Desalegn Hagirso

Desalegn Hagirso

Share

14/03/2026

Sidaama federaaliste paarte ayirrado sidaamu dagara hawalle fichee cambalaallate ayyaanira keerunni iillishi'ne yitanno sokko saayissino.

Sidaamu daga ha'nura budese seeda yannanni kaayisse babbaxitino kadote gashshootubba bude ciiggishate adhitanni keeshsh*tino qaafo gufissukkini akkimale waaga baatte techo ilamara iillishshino. Konne bulduudda bude techo yannara tini ilama gobbatennino sa'e kalqete deerrinni afansha afire dhagete donira maarekkamanno gede loossinoti sidaamu dagaha sigiiga budu tareessonna s***a gede ugginannikki bareda daga ikkase leellishshanno.

Sidaama federaaliste paarteno sidaamu daga bulduudda bude polisenna pirograamese biso assatenni, bude yannite egenno ledo waaxxe bowirsate kaajjillunni loossanni nooota egensiissanno.

Jeefoteno SFP Sidaamu daga baalanta hawalle diru soorro fichee-canbalaallate ayyaannira keerunni iillishinoke yitanni, haaru diru soorro ayaani keerunniha, altennihanna baxillunniha ikkanno gede kaajjado halchose xawissanno.

AAYIIDDE CANBALAALLA !!!

03/09/2025
30/08/2025

#መረጃ: በሲዳማ ክልል የጡረታ መዋጮ የተሰበሰበውን ገንዘብ ለማህበራዊ ዋስትና ገቢ መደረግ የሚገባውን ዘጠኝ መቶ ሚልዮን ብር መዘረፉ ተሰማ፤

በሲዳማ ክልል ለማህበራዊ ዋስትና የመንግሥት ሠራተኞች ከደመወዛቸው የተቀነሰ እና የመንግሥት ድርሻ የጡረታ መዋጮ የተሰበሰበውን በወቅቱ መከፈል የነበረበት ዘጠኝ መቶ ሚልዮን ብር በክልሉ መንግስት አማካኝነት ላልተገባ መንገድ መባከኑ ተነገረ።

ከወረት በፊት የክልሉ መንግሥት የጥሬ ገንዘብ እጥረት አጋጥሞኛል በማለት በሰኔ ወር 2017 ዓ.ም በክልሉ ካቢኔ አስወስኖ ከ2018 ባጀት ብድር ለመቀበል ለገንዘብ ሚኒስተር ጥያቄ ማቅረቡን ዘግበን እንደነበር አይዘነጋም። ገንዘብ ሚኒስተሩ ይህንን የብድር ጥያቄ ተከትሎ አቶ አህመድ ሽዴ ብድሩ እንድፈቀድላቸው ወደ ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ደብዳቤ የተላኩ ቢሆንም፤ በጠቅላይ ሚኒስተር አብይ አህመድ (ዶ/ር) ባለመስማማት ምክንያት እንዲታገድ መደረጉ ተሰምቷል፡፡

የመረጃ ምንጫችን አንደገለጹት በሲዳማ ክልል በክልሉ መንግስት ደረጃ የተንሰራፋው ሌብነት እና ሙስና የመንግሥትን በጀት በጠራራ ፀሀይ እንድመዘበር አድርጓል የተባለ ስሆን፤ የ2017 በጀት አመት የተፈቀደውን በጀት ከታለመለት ዓላማ ውጪ በማዋል፤ ምንም ዓይነት የልማት ሥራዎች ሳይሠራ፤ በሙስና እና አላስፈላጊ ድግስ በማዘጋጀት እንድሁም፤ በሽልማት መልክ ያልተገባ ጥቅም በማሰባሰብ በጀቱን አባክኖ በመጨረስ፤ ገንዘብ ሚንስተር የጠየቀው ብድር ስከለክል፤ ከደሞዝተኛ የተቆረጠ ጡረታ ለማህበራዊ ዋስትና ገቢ መሆን የነበረበትን ዘጠኝ መቶ ሚሊየን ብር ከዓላማው ዉጭ ለግል ጥቅማቸው ብቻ ማዋላቸውን ከታማኝ ምንጮች ያገኘነው መረጃ ያስረዳል። ከመረጃ ምንጫችን መረዳት እንደተቻለው፤ በክልሉ መንግስት ከፍተኛ አመራራሮች ይህንን አስነዋሪ ተግባር በመደረጉ የተነሳ ለረዥም ጊዜ ሀገራቸውን አገልግለው በጡረታ የተገለሉና ቤተሰቦቻቸው በሞት ያጡ ወገኖች ለከፍተኛ ችግር መደረጋቸውን ታውቋል፡፡

ይህ በእንድህ እንዳለ ከፈደራል መንግሥት ግምጃቤት ብድር የተከለከለው የክልሉ መንግስት፤ ከሲዳማ ባንክ እና ከሲዳማ ቡና ዩኒየን 2.5 ቢልዮን ብር ብድር መውሰዱ የተረጋገጠ ስሆን፤ የብድሩ ዓላማ ሁለተኛ ዙር ኮርደር ልማት ማጠናቀቂያ የምል ሰበብ ቢሆንም፤ እስከአሁን ኮርደር ልማትን ለምሰራው ኮንትራክተር የክልሉ መንግስት አምስት መቶ ሚሊየን ብር ብቻ በመከፈሉ ሥራው በሚፈለገው ጥራትና ፍጥነት እየተከናወነ አለመሆኑን እስከ ቦታው ሄዶ ከጎበኙ የዓይን እማኞች ለሉዋ ሚዲያ አስረድተዋል።

ኮንትራክተሩ ለክልሉ ፋይናንስ ቢሮ ቀሪዉን የክፍያ እንዲፈጸም ጥያቀ አቅርቦ፤ ከፋይናንስ ቢሮ የጥሬ ገንዘብ እጥረት አለን በማለት ባለመከፈሉና ሥራውም ስላልተጠናቀቀ በባለፈው የጠቅላይ ሚኒስተሩ ጉብኝት ወቅት የክልሉ አመራር በዓይን የሚታይ የልማት ሥራዎች ለማስጎብኘት መቸገራቸውን ለማወቅ ተችሏል።

በአጠቃላይ የአቶ ደስታ ለዳሞ አስተዳደር በሌብነት ተጨማልቆ የክልሉን ህዝብ ለሁለገብ ችግር በመዳረጉ የመንግሥት ፋይናንስ ብቃት የለላቸውና በሌባ አመራሮች እንዲመራ በማድረግ ክልሉን የከፋ ችግር እንዲዳረግ በማድረጉ እና ማህበራዊ ዋስትና ኤጀንስ ያለአግባብ የተወሰደ ገንዘብ በፍርድ ቤት አስወስኖ ዘጠኝ መቶ ሚሊየን የባንክ ሂሳብ አሳግዶ በመውሰዱ የክልሉ ቢሮዎች ዞኖች እና ወረዳዎች የጥሬ ገንዘብ እጥረት አለን በሚል ምክንያት ምንም ዓይነት ሥራ ሳይሰሩ ሁለት ወር ማሳለፋቸውን ለማወቅ ተችሏል፡፡

ሉዋ ሚዲያ

Want your business to be the top-listed Media Company in Addis Ababa?
Click here to claim your Sponsored Listing.

Address


Chercher
Addis Ababa
...