምአቀፍ ደረጃ የእግር ኳስ ቀንን ያከብራል። የመንግስታቱ ድርጅት የእግር ኳስ ሀይልን በማመን በመላው ዓለም ለሚገኙ የእግር ኳስ ተጫዋቾች: አስተዳደሮችና ደጋፊዎች የዓለምን አንድነት ለማስከበር ባላቸው ሚና የተነሳ የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክት ያስተላልፋል።

እኛ የእግር ኳስ አፍቃሪዎች ተከታታይ የኢዜማ አባላትና ደጋፊዎች በዞናችን ላሉ ሁሉም የእግር ኳስ ተጫዋቾች: አመራሮችና ደጋፊዎች በሙሉ እንኳን አደረሳችሁ ለማለት እንወዳለን።

እግር ኳስ የሰው ልጆችን በሙሉ ዘር ቀለም ሳይለይ አንድ የሚያደርግና የማህበራዊ ፍትህ እንዲሰፍን በዘርፉ ከፍተኛ ድጋፍ እንደሚያደርግ አካል እንኳን አደረሳችሁ ለማለት ይወዳል።

በዛሬው ዕለትም ለመላው የባስኬት ቡና እግር ኳስ ክለብ ተጫዋቾች: አመራሮችና ደጋፊዎች በሙሉ እንኳን አደረሳችሁ ለማለት ይወዳል!
⚖️
በድጋሚ እንኳን ለዓለምአቀፉ የእግር ኳስ ቀን በሰላም አደረሳችሁ!

Photos from Basketo Intellectuals Association-BIA's post 24/05/2026

ኢዜማ ባስኬቶ

በዛባ አካባቢ የምርጫ ቅስቀሳ አደረገ። የላስካ 02 ቀበሌ ነዋሪዎችን ተደራሽ ያደረገ የመሠረተ ልማት እና የመልካም አስተዳደር ጥያቄ ላይ የማህበረሰቡን ፍላጎት ያማከለ የግንዛቤ ማስጨበጫ አድርጓል።

ኢዜማ በዛባ እና አካባቢው ቀበሌያት ነዋሪዎች በቀጣይ የምርጫ ሳምንት ውስጥ የኢዜማ የምርጫ ምልክትና የፓርቲውን ፖሊሲዎች የኢዜማ ላስካ መደበኛ የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ምክር ቤት ዕጩዎች ተገኝተዋል።

የዛባ እና አካባቢው ነዋሪ ምርጫ ኢዜማ እንደሆነ አረጋግጧል!
⚖️
ባለሚዛን ምልክቱን ኢዜማን ይምረጡ!

24/05/2026

በሀቅ አደባባይ

እውነት ጎልቶ እንዲታይ

በፖለቲካ ውጣ ውረድ ውስጥ እንደአንድ ህዝብ እንደማህበረሰብ በጋራ ቆመን በአብሮነት መወሰን እስካልቻልን ድረስ ወደ መግባባት አንመጣም። ለዓመታት በጋራ ጉዳያችን ላይ ውሳኔ የሰጡ ግለሰቦች በውሳኔዎቻቸው ማፈርና መሸማቀቅ ሲገባቸው ወደኋላ ለቀረንበት ውሳኔያቸው ተጠያቂ አካል በመፍጠር ጊዜያቸውን ማራዘም ይሻሉ።

በሀቅ አደባባይ ላይ በእውነት ሚዛን መስራት ሲገባን በጥቃቅን ፍላጎቶቻችን ከማህበረሰባችን የወጡ አካላትን እያገለልን ስናርቃቸው ከርመናል። አሁን የህዝቡን ክቡር ሀሳብ የምንቀበልበት ወቅት ላይ እንገኛለን። የግል ጥፋቶቻችን ለመሸፋፈን የምናደርጋቸው ተጨማሪ ልፍያዎች ከታሪክ ተጠያቂነት እስከ ወንጀለኛነት ያስወስናሉ።

ገዢዎቻችን በኛ ጉዳይ የሰጡን ውሳኔ በሙሉ ዛሬ ላለንበት አዘቅት መነሻ ሆኗል። ከገባንበት ውጥንቅጥ የምንወጣው በእናንተው ስሁት ውሳኔ ሳይሆን በህዝባችን ቀጥተኛ ፍላጎት ነው።

አስፈፃሚዎቻችን ለዘመናት አቅልለው በወሰኑብን አንድ ትውልድ ወደኋላ እንዲቀር አድርገዋል። ለዚህም ተግባራቸው ተጠያቂነታቸው ሊረጋገጥ ይገባል!
🤝

Photos from Basketo Intellectuals Association-BIA's post 22/05/2026

ኢዜማ በላስካ ዙሪያ ወረዳ

በጌዜ ኣይማ ቀበሌ

ከማህበረሰቡ ጋር ውይይት እያደረገ ነው።

Want your organization to be the top-listed Non Profit Organization in Addis Ababa?
Click here to claim your Sponsored Listing.

Website

Address


Basketo Laska
Addis Ababa