Cynoox Technology
05/08/2023
ያለመከሰስ መብት ያለውን የህዝብ እንደራሴ አቶ ክርስቲያን ታደለን ፌደራል ፖሊስ አስሮታል።
05/08/2023
የአዲስ አበባ የምክር ቤት አባል የሆኑትን ዶክተር ካሳ ተሻገርን በሌሊት ፖሊሶች ቤቱ ድረስ መጥተው አስረውታል❗❗
04/08/2023
ዛሬ የሚኒስትሮች ምክር ቤት በ " አማራ ክልል " የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ እንዲደነገግ ውሳኔ ማሳለፉ ይታወቃል።
አመሻሹን ደግሞ የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ እንዴት ተግባራዊ እንደሚደረግ እንዲሁም የሚወሰዱ እርምጃዎች እና ተከለከሉ ተግባራት ዝርዝር ይፋ ተደርጓል።
በዚህም ፤ የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁን የሚያስፈፅም በብሔራዊ መረጃና ደህንነት አገልግሎት ዳይሬከተር ጄነራል የሚመራ የአስቸኳይ ጊዜ ጠቅላይ መምሪያ ዕዝ መቋቋሙ ተገልጿል።
የአስቸኳይ ጊዜ ጠቅላይ መምሪያ ዕዙ አባላት፣ መዋቅር እና አደረጃጀት በጠቅላይ ሚኒስትሩ የሚወሰን ይሆናል ተብሏል።
የአስቸኳይ ጊዜ መምሪያ ጠቅላይ ዕዙ ተጠሪነት ለኢፌድሪ ጠቅላይ ሚኒስትር እንደሚሆንም ተገልጿል።
በአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ የሚወሰዱ እርምጃዎችና የተከለከሉ ተግባራት ምንድናቸው ?
- ማንኛውም ሰው በአዋጁ መሰረት የሚወጡ መመሪያዎችን፣ የሚሰጡ ትዕዛዞች እና የሚተላለፉ ውሳኔዎችን የመተግበር እና የማከበር ግዴታ አለበት ተብሏል።
- የአስቸኳይ ጊዜ ጠ/መምሪያ ዕዙን እንቅስቃሴና የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁን አላማ #የሚቃረን ፣ #የሚቃወም እና በክልሉ የአመጽ እንቅስቃሴን የሚያበረታታ ፣ ሰላማዊ ዜጎችን የሚያሸብር፣ እንዲሁም የፀጥታ መደፍረሱን የሚያባብስ ንግግር፣ የቀጥታም ሆነ የተዘዋዋሪ ቅስቀሳ በማንኛውም መንገድ ማድረግ ወይም ማሰራጭት የተከለከለ መሆኑ ተመላክቷል።
- በየትኛውም መንገድ፣ በቀጥታ ሆነ በተዘዋዋሪ ለታጣቂ ቡድኖች የገንዝብ፣ የመረጃ፣ የቁስም ሆነ የሞራል ድጋፍ ማድረግ የተከለከለ መሆኑ ተገልጿል።
- ከአስቸኳይ ጊዜ ጠቅላይ መምሪያ ዕዙ ፈቃድ ውጪ ማንኛውንም የአደባባይ ስብሰባ ወይም ሰላማዊ ሰልፍ ማድረግ እንዲሁ ተከልክሏል።
- ከአስቸኳይ ጊዜ ጠ/መምሪያ ዕዙ ፈቃድ ውጭ ማናቸውንም የጦር መሳርያ ይዞ መንቀሳቀስ እንደማይቻል ተመላክቷል።
(ተጨማሪ ዝርዝር ጉዳዮችን ከላይ ያንብቡ)
04/08/2023
የሸኔ ታጣቂዎች በጉራጌ ዞን ቡኢ ከተማ በሚገኝ ፖሊስ ጣቢያ ላይ ጥቃት መፈጸማቸው ተገለጸ
በደቡብ ክልል በጉራጌ ዞን የሶዶ ወረዳ ዋና መቀመጫ በሆነችው ቡኢ ከተማ ራሱን የኦሮሞ ነጻነት ሠራዊት ብሎ የሚጠራው እና በመንግሥት “ኦነግ ሸኔ” በሚል በአሸባሪነት የተፈረጀው ኃይል፤ በከተማው በሚገኘው ፖሊስ ጣቢያ ላይ ጥቃት መፈጸሙን ነዋሪዎች ለአዲስ ማለዳ ገልጸዋል፡፡
ታጣቂዎቹ ጥቃቱን የተፈጸሙት በረቡዕ ሐምሌ 26/2015 ሌሊት አምስት ሰዓት ገደማ መሆኑን የጠቆሙት ነዋሪዎቹ፤ ጥቃቱ በፖሊስ ጣቢያው የታሰሩ ከ30 በላይ የሽብር ቡድኑን አባላት ለማስፈታት መሆኑን ተናግረዋል፡፡
የታጣቂ ቡድኑ አባላት ወደ ከተማው የገቡት በሞተር ሳይክልና በባጃጅ ተሸከርካሪዎች መሆኑን ጠቅሰውም፤ ከፖሊስ ጣቢያው ጠባቂ ፖሊሶች ጋር ለአንድ ሰዓት ያህል የዘለቀ የተኩስ ልውውጥ ማድረጋቸውን ገልጸዋል፡፡
Click here to claim your Sponsored Listing.
Category
Contact the business
Website
Address
Addis Ababa
Addis Ababa