Addis Hiwot General Hospital

Addis Hiwot General Hospital

Share

14/11/2025

ዛሬ ህዳር 5 🌍 አለም አቀፍ የስኳር ህመም ግንዛቤ ማስጨበጫ ቀን ነው፡፡
ከዚህ ጋር ተያይዞ ከስኳር ህመም ጋር የሚኖሩ ሰዎች የስኳር መጠናቸውን ለመቆጣጠር እና እራሳቸውን ለመንከባከብ የሚያግዛቸውን ነጥቦች እናንሳ። 💙

1️⃣ አመጋገብን ማስተካከል

🥗 ከአትክልት፣ 🍗 ከፕሮቲን እና 🌾 ካልተፈተጉ እህሎች የሚዘጋጁ ምግቦችን ማዘውተር

2️⃣ የአካል ብቃት እንቅስቃሴ ማድረግ

🚶‍♂️ በቀን 30 ደቂቃ እንቅስቃሴ ማድረግ ደም ውስጥ ያለውን የስኳር መጠን ለመቀነስ ይረዳል።

3️⃣ የታዘዘ መድሃኒትን በአግባቡ እና በሰዓቱ መውሰድ 💊

4️⃣ ደም ውስጥ ያለውን የስኳር መጠን በመለካት መከታተል 🩸

5️⃣ የስኳር ማነስ ምልክቶችን መለየት

የረሃብ ስሜት፣ ማላብ፣ መንቀጥቀጥ፣ የልብ ምት መጨመር
👉 እነዚህ ሲከሰቱ ወዲያው ከረሜላ 🍬 ወይም ስኳር ይውሰዱ ከዚያም በቅርብ ወዳለ ጤና ተቋም መሄድ ያስፈልጋል። 🏥

6️⃣ በየጊዜው በሃኪም የሚታዘዙ ምርመራዎችን ማድረግ

🦶 በየቀኑ የእግሮችን ጣቶች መመርመር
🧪 በየ3 ወሩ HbA1C ምርመራ ማሰራት
👁 በየዓመቱ የአይንና ኩላሊት ምርመራ ማድረግ

7️⃣ የጥርስ ንፅህናን መጠበቅ

🦷 የስኳር ህመም የጥርስ መቦርቦር እና ጥርስ አቃፊ አካላት በቀላሉ እንዲጎዱ ሊያደርግ ይችላል።

ለበለጡ የጤና ምክሮች እና መረጃ ወደ 7560 | 0116639634 | 0116180449 ይደውሉ
Telegram | Instagram | Tiktok | Facebook

15/10/2025

ዜና እረፍት
በአዲስ ህይወት አጠቃላይ ሆስፒታል በ ህጻናት ቀዶ ህክምና ክፍል ሲሰሩ የቆዩት ፕሮፌሰር አመዘነ ታደሰ ከዚህ አለም በሞት በመለየታቸው የተሰማንን ጥልቅ ሃዘን እንገልፃለን። ለመላዉ ቤተሰቦቻቸው እና ወዳጆቻቸው መፅናናትን እንመኛለን።

አዲስ ህይወት አጠቃላይ ሆስፒታል

Want your practice to be the top-listed Clinic in Addis Ababa?
Click here to claim your Sponsored Listing.

Category

Telephone

Address


Haile Gebre Silase Street
Addis Ababa
170023