WanawTena

WanawTena

Share

07/05/2022

የእናቶች እንግልት እና የጤና ባለሙያዎች ስቃይ በወላይታ ዞን ዉስጥ እንደቀጠለ ነዉ!

ከዚህ በፊት በወላይታ ኦቶና ሆስፒታል መድኃኒት መግዛት የማይችሉ እናቶች የራሳቸዉንም ሆነ የጽንሳቸዉን ህይወት እያጡ እንደሆነ በማስረጃ ተደግፎ በማህበራዊ ሚድያ ተዘግቧል፣ እኔም አቅርቤው ነበር።

እዉነትነቱም ተረጋግጦ የማስተካከያ እርምጃ የተባሉ ሙከራዎች ተደርገዉ ነበር። ግን የተባሉት እርምጃዎች ከ3 ቀን በላይ ዘለቄታ አልነበራቸዉም። አሁንም የገንዘብ አቅም የሌላቸዉ እየሞቱና 9 ወር የተሸከሙትን ጽንሳቸዉን እያጡ ይገኛሉ።

እጅግ በጣም የሚያሳዝነዉ የነገሩ እዉነትነት እንዳይመዘገብ ከፍተኛ ማስፈራሪያ ለጤና ባለሙያዎች ስለተሰጠ የችግሩን ልክ ራሱ ማወቅ አይቻልም። ነገር ግን በሀገር አቀፍ ደረጃ የእናቶች ህክምና ነጻ እየተሰጠ እንደሆነ ሁላችንም የምናዉቀዉ ቢሆንም የወላይታ እና አካባቢዉ እናቶች ለዚህ አልታደሉም።

ሌላዉ የጤና ባለሙያዎች የሰባት ወር duty ክፍያ አልተሰጣቸዉም። ሌሊት ያለ እንቅልፍ፣ ሰንበትንና በዓላትን ከቤተሰብ ተለይተዉ ደከመኝ ሳይሉ የሰሩትን የላባቸዉን ክፍያ አልተሰጣቸዉም። ይባስ ብሎ ይህን የጠየቀ ማንም ቢሆን የጁንታ ተላላኪ ነዉ የሚል ስም በመስጠት ባለሙያ እያሸማቀቁና ከስራም ለማባረር ማስጠንቀቂያ ይሰጣል።

ኦቶና ብቻ ሳይሆን ወላይታ ዞን ዉስጥ ባሉ የጤና ተቋማት ለባለሙያ duty አለመክፈል፣ ከደመወዝ እንደፈለጉ መቁረጥ፣ለመጠየቅ የሞከረ ባለሙያ ማሰር፣ ማስደብደብ፣ የተለያዩ እርምጃዎችን መዉሰድ የተለመደ ሆኗል።

ይህ ብቻ አይደለም፣ የጤና ባለሙያ የመድኃኒት ሌባ በማለት ስም የማጥፋት ዘመቻ ተደርጎበታል። ከዚህ የተነሳ ታካሚዎች በተቋማት ያሉ ጤና ባለሙያዎችን ሌባ እያሉ ቁስላቸዉ ላይ እንጨት አየሰደዱ ሀኪሞችን እጅግ እያሳዘኑ ይገኛሉ።

መንግስት ይህንን ችግር ላንዴና ለመጨረሻ ፈትሾ መፍትሄ ቢሰጥ መልካም ነው።

Want your business to be the top-listed Beauty Salon in Addis Ababa?
Click here to claim your Sponsored Listing.

Category

Telephone

Address


Addis Ababa